.የኢሳት አማርኛ ዜና

በጎንደር ከተማ ህዝበ ሙስሊሙ በመንግስት ላይ ቅሬታውን እየገለጠ ነው፡፡

ሐምሌ ፳፬(ሃያ አራት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የመቃብር ቦታ ጥያቄያችን አልተመለሰም ፤ ለመስጊዶቻችንን  የባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተር ተከልክለናል፡፣ ሙስሊሙ ህብረተሰብ ፍትህ አጥቷል” በማለት ሙስሊሞች ተናግረዋል። የጎንደር ከተማ ኗሪ የሆኑት ሐጅ ሙርፉቅ ሙስሊሙ ከመንግስት ጋር ሆድና ጀርባ መሆኑን ገልጸዋል። በየቀኑ ደብዛቸው እየጠፋ በአፋልጉኝ የሚጠሩት ህዝበ ሙስሊሞች የመንግስት የአፈና ውጤት መሆናቸውን የተናገሩት የጎንደር ህዝበ ሙስሊሞች፤ያለምንም ፍትህ የሚያስረውና የሚያንገላታው ኢህአዴግ የማሰተዳደር አቅሙ ደካማነትን ...

Read More »

ከ2 ቢሊዩን ብር በላይ በሆነ ወጭ የተገነቡ የውሃ ተቌማት ላይ ጉዳት ደረሰ

ሐምሌ ፳፬(ሃያ አራት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአማራ ክልል በሚገኙ የተለያዩ ዞንና ወረዳዎች በበጎ አድራጊዎች ድጋፍና በህብረተሰቡ የተገነቡ ከ110 በላይ  የውሃ ተቌማት ላይ የእጅ ፓምፕ ዝርፊያ በመፈጸሙ በውሀ አቅርቦቱ ላይ ችግር ተፈጥሯል። ዝርፊያውን ተከትሎ የወረዳ አመራሮች ለህዝቡ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ናቸው እያሉ ፤ ፓርቲዎችን የማሰጠላት ዘመቻ እያከናወኑ ነው፡፡ በተለያዩ  አካባቢዎች እየተከሰተ ባለው የውሃ ተቋማት ዝርፊያ እስካሁን ወደ 250 የሚጠጉ ሰዎች ...

Read More »

የሰቆጣ ከተማ ወጣቶች “ችግራችን በዝቷል ነጻነት እንፈልጋለን” አሉ

ሐምሌ ፳፫(ሃያ ሦስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ቅዳሜ ከላሊበላ ሰቆጣ ይሰራል ተብሎ የነበረው መንገድ ባለመሰራቱ የተበሳጩት   የከተማዋ ነዋሪዎች በራሳቸው አነሳሽነት የተቃውሞ ሰልፍ ያደረጉ ሲሆን፣ ወጣቶቹ አጋጣሚውን በመጠቀም ” ነጻነት እንፈልጋለን፣ እኛ ወታቶች ብዙ ችገሮች አሉብን፣  ሰቆጣ መብት የለም፣ ብልጭጭልታ የእድገት ምልክት አይደለም፣ እድገት የለም፣ መንገድ ላሳ ህዝብ መንገድ ሊከለከል አይገባውም፣ ልማት በተግባር እንጅ በውሬ አይደለም፣ ዋግ ለጦርነት ብቻ ...

Read More »

ከብአዴን ድርጅቶች አንዱ የሆነውና በጥረት ሥር የሚገኘው ጣና ሞባይል ከስሮ ሠራተኞችን መቀነስ ጀመረ፡፡

ሐምሌ ፳፫(ሃያ ሦስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ጣና ሞባይል የኢትዮጵያ ቴሌኮምኒኬሽን ደንበኛ ከሆነው ከቻይናው ግዙፍ ቴሌኮም ኩባንያ ዜድ.ቲ.ኢ  ጋር በጋራ ለመስራት በደረሱት ስምምነት መሰረት በ2003 ዓ.ም በ50 ሚሊየን ብር ወጪ በባህርዳር ከተማ ዘመናዊ የሞባይል ቀፎዎችን ማምረቻ ፋብሪካ በመክፈት ምርቱን ለአገር ውስጥ ገበያ ሲያቀርብ ቆይቷል፡፡ ሆኖም ፋብሪካው ባልታወቀ ሁኔታ  ከቀጠራቸው ሠራተኞቹ መካከል ወደ 70 የሚጠጉትን ከዚህ ወር መጀመሪያ ጀምሮ በይፋ ...

Read More »

የመድረክ ሕዝባዊ ስብሰባ የፊታችን እሁድ ይካሄዳል

ሐምሌ ፳፫(ሃያ ሦስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአራት ፓርቲዎች ግንባር የሆነው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ በአደባባይ ላይ ሊያካሂድ ያቀደውን የአደባባይ ሰልፍ ተገዶ ወደ ሕዝባዊ ስብሰባ መቀየሩ ታውቋል፡፡ በዚሁ መሠረት ግንባሩ የፊታችን እሁድ ሐምሌ 28 ቀን 2005 ዓ/ም ሕዝባዊ ስብሰባ መጥራቱን የአዲስ አበባው ዘጋቢ ገልጿል፡፡ ከወቅታዊ የአገራችን ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ሐምሌ 7 ቀን 2005 ዓ.ም በአዲስአበባ ከስድስት ኪሎ እስከድላችን ...

Read More »

ኢህአዴግ የመለስ ሙት አመት መታሰቢያን በልዩ ዝግጅት ሊያከብር ነው

ሐምሌ ፳፪(ሃያ ሁለት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቀድሞ ጠ/ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ሙት ዓመት አከባበር ሥነ ሥርዓት ጋር  በተያያዘ ሠራተኞቹን በየደረጃው ማወያየት ጀመረ፡፡ሕዝብ በከፍተኛ ደረጃ ከመሰልቸቱ ጋር ተያይዞ በመንግስት መገናኛ ብዙሃን ሽፋናቸው እንዲቀንስ ተደርጎ የነበሩት የአቶ መለስ ርዕሰ ጉዳይ- ሙት ዓመታቸውን ተከትሎ እንደገና አዲስ አጀንዳ ሆኗል፡፡ የአስተዳዳሩ ምንጮች እንደገለጹት የአቶ መለስን ሙት ዓመት በአረንጓዴ የልማት ዘመቻ ...

Read More »

በወልድያ ከተማ 3 ሰዎች ተገድለው ተገኙ

ሐምሌ ፳፪(ሃያ ሁለት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት ወኪል ከስፍራው እንደዘገበው ሁለቱ ሰዎች በአንድ ቦታ ላይ ተገድለው ተጥለው ሲገኑ፣ አንደኛው የተገኘው በተለየ ስፍራ ነው። ሰዎቹ በምን ምክንያት ተገድለው እንደተገኙ ለማወቅ አሳት ወደ አኳባቢው ፖሊስ  በመደወል ላቀረበው ጥያቄ፣ ፖሊስ ሰዎቹ ተገድለው መገኘታቸውን አረጋግጦ፣ ስለአሟሟታቸው ምክንያት ማጣሪያ እያደረገ መሆኑና ምርመራውንም እንደጨረሰ መረጃውን ይፋ እንደሚያደርግ ገልጿል። ኢሳት በጉዳዩ ዙሪያ ተጨማሪ መረጃዎች እንደደረሱት ዝርዝር ...

Read More »

በቁጫ ወረዳ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ከታሰሩት ውስጥ የተወሰኑት ተፈቱ

ሐምሌ ፳፪(ሃያ ሁለት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከማንነት ጥያቄ ጋር በተያአዘ በቅርቡ በጋሞጎፋ ዞን በቁቻ ወረዳ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ከታሰሩት በርካታ ሰዎች መካከል 13ቱ ዛሬ በዋስ የተለቀቁ ሲሆን፣ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሰዎች ደግሞ ለሀምሌ 25 መቀጠራቸውን ለማወቅ ተችሎአል። በቅርቡ በወረዳው የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ የከተማዋ አገር ሽማግሌዎች እና ታዋቂ ሰዎች መታሰራቸው ይታወቃል ።

Read More »

በኢትዮጵያ የሚገኘው የከፍተኛው ፍርድ ቤት ተቋማዊ ብቃት አጅግ አሳሳቢ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ባለ ጉዳዮች በስፍራው ይገኝ ለነበረው ለኢሳት ዘጋቢ ገለጹ::

ሐምሌ ፳፪(ሃያ ሁለት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለጉዳዮቹ  የከፍተኛው ፍርድ ቤት በደርግ ጊዜ ከነበረው የቀበሌ ፍርድ ሸንጐ ማነሱንና በጥራትም በብቃትም እጅግ መውረዱን ገልጸዋል:: የከፍተኛው ፍርድ ቤት በሚሊዮን የሚቆጠር የገንዘብና የንብረት ክርክሮችን የሚዳኝ ሲሆን አልፎ አልፎ የወንጀል ጉዳዮችን ይመለከታል:: ይህ ፍርድ ቤት የተሟላ የህዝብ መጸዳጃ የሌለውክመሆኑም በላይ መብራት ሲቋረጥ ጀነሬተር ባለመኖሩና የፍርድ ቤቱ የድምጽ ቀረጻ ስለሚስተጎገል ባለጉዳዮችም ለተጨማሪ ቀጠሮ ይዳረጋሉ ። ...

Read More »

የአንድነት አባል የሆኑት አቶ ግርማ ወልደሰንበት አረፉ

ሐምሌ ፳፪(ሃያ ሁለት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አቶ ግርማ በህይወት ዘመናቸው ለሚወዷት ሀገራቸው ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ በተለያዩ ሀርፎች ያገለገሉ ሲሆን ወደ ፖለቲካው በመግባትም ትልቅ ዋጋ የከፈሉ የቁርጥ ቀን ልጅ ነበሩ ሲል አንድነት ፓርቲ ለኢሳት በላከው መግለጫ አመልክቷል። አቶ ግርማ ወደ ተቃውሞ ጎራው ትግል የገቡት ለ1984 ዓ/ም ከፕ/ር አስራት ወልደየስ ጋር በመሆን መአህድን በመመስረት ነው። የመኢአድ አባልና የአዲስ አበባ ሰብሳቢ በሁዋላም ...

Read More »