ሐምሌ ፲፭(አስራ አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በእነ አቶ ተሻለ በካሻ መዝገብ ተከሰው ከሁለት አመታት በላይ በእስር ቤት የቆዩት እስረኞች ሰሞኑን ከፍተኛ ድብደባ ከተፈጸመባቸው በሁዋላ ለተከታታይ ቀናት ምግብ ባለመመገባቸው ህይወታቸው አደጋ ላይ መውደቁን በመግለጽ የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲደርስላቸው አቤት ብለዋል። እስረኞቹ በጻፉት ደብዳቤ ላይ ከውጭ የመጡ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በፌሮ ክፉኛ እንደደበደቡዋቸውና ህክምና በማጣታቸው ከፍተኛ ስቃይ እየደረሰባቸው መሆኑን ገልጸዋል። ፍርድ ቤት ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ኢህአዴግ አንድነት ፓርቲ የጠራው ሰልፍ እንዳይሳካ ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረገ ነው
ሐምሌ ፲፭(አስራ አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አንድነት የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት በማለት የጠራው ህዝባዊ ንቅናቄ ገዢውን ፓርቲ በማስደንገጡን አዲስ ከጀመራቸው ግምገማዎችና የህብዕ እንቅስቃሴዎች ለመረዳት ተችሎአል። በደሴ እና በጎንደር የተካሄደውን ስላማዊ ሰልፍ ተከትሎ የፖሊስ እና የቀበሌ የፖለቲካ አመራሮች በጠንካራ ግምገማ ተይዘው መሰንበታቸውን ከኢህአዴግ ምንጮች ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ስማችን እና ድምጻችን አይተላለፍ ያሉት ምንጮች እንደገለጹት በ1ለ5 አደራጃጀት መሰረት ህዝቡ በሰልፉ ላይ እንዳይገኝ ...
Read More »ኢህአዴግ በልሳናቱና በልማታዊ ባለሃብቶቹ ድጋፍ አትራፊ መሆኑን ገለጸ
ሐምሌ ፲፭(አስራ አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የግንባሩ 9ኛ ጉባዔ ሪፖርት እንደሚያሳየው በ2003 እና በ2004 ዓ.ም ግንባሩ 88 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር ገቢ ያገኘ ሲሆን ቀድሞ በባንክ አካውንት ውስጥ ከነበረው ሒሳብ ጋር ሲደመር ገቢው 171 ነጥብ 2 ሚሊየን መድረሱንም ይፋ አድርጓል፡፡ 46 በመቶ የሚሆነው ገቢ የተገኘው ከ“አዲስ ራዕይ” እና “ህዳሴ” ከተሰኙ ሕትመቶች ሽያጭ ነው ፡፡ ቀሪው 54 በመቶ የተገኘው ደግሞ ...
Read More »በባህርዳር ከተማ በሙስሊሞች እና በፖሊስ መካከል ግጭት ተፈጠረ
ሐምሌ ፲፭(አስራ አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በባህር ዳር ከተማ በህዝበ ሙስሊሙ መካነ መቃብር አጠገብ የሚገኘውን ትንሽ ቦታ መንግስት ሞይንኮ ለተሰኘ የመኪና ጋራጅ ድርጅት አሳልፎ መስጠቱን ተከትሎ የአካባቢው ሙስሊም ባነሳው ተቃውሞ ምክንያት ድርጅቱ ቦታውን እንደማይወስድ እና እንደማይረከብ አስታውቆ ነበር። ትናንት ህዝበ ሙስሊሙ ቦታውን ለማጠር እና አታክልት ለመትከል ሲሰባሰብ የፌደራል ፖሊስ በፍጥነት በመምጣት ያስቆማቸው ሲሆን እርምጃውን ተከትሎ በሙስሊሙ ማህበረሰብ እና በፌደራሎቹ ...
Read More »በረመዳን ጾም ሙስሊሙ ተቃውሞውን አጠናክሮ ቀጥሎአል
ሐምሌ ፲፪(አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መንግስት በረመዳን ጾም ሙስሊም ኢትዮጵያውያን የጀመሩት ተቃውሞ ይበርዳል የሚል እምነት የነበረው ቢሆንም፣ ተቃውሞው ከሳምንት ሳምንት እያየለ በመምጣቱ፣ የፌደራል ፖሊስ አባላት በአንዳንድ አካባቢዎች የሀይል እርምጃ መውሰድ ጀምረዋል። ከሀሙስ ጀምሮ በፌደራል ፖሊስ አባላት ክትትል ስር የነበሩት የወልድያ ሙስሊሞች በዛሬው እለት በመስጊዳቸው ውስጥ ታግተው መዋላቸውና አንዳንዶች መደብደባቸውን ሌሎች ደግሞ መታሰራቸው ታውቋል። የፌደራል ፖሊስ አባላት ወደ ...
Read More »አንድነት ፓርቲ ተቃውሞ የሚካሄድባቸውን ቦታዎች ይፋ አደረገ
ሐምሌ ፲፪(አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ፓርቲው ባወጣው የህዝባዊ ንቅናቄ እቅድ መሰረት ባህርዳር፣ ጅንካ፣ አርባምንጭ፣ አዳማ፣ ባሌ፣ ወሊሶ፣ ፍቼ፣ ጋምቤላ፣ አሶሳ እና አዲስ አበባ ለህዝባዊ ሰልፎች ሲመረጡ፣ መቀሌ፣ ወላይታ ሶዶ፣ አዋሳ፣ ድሬዳዋ፣ አምቦ፣ ደብረማርቆስና አዲስ አበባ በድጋሜ ለህዝባዊ ስብሰባዎች ተመርጠዋል። ሀምሌ 21 እና 28 በአዲስ አበባ 2 ቦታዎች እንዲሁም ሀምሌ 28 በወላይታ ሶዶና በመቀሌ ህዝባዊ ስብሰባዎች ሲደረጉ፣ በተመሳሳይ ...
Read More »በአማራ ክልል ከ2001- 2004 ዓ.ም ባሉት ጊዜያት ብቻ 67 በገንዘብ የማይተመኑ ቅርሶች ተዘረፉ ፡፡
ሐምሌ ፲፪(አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የክልሉ ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት አጠናቅሮ ለክልሉ ባለስልጣናት ባቀረበው ሪፖርት ላይ እንተመለከተው የክልሉ ቅርስ ጥበቃ ቢሮ ታሪካዊ ቦታዎችን በመንከባከብና የቅርስ ዘረፋ እንዳይካሄድ በመከላከል በኩል በቂ ጥረት አላደረገም። በክልሉ ከ3000 በላይ የቅርስ መገኛ ተቋማት ቢኖሩም ሙዝየም በማሰራት ቅርሶቻቸውን በጥንቃቄ ለእይታ የቀረቡት 13 ብቻ መሆናቸውን የኦዲት ሪፖርቱ ጠቁሟል፡፡ በተለያዩ ዞኖች የሚጠፉ ታሪካዊ ቅርሶች ከአመት ...
Read More »ኢትዮጵያዊው ፓይለት የ78 ሰዎችን ህይወት አተረፈ
ሐምሌ ፲፪(አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ረቡእ 78 ሰዎችን አሳፍሮ ከአዲስ አበባ ወደ አክሱም ይበር የነበረው ቦምባርዴር ኪው 400 አውሮፕላን ማረፊያ ቦታው ላይ ሊደርስ ደቂቃዎች ሲቀሩት የጭስ መቆጣጠሪያው በመጥፋቱ፣ ፓይለቱ አውሮፕላኑን በአስቸጋሪ ሁኔታ በማሳረፍ የሰዎችን ህይወት እና የአየር መንገዱንም መልካም ስም ታድገዋል። ሱዳን ትሪቢውን አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ባለስልጣንን ጠቅሶ እንደዘገበው የጭስ መቆጣጠሪያው አውሮፕላኑ ለማረፍ አንድ ደቂቃ ...
Read More »በወልድያ 2 ወር ያልሞላትን አራስ ጨምሮ ከ10 ያላነሱ ሙስሊሞች ታሰሩ
ሐምሌ ፲፩(አስራ አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዘወትር አርብ የሚደረገውን ስግደት ተከትሎ ተቃውሞ ሊያስነሱ ይችላሉ ተብለው የተጠረጠሩ ከ10 ያላነሱ የወለድያ ከተማ ነዋሪዎች ታስረው ፍርድ ቤት መቅረባቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት ተናግረዋል። ከታሰሩት መካከል ኢብራሂም ገበየሁ፣ ከድር ሙሀመድ፣ ወ/ሮ ሀያት ይማም፣ ወ/ሮ ነሲሳ አህመድ፣ ወ/ሮ ሀያት አህመድ ይገኙበታል። ወ/ሮ ሀያት አህመድ ሁለት ወር ያልሞላት አራስ ስትሆን፣ ወደ እስር ቤት የተወሰደችውም አዲስ ከተወለደው ...
Read More »አንድነት የተቃውሞ ፊርማ የማሰባሰብ ሂደቱ በደህንነቶችና በፖሊስ ጥምረት እየተደናቀፈ ነው አለ
ሐምሌ ፲፩(አስራ አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ፓርቲው በህገ ወጥ የዘመቻ እስር የሚሊዮኖች ድምፅ አይታጠፍም” በሚል ርእስ ባወጣው መግለጫ በአዲስ አበባ ከተማ የጸረ ሽብር አዋጁ በህገ መንግስቱ እውቅና የተቸራቸውን መብቶችን የሚጨፈልቅና ከህገ መንግስቱ ድንጋጌዎች ጋር የሚጋጭ በመሆኑ መሰረዝ ይገባዋል የሚሉ ዜጎች ወደ ዋናው የፓርቲው በጽ/ቤት በመምጣት የተቃውሞ ፊርማቸውን እንዲያኖሩ የሚጠይቅ ‹‹ከሚሊዮኖች ለምን አንዱ አይሆኑም›› የሚል በራሪ ወረቀት በሁሉም የአዲስ አበባ ...
Read More »