አንድነት ፓርቲ ተቃውሞ የሚካሄድባቸውን ቦታዎች ይፋ አደረገ

ሐምሌ ፲፪(አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ፓርቲው ባወጣው የህዝባዊ ንቅናቄ እቅድ መሰረት ባህርዳር፣ ጅንካ፣ አርባምንጭ፣ አዳማ፣ ባሌ፣ ወሊሶ፣ ፍቼ፣ ጋምቤላ፣ አሶሳ እና አዲስ አበባ ለህዝባዊ ሰልፎች ሲመረጡ፣ መቀሌ፣ ወላይታ ሶዶ፣ አዋሳ፣ ድሬዳዋ፣ አምቦ፣ ደብረማርቆስና አዲስ አበባ በድጋሜ ለህዝባዊ ስብሰባዎች ተመርጠዋል። ሀምሌ 21 እና 28 በአዲስ አበባ 2 ቦታዎች እንዲሁም ሀምሌ 28 በወላይታ ሶዶና በመቀሌ ህዝባዊ ስብሰባዎች ሲደረጉ፣ በተመሳሳይ ቀን ሀምሌ 28 በባህርዳር፣ ጅንካና አርባምንጭ የተቃውሞ ሰልፎች ይደረጋሉ።

ነሃሴ 12 ደግሞ አዳማ፣ ባሌ፣ ወሊሶ እና ፍቼ የተቃውሞ ሰልፎችን ሲያስተናግዱ ነሃሴ 26 ደግሞ ጋምቤላና አሶሳ ያስተናግዳሉ። ድሬዳዋ አዋሳ፣ አምቦና ደብረማርቆስ ከተሞች ደግሞ ነሀሴ 26 ህዝባዊ ስብሰባዎችን ያደርጋሉ። መስከረም 5፣ 2006 ዓም  ፣ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋና አንዱአለም አራጌ የታሰሩበትን 2ኛ አመት ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ የማጠቃለያ የተቃውሞ ሰልፍ ይደረጋል።

ከፓርቲው ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው ከደሴና ጎንደር የተቃውሞ ሰልፎች በሁዋላ ድርጅቱን የሚቀላቀሉ ሰዎች ጨምረዋል።