.የኢሳት አማርኛ ዜና

መብራት ሀይል በምዝበራና በብልሹ አሰራር ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ ገንዘብ ማባከኑን ጸረ ሙስና ኮሚሽን በጥናት አረጋገጠ

መስከረም ፳፩(ሃያ አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጸረ ሙስና ኮሚሽን  በአዲስ አበባ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ውስጥ ስላለው የንብረት አስተዳደር አሰራር ስርዓት ጥናት አካሒዶ ከፍተኛ የገንዘብ ጉድለት መገኘቱን አረጋግጧል። በጥናቱ የተለየው የመጀመሪያው ችግር እቃዎች ተገዝተው ወደ ንብረት ክፍል ከመግባታቸው በፊት ንብረት ክፍሉን ቅድመ ዝግጅት እንዲያደረግ የሚያስችለውና ወጥነት ያለው የማሳወቂያ ስርዓት አለመሰራት ነው፡፡ አብዛኛዎቹ ግዥዎች ከተፈጸሙ በኋላ ለእቃ ግምጃ ቤቶች ወጥነት ...

Read More »

የኢህአዴግ ባለስልጣናትን የሚያስተምረው ትምህርት ቤት ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር ውዝግብ ውስጥ ገባ

መስከረም ፳፩(ሃያ አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በፕሮፌሰር ባደግ በቀለ የሚመራውና የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናትን በተለይም የአመራር ሥልጠናዎችን በአገር ውስጥ በማስተማር የሚታወቀው ኢንተርናሽናል ሊደርሺፕ ኢንሰቲትዩት  በትምህርት ሚኒስቴር ስር ካለው የከፍተኛ ትምህርት አግባብነት ጥራት ኤጀንሲ ጋር ውዝግብ ውስጥ መግባቱ  ታውቋል። የሁለቱ አካላት ውዝግብ መነሻ ምክንያቱ ተቋሙ ሳይፈቀድለት በዶክትሬት ዲግሪ ከፍተኛ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር በመጀመሩ ነው፡፡ የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ ኢንስቲትዩት ሳይፈቀድለት ...

Read More »

የአሜሪካ የመንግስት መስሪያቤቶች በበጀት ውዝግብ ምክንያት በከፊል ተዘጉ

መስከረም ፳፩(ሃያ አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር የሪፐብሊካን እና የዲሞክራቲክ ፓርቲ አባላት በአዲሱ በጀት ላይ ስምምነት ላይ ባለመድረሳቸው ሳቢያ  በርካታ መስሪያ ቤቶችና  ተቋማት በከፊል እየተዘጉ ነው።  ሪፐብሊካኑ የምክር ቤት አባላት በጀቱን ለማጽደቅ  የፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ   የህክምና ፖሊሲ ማሻሻያ፤ በእግሊዝኛው አጠራር “ሄልዝ ኬር ሪፎርም” ሊዘገይ ይገባል  የሚል አቋምን እንደ ቅድመ-ሁኔታ አስቀምጠዋል። በዚህም ምክንያት በፌዴራል መስሪያ ቤቶችና በልዩ ልዩ ...

Read More »

ኢሳት ያዘጋጀው የመኪና የቶምቦላ እጣ በፈረንጀች አቆጣጠር ኦክቶበር 11 ታዛቢዎች በተገኙበት በአምስተርዳም ከተማ ይወጣል።

መስከረም ፳፩(ሃያ አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በየአገሩ የተመደቡ የትኬት ሽያጭ ወኪሎች የተሸጡና ያልተሸጡ ቁጥሮችን በመለየት እስከ ኦክቶበር 8፣ በስልክ ወይም በኢሜል እንድታስታውቁ እንጠይቃለን። ትኬቱን እስካሁን ያልገዛችሁ ውድ የኢሳት ቤተሰቦችና ደጋፊዎች የቀሩትን ጥቂት ቀናት በመጠቀም ከአካባቢያችሁ ካሉ ወኪሎች ወይም በኦን ላይን ትኬቶችን መግዛት የምትችሉ መሆኑን ለማስታወስ እንደወዳለን። ትኬቶችን ሽጣችሁ የጨረሳችሁ ደግሞ በኢሳት አካውንት ገንዘቡን ገቢ እንድታደረጉ እናሳስባለን ኢሳት ቶምቦላ ሽያጭ ...

Read More »

አንድነት ፓርቲ የእሁዱን ሰልፍ ውጤት እየገመገመ ነው

መስከረም ፳(ሃያ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፓርቲው አመራሮች በዛሬው እለት ተሰብስበው ትናንት እሁድ ፓርቲው የጠራውን ሰለማዊ ሰልፍ ውጤት ገምግመዋል። መስቀል አደባባይ ብንሄድ ኖሮ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ህዝብ ሊገኝ እንደሚችል የተናገሩት አቶ ደንኤል፣ በከፍተኛ አፈና ውስጥ የተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ ከ80 ሺ በላይ በሆነ ህዝብ መካሄዱ የተሳካና ለሚቀጥለው ሰልፍ ፍንጭ የሰጠ፣ ህዝቡ ለውጥ ፈላጊ መሆኑንና ከፓርቲያቸው ጎን የቆመ መሆኑን ለማየት ችለናል ...

Read More »

ግንቦት7 በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ መስመሩን እየዘረጋ መሆኑን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ተናገሩ

መስከረም ፳(ሃያ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አቶ አንዳርጋቸው ይህንን የተናገሩት በኖርዌይ ከተካሄደው ደማቅ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በሁዋላ ነው። የግንቦት7 ዋና ጸሀፊ የሆኑት አቶ አንዳርጋቸው  የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅቱ በአንድ በኩል በግንቦት7 ህዝባዊ ሀይል አባላት ላይ ከፍተኛ መነቃቃት የሚፈጥር በሌላ በኩል ደግሞ የተጣለብን ህዝባዊ አደራ ከፍተኛ መሆኑን የሚያስታውሰን ነው ብለዋል። በቅርቡ ከኢትዮጵያ አየር ሀይል ከድተው የሄዱት ሰዎች በጥሩ ሁኔታ እንደሚገኙ የገለጹት ...

Read More »

9.5 ሚልዮን የባለ አንድ እና የባለ አምስት ብሮች የአገልግሎት ጊዜያቸው ከመጠናቀቁ በፊት ከገበያ ውጭ ሆኑ

መስከረም ፳(ሃያ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዩጵያ አቆጣጠር በ2000 ዓ.ም በአውሮፓውያኑ በ2008  ወደ ገበያ የገቡት የባለ አምስት እና ባለ አንድ ብር የመገበያያ ኖቶች ከተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ በታች በሆነ ጊዜ ውስጥ ከገበያ መውጣታቸውን የኢትዩጵያ ንግድ ባንክ ገለጸ፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እንደሚለው ገንዘቦቹ የወደሙት የአገልግሎት ጊዚያቸው አብቅቶ በመቀደዳቸው ፣ በመቆረጣቸው፣  በመንተባቸው ወይም  በመታሸታቸው ነው። ብሮችን የሚቀብሩ እና አሽገው የሚያስቀምጡ እንዳሉ የገለጹት ...

Read More »

አንድነት ፓርቲ በአዲስ አበባ በነጻነት ቅስቀሳ ለማድርግ አልቻለም

መስከረም ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፓርቲው ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ዳንኤል ተፈራ ለኢሳት እንደገለጹት፣ ሊቀመንበሩን ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳን ጨምሮ በርካታ የፓርቲው አመራሮች ቅስቀሳ በማድረግ ላይ እያሉ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ተወስደው ለሰአታት ታግተው አርፍደዋል። ምንም እንኳ የአዲስ አበባ መስተዳደር  በመጪው እሁድ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲያደርግ ለፓርቲው ፈቃድ ቢሰጥም ፣ ፖሊስ በበኩሉ ፓርቲው ቅስቀሳ ለማድረግ ከፈለገ ከሚመለከተው አካል ልዩ ፈቃድ ማምጣት ...

Read More »

በቁጫ ወረዳ ታስረው የነበሩ ሰዎች ተለቀቁ

መስከረም ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከወራት በፊት በቁጫ ወረዳ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ታስረው የነበሩ 40 ሰዎች ተፈቱ። አስተባባሪ ናቸው በሚል የታሰሩት መቶ አለቃ ማሴቦ ማዳልጮ ግን ሳይፈቱ ቀርተዋል። ሰዎቹ ከ3 ወራት በፊት ፍርድ ቤት እንዲፈቱ ውሳኔ ቢያስተላልፍም ፖሊስ በራሱ ስልጣን አልፈታም ብሎ መቆየቱን በተደጋጋሚ መዘገባችን ይታወሳል። ይሁን እንጅ እስረኞቹ በትናንትው እለት ተለቀው ከቤተሰቦቻቸው ጋር መገናኘታቸውን የደረሰን መረጃ አመልክታል። ...

Read More »

ከባድ የጦር መሳሪያዎችን የተሸከሙ መኪኖች ወደ ሰሜን ማቅናታቸው ተዘገበ

መስከረም ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አይን እማኞች እንደገለጹት ባለፉት 3 ቀናት ከ30 በላይ የሚሆኑ ታንኮችን እና የጦር መሳሪያዎችን የጫኑ ከባድ ተሽከርካሪዎች ወደ ትግራይ ሰሜናዊ ክፍል አቅንተዋል። መንግስት የጦር መሳሪያዎችን ለማንቀሳቀስ ለምን እንደፈለገ የታወቀ ነገር የለም። አንዳንድ ወገኖች እንደሚገምቱት በትግራይ አንዳንድ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ አማጽያን የሚፈጥሩትን ስጋት ለመቋቋም ተብሎ የተወሰደ እርምጃ ሊሆን ይችላል። በጉዳዩ ዙሪያ የመንግስት ባለስልጣናትን ለመነጋገር ያደረግነው ሙከራ ...

Read More »