መስከረም ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-እውቋ የብእር ሰው፣ የነጻነት ታጋይ፣ የዩኒስኮና የኢንተርናሽናል ውሜንስ ሚዲያ ፋውንዴሽን አሸናፊ ጸሀፊና መምህርት ርእዮት አለሙ ዛሬም በረሀብ አድማው ገፍታበታለች። እህቷ እስከዳር አለሙ እንደገለጸችው ዛሬ እርሷና የርእዮት እጮኛ የሆነው ስለሺ ሀጎስ ወደ ቃሊቲ እስር ቤት ቢሄዱም እንዳይገቡ ተከልክለዋል። እጮኛዋ ስለሺ ለሰአታት ታግቶ በማረሚያ ቤቱ ፖሊሶች መደብደቡንም እስከዳር ተናግራለች ርእዮት ከእናት፣ አበቷና የንስሀ አባታ በስተቀር ሌላ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የስኳር ፋብሪካዎች የግንባታ ሂደት ችግር ውስጥ ነው ተባለ
መስከረም ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ መንግስት በቀጣዩ ዓመት በሚጠናቀቀው የአምስት ዓመት ዕቅዱ በስኳር ኢንዱስትሪ ዘርፍ ለመገንባት ያቀደውን እንደማያሳካ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገለጹ። በህወሃት ነባር ታጋይ አቶ አባይ ጸሐዬ የሚመራው የስኳር ኮርፖሬሽን ከነባርና ዕውቀትና ልምዱ ካላቸው ባለሙያዎች ጋር ተግባብቶ መስራት ባለመቻሉ ብዙዎቹ ኮርፖሬሽኑንና በስሩ ከሚገኙ የስኳር ፋብሪካዎች ለቅቀዋል፡፡ ኮርፖሬሽን የገጠመውን የሰለጠነ የሰው ኃይል እጥረት ከውጪ አገር ባለሙያዎችን በመቅጠር ...
Read More »ቻይና ለመለስ ፋውንዴሽን ማስገንቢያ ገንዘብ ለገሰች
መስከረም ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአቶ መለስን ፋውንዴሽን ለመገንባት መንግስትና የመለስ ፋውንዴሽን በጋራ በመንቀሳቀስ ላይ ባሉበት በዚህ ጊዜ፣ የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ልኡካን ለፋውንዴሽኑ ግንባታ የሚውል 50 ሺ ዶላር ለመለገስ ቃል መግባቱዋን የልኡካን ቡድኑ መሪ ሚስተር ዛሆ ገልጸዋል። አቶ መለስ በቻይናና በኢትዮጵያ መካከል ያለው ግንኙነት እንዲጠናከር በማድረጋቸው ልኢካኑ አመስግነዋቸዋል። ቻይና የኢትዮጵያን የአምስት አመት የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ እንደምትደግፍም እኚሁ ባለስልጣን ገልጸዋል።
Read More »የግብጽ ጊዜያዊ መንግስት የደነገገውን የ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለተጨማሪ 2 ወራት አራዘመ።
መስከረም ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቢቢሲ ከፕሬዚዳንቱ ጽህፈት ቤት የወጣውን መግለጫ በመጥቀስ እንደዘገበው፤ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ማራዘም ያስፈለገው ከአገሪቱ የ ደህንነት ሁኔታ ጋር በተያያዘ ነው። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተደነገገው ባለፈው ነሐሴ ወር በመሀመድ ሙርሲ ደጋፊዎች ላይ የግብጽ ፖሊስና መከላከያ የሀይል እርምጃ መውሰዳቸውን ተከትሎ ነው። የፕሬዚዳንት መሀመድ ሙርሲን ከስልጣን መወገድ በተቃወሙ ደጋፊዎቻቸው ላይ በተወሰደው እርምጃ በመቶዎች የሚቆጠሩ ግብጻውያን መገደላቸው ይታወሳል። ...
Read More »በሩሲያ ሆስፒታል ውስጥ በተነሳ የእሳት አደጋ 37 ሰዎች ሞቱ
መስከረም ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሰሜን ምዕራብ ሩሲያ በሚገኝ በ አንዳ ሳይካተሪክ ሆስፒታል ውስጥ በተነሳ የ እሳት አደጋ 37 ሰዎች መሞታቸውን ባለስልጣናት ገለጹ። “ኖቭጎሮድ” ተብሎ በሚጠራው ግዛት በ”ሉካ” መንደር ውስጥ ከእንጨት በተሠራው ሆስፒታል ውስጥ ወደ 60 ሰዎች እየታከሙ ነበር። የሩሲያ ብዙሀን መገናኛ ሪፖርቶችን በመጥቀስ ቢቢሲ እንዳለው፤ ህሙማኑን ትንከባከብ የነበረች አንዲት ነርስም ከሟቾቹ መካከል ትገኝበታለች። እስካሁን ከሟቾቹ መካከል የ15ቱ አስከሬን ...
Read More »ጋዜጠኛ ርእዮት አለሙ በረሀብ አድማው ገፍታበታለች
መስከረም ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የዩኒስኮና የ’ኢንተርናሽናል ዊመንስ ሚዲያ ፋውንዴሽን’ ሽልማቶች አሸናፊ የሆነቸው ታዋቂዋ ፀሀፊና መምህር ርእዮት አለሙ በእስር ቤት የጀመረቸውን የረሀብ አድማ የቀጠለች ሲሆን፣ በእስር ቤት የሚገኙ ሌሎች እስረኞች እያሰቃዩዋት መሆኑን ለማወቅ ተችሎአል። በግፍ የታሰረቸው ርእዮት ይቅርታ ለመጠየቅ ፈቃደኛ ባለመሆኑዋ የሚደርስባት ስቃይ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው። ሆን ተብሎ በተቀነባበረ ስልት ርእዮት ከእናትና አባቷ እንዲሁም ከነፍስ አባቷ በስተቀር ...
Read More »ፖሊስ የፍርድ ቤት ትእዛዝ አልቀበለም በማለት በቁጫ ወረዳ ያሰራቸውን የሀገር ሽማግሌዎች ለመፍፋት ፈቃደኛ ሳይሆን ቀረ
መስከረም ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጋሞጎፋ ዞን በቁጫ ወረዳ በቅርቡ የተነሳውን የህዝብ ተቃውሞ መርታችሁዋል በሚል የታሰሩ የወረዳዋ አገር ሽማግሌዎች እና ነዋሪዎች ማስረጃ በመጥፋቱ እንዲፈቱ ፍርድ ቤት ሀምሌ 22 እና 30 ቢወስንም ፖሊስ የፍርድ ቤትን ትእዛዝ አልቀበልም በማለት ግለሰቦቹ እስከሁን ድረስ ታስረው እንደሚገኙ ታውቋል። ፖሊስ ከፍርድ ቤት በላይ ሆኖ እስረኞችን አልፈታም ማለቱ እና እንዲያውም ሌሎች ተጨማሪ ሰዎችን ለማሰር በዝግጅት ላይ ...
Read More »መብራት ሀይል ለሁለት አመታት በህዶች ሊተዳደር ነው
መስከረም ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያን ህዝብ የመብራት ፍላጎት ማሙዋላት ያልቻለውን መብራት ሀይልን ከ300 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ክፍያ የህንድ ኩባንያ ሊያስተዳድረው ነው። ቴሌን ሲያስተዳድረው የነበረው የፈረንሳይ ኩባንያ በሺ የሚቆጠሩ ሰራተኞችን በማባረርና በቦታቸው በተለይም ከመከላከያ የመጡ ሰዎች እንዲይዙት ከማድረግ የዘለለ ነገር አልፈጸመም በሚል በሰራተኞች ሳይቀር ትችት ቢቀርብበትም፣ መንግስት መብራት ሀይልንም በተመሳሳይ መንገድ ለማስተዳደር ያወጣውን እቅድ ተግባራዊ አድርጓል። አዲሱ ኩባንያ በርካታ ...
Read More »ሶሪያ የኬሚካል የጦር መሳሪያዎቿን ለማስፈተሽ መስማማቱዋን ፕሬዚዳንት አሳድ አስታወቁ
መስከረም ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከምእራባዊያን አገራት በተለይም ከአሜሪካ ድብደባ ለጊዜውም ቢሆን የተረፈችው ሶሪያ በአገሯ ያሉ የኬሚካል የጦር መሳሪያዎችን በሙሉ ለማውደም ፈቃደኛ መሆኑዋን ፕሬዚዳንት በሽር አላሳድ ተናግረዋል። ከሩሲያ የቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት አላሳድ፣ አገራቸው ስምምነቱን የምትፈርመው ሩሲያ ስላግባባቻች እንጅ የአሜሪካን ጥቃት ፈርታ አይደለም። የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሜር ፑቲን በኒውዮርክ ታይምስ ላይ ለአሜሪካ ህዝብ እንዲደርስ በማለት ባሰፈሩት ጽሁፍ አሜሪካ ...
Read More »ኢሳት የቶምቦላ እጣ ማውጣቱን ስነስርአት ለአንድ ወር ማራዘሙን አስታወቀ
ጳግሜ ፭(አምስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢሳት ለኢትዮጵያውያን አዲስ አመት የመኪና የቶምቦላ ትኬት ማዘጋጀቱ ይታወቃል። ይሁን እንጅ በተለያዩ አገራት የሚገኙ የሽያጭ ወኪሎቻችን፣ በርካታ ኢትዮጵያን የሽያጭ ጊዜው በአንድ ወር እንዲራዘም መጠየቃቸውን ተከትሎ ሽያጩን ለመጨረሻ ጊዜ ለአንድ ወር ለማራዘም መወሰኑን የድርጅቱ የገቢ አሰባሳቢ ግበረሀይል ገልጿል። ተቋሙ እጣውን አስቀድሞ በተያዘለት መረሀ ግብር ለማውጣት ባለመቻሉም ይቅርታ ጠይቋል። በተለያዩ አገራት የሚገኙ የኢሳት የሽያጭ ወኪሎች፣ በእጃችው ...
Read More »