መስከረም ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-33ቱ ፔቲሽን ፈራሚ ፓርቲዎች ባወጡት መግለጫ ፣ በርካታ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሰላማዊ ትግላቸውን ለማስፋት በተጠናከረ መንገድ እየተንቀሳቀሱ ቢሆንም፣ መንግስት የህግ ጥበቃ ሊያደርግ ባለመቻሉ ከፍ ያለ ጉዳት እየደረሰባቸው ነው ብለዋል። አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ በወላይታ፣ በአርባ ምንጭ፣ በፍቼና፣ በጎባ ከተሞች በተንቀሳቀሰባቸው ወቅቶች አባሎቻቸው መደብደባቸውን፣ መታሰራቸውን፣ የሥራ መሣሪያዎቻቸውን መነጠቃቸውን፣ ለመኝታ ገንዘብ የከፈሉበት ሆቴል በር እንዲዘጋባቸውና ደጅ እንዲያድሩ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ጋዜጠኛ ርዕዮት ዐለሙ እና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የሻካሮቭ ሽልማት የ2013 ዕጩ ሆነው ተመረጡ።
መስከረም ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጋዜጠኛ ርዕዮት ዐለሙን ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን እና አሜሪካዊው ኤድዋርድ ስኖውደንን ጨምሮ ሰባት ሰዎች የአውሮፓ ህብረት ለነፃነት ታጋዮች በየአመቱ ለሚያዘጋጀው የ “ሻካሮቭ ሽልማት” የ2013 ዕጩ ሆነው ተመረጡ። የአውሮፓህብረት የሻካሮቭ ሽልማት ኮሜቴ-ከህብረቱ የውጪ ጉዳይና ልማት ኮሚቴ እና ከሰብዓዊ መብት ንዑስ ኮሚቴ ጋር በመሆን ትናንት ሰኞ ይፋ እንዳደረጉት ማላላ ዩሳፍዛይ ከፓኪስታን፣ ኤድዋርድ ስኖውደን ከ አሜሪካ፣ርዕዮት ዓለሙና እስክንድር ነጋ ...
Read More »በአማራ ክልል በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በከተማ መልሶ ማልማት ይፈናቀላሉ፡፡
መስከረም ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከ8 ሺ 800 በላይ ሰዎች በመልሶ ማልማት የተነሳ እንደሚፈናቀሉ ከክልሉ የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ተፈናቃዮች እንደሚሆኑ ያወቁ ነዋሪዎች በከፍተኛ የኑሮ ችግር ውስጥ ወድቀናል ሲሉ አማረዋል።በአማራ ክልል በሚገኙ በሶስቱ የክልሉ ሜትሮፖሊታን ከተሞች ማለትም በባህርዳር፣ደሴና ጎንደር በመልሶ ልማት የሚፈናቀሉ 5 ሳይቶች ተለይተው ተከልለዋል፡፡ በባህርዳር በመጀመሪያው ዙር 431 የቀበሌ ቤት ተከራዮች ፣ 2 ሺ 155 ቤት ተጋሪዎችና ቤተሰቦቻቸው ...
Read More »በኬንያው ም/ል ፕሬዚዳንት ላይ የመጀመሪያዋ መስካሪ ቀረቡ
መስከረም ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከስድስት አመታት በፊት በኬንያ ከተደረገው ምርጫ ጋር በተያያዘ ለተገደሉት ሰዎች ተጠያቂ የተደረጉት የአገሪቱ ምክትል ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ዘ ሄግ በሚገኘው አለማቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤት በአካል ቀርበው የመጀመሪያዋን የጉዳቱ ሰለባን ቃል አዳምጠዋል። ማንነቷ በውል ያላታወቀችው መስካሪ በረብሻው ጊዜ የደረሰውን ግፍ በዝርዝር አስረድታለች፡፤ ም/ል ፕሬዚዳንቱ ክሱን ውድቅ ማድረጋቸው ታውቋል። ሌሎች 22 ምስክሮችም በተከታታይ ቀርበው እንደሚመሰክሩ ታውቋል። ...
Read More »ሰማያዊ ፓርቲ በመጪው እሁድ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚካሄድ አስታወቀ
መስከረም ፮(ስድት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አዲስ ፓርቲው ባወጣው መግለጫ ምንም እንኳ የአዲስ አበባ መስተዳደር ለሰልፉ በ12 ሰአታት ውስጥ መልስ የመስጠት ሀላፊነት የነበረበት ቢሆንም ይህን አላዳረገም። ፓርቲው የሚጠበቅበትን ሁሉ ለሚመለከተዉ አካል የማሳወቅ ግዴታ በአግባቡ ስለተወጣና ለሰልፉም የሚያስፈልጉ ስራዎች እየተከናወኑ በመሆኑ መስከረም 12 ቀን 2006 ዓ.ም በታቀደው መሰረት ሰልፉ ይካሄዳል ብሎአል፡፡ በዚህ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ የምናነሳቸው ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሲቪክ ...
Read More »734 ሚሊዮን 600 ሺ ብር የመዘብሩ የስራ ሃፊዎች አለመቀጣታቸውን መረጃዎች አመለከቱ
መስከረም ፮(ስድት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አዲስ ከስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሺን የተገኝው መረጃ እንደሚያመለክተው ከተለያዩ የፌደራል መስሪያ ቤቶች 734 ሚሊዮን 6 መቶ ሺ ብር የመዘብሩ የስራ ሃፊዎች በተጣራ መረጃ ክስ ቢመሰረትባቸውም የውሳኔ ቅጣት እንዳልተላለፈባቸው ታውቋል። ለረጅም ጊዜ በተደረገ ምርመራ ተጣርቶና መስረጃ ተገኝቶባቸው ከ2004 ዓም ጀምሮ ክስ የተመሰረተባቸው የተለያዩ የሙስና ወንጀሎች የውሳኔ ሀሳብ እንዳልተላለፈባቸው ከመሰሪያ ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል። በቤንሻንጉል ...
Read More »የኢንዱስትሪው ዘርፍ የወጪ ንግድ አሽቆለቆለ
መስከረም ፮(ስድት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አዲስ በኢንዱስትሪ ዘርፍ ባለፈው ዓመት የተመዘገበው የወጪ ንግድ (ኤክስፖርት) አፈጻጸም እጅግ አነስተኛ እንደነበር ከኢንዱስትሪ ሚ/ር የተገኘ መረጃ አመለከተ፡፡ በ2005 የኢትዮጵያዊያን በጀት ዓመት ከጨርቃጨርቅና አልባሳት፣ ከቆዳና የቆዳ ውጤቶች፣ከአግሮ ፕሮሰሲንግ፣ ከፋርማሲዩቲካልስና ከኬሚካል የወጪ ንግድ 542 ሚሊዮን 4 መቶ ሺ ዶላር ለማግኘት ታቅዶ ማሳካት የተቻለው 281 ሚሊዮን 2 መቶ ሺ ዶላር ወይንም 52 በመቶ ያህሉን ብቻ ነው፡፡ ዘርፉን ባለፉት ሁለት ...
Read More »ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋና ሌሎች በእስር ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የህሊና እስረኞች እንዲፈቱ ተጠየቀ።
መስከረም ፮(ስድት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አዲስ ከዓመት በፊት ኢትዮጵያ ውስጥ ለ14 ወራት በቃሊቲ እስርቤት ከታሰሩ በኋላ ተፈተው የወጡት ስዊድናውያን ጋዜጠኞች ማርቲን ሺቢ እና ዩዋን ፐርሹን እንዲሁም ዓለምዓቀፍ የሰብዓዊና የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅቶች ተወካዮች፡ ጋዜጠኞችና በስዊድን የሚኖሩ በመቶ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን እና ስዊድናውያን አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባዘጋጀው ደብዳቤ ላይ ፊርማቸውን በማኖር ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ የታሰሩ ጋዜጠኞችን እንዲፈቱ ጠይቀዋል። ስዊድናውያን ጋዜጠኞች ኢትዮጵያ ውስጥ ያሳለፉትን የእስር ህይወት የሚተርከውን እና ...
Read More »የአንበሶች መጋቢው -በአንበሳ መበላታቸው ተዘገበ።
መስከረም ፮(ስድት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አዲስ አበባ በተለምዶ አንበሳ ግቢ ተብሎ በሚጠራው የአንበሶች ማቆያ ማእከል ውስጥ ዛሬ ከጠዋቱ 1:30 ላይ የአንበሶች መጋቢ የነበሩ ግለሰብ በ አንበሳ መበለታቸውን ራዲዮ ፋና ዘገበ። እንደራዲዮጣቢያውዘገባአደጋው የተከሰተው በዛሬው እለት ተረኛ ተንከባካቢ የነበሩት እና አቶ አበራ ሲሳይ የተባሉትየአንበሶቹ መጋቢ፥ የአንበሶቹን ማዳሪያ እያጸዱ ባሉበት ወቅት ነው። ከጥንቃቄ ጉድለት ባልተዘጋው በር የገባውና መጋቢውን ለህልፈተ ህይወት የዳረጋቸው አንበሳ ስሙ-ቀነኒሳ እንደሆነም ራዲዮው ጨምሮ ዘግቧል። የግለሰቡን ህይወት ለማትረፍ በወቅቱ በስራ ላይ የነበሩ የግቢው ሰራተኞች ጥረት ቢያደርጉም-ሳይሳካ መቅረቱንም ለማወቅ ተችሏል። የሟች አስከሬን ከመንከባከቢያ ስፍራው ወጥቶ ወደ ምኒሊክ ሆስፒታል ተወስዷል። የዚህ አይነት አደጋ በ19 89 ዓ.ም መከሰቱ የሚታወስ ነው።
Read More »አንድነት ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፉን ለመስከረም 19 ቀን 2006 ዓም አራዘመ
መስከረም ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፓርቲው የምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ዘካርያስ የማነብርሀን እንደገለጹት የአዲስ አበባ መስተዳድር ከተማሪዎች ትምህርት መጀመር እና ከተለያዩ የአዲስ አመት በአላት ጋር በማያያዝ ፓርቲው ሰልፉን በሁለት ሳምንት እንዲያራዝም በተጠየቀው መሰረት፣ ጥያቄውን ተቀብሎ ለማራዘም ፈቃደኛ ሆኗል። መስተዳድሩ ፓርቲው ተቃውሞውን መስከረም 19 ማካሄድ የሚችል መሆኑን ከመስተዳድሩ ወረቀት አግኝቷል። አቶ ዘካሪያስ መስተዳድሩ ሰላማዊ ሰልፉን ለማራዘም የህግ ድጋፍ እንዳለው ገልጸው፣ ...
Read More »