ጥቅምት ፳(ሃያ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የጥሬ ቆዳና ሌጦ ኤክስፖርት ባለፉት አምስት ዓመታት የተሻለ ገቢ ያስገኘ ቢሆንም ግብይቱ ኃላቀር፣ሰንሰለቱ የተንዛዛና ከፍተኛ የግብይት ወጪዎች የሚታዩበት እንዲሁም በምርት ጥራት በኣለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪነቱ እጅግ አነስተኛ መሆኑን ከንግድ ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ አመለከተ፡፡ የጥሬ ቆዳና ሌጦ ኤክስፖርትን በማቆም እሴት የተጨመረባቸውን የተለያዩ የቆዳ ውጤቶች ለውጪ ገበያ በመላክ የተሻለ የውጪ ምንዛሪ ለማስገኘት ጥረት እየተደረገ መሆኑን ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ወደ አዲስ አበባ የሚጎርፉ አረጋውያን ለማኞች ቁጥር ጨምሯል
ጥቅምት ፳(ሃያ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የከተማዋ ነዋሪዎች እንደሚሉት በልመና የሚተዳደሩ አረጋውያን ቁጥር ከመቼውም ጊዜ በላይ ጨምሯል። አረጋውያኑም ከክልል ከተሞች ወደ አዲስ አበባ እንደሚጎርፉ ነዋሪዎች ይናገራሉ። መንግስት የገጽታ ግንባታ በሚል አረጋውያንን ሰብስቦ ወደ ክልል ቢበትናቸውም፣ አረጋውያኑ ተመልሰው በምጣት በልመናው ቀጥለዋል። አንድ ነዋሪ እንዳሉት ቀድሞ ” አብያተ ክርስቲያናት ቅጥር ግቢ ውስጥ አይለመንም ነበር፣ አሁን ግን ልመናው ቤተክርስቲያን ውስጥ ሁሉ ሆኗል፣ ...
Read More »የስኳር ህመምተኞች መድሀኒት የለም ተባሉ
ጥቅምት ፳(ሃያ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በዘውዲቱ ሆስቲታል መድሀኒቱን ለመቀበል ከሳምንታት በላይ ሲጠባበቁ የነበሩ የስኳር ህመምተኞች በመጨረሻ መድሀኒት የለም መባላቸውን ለኢሳት ገልጸዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሚሰጠው እርዳታ መቋረጥ ለችግሩ መፈጠር ምክንያት ነው ቢባልም፣ አንዳንድ ወገኖች ደግሞ የችግሩ ምንጭ መድሀኒቱ አየር ባየር ስለሚሸጥ ነው ብለዋል። ህመምተኞች እንደሚሉት መድሀኒቱን በግላቸው ገዝተው ለመጠቀም ዋጋው የሚቀመስ አይደለም። ብዙዎቹ መድሀኒቱን ለማግኘት ባለመቻላቸው ህይወታቸው አደጋ ላይ ...
Read More »ኢትዮጵያዊቷን የማደጎ ልጅ በርሀብ የገደለችው አሜሪካዊት በ37 አመታት እስራት ተቀጣች
ጥቅምት ፳(ሃያ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የ42 አመቷ ካሪ ዊሊያምስ የ13 አመቷን ታዳጊ ሐና ዊሊያምስን በረሀብና በብርድ በመቅጣት ህይወቷ እንዲያልፍ ማድረጓን ፍርድ ቤቱ አረጋግጧል። የገዳዩዋ ባለቤት በ28 አመታት እንዲታሰር ተፈርዶበታል። ሌላው የ10 አመቱ የማደጎ ታዳጊ ኢትዮጵያዊም ለሌሎች አሳዳጊዎች እንዲሰጥ ተደርጓል። ፍርዱን የሰጡት ዳኛ ከፍተኛ የሚባለው ቅጣት ማስተላላፋቸውን ተናግረዋል። ሁለቱም ሰዎች ከሁለት አመታት በፊት መታሰራቸው ይታወሳል።
Read More »የቦሌ ሩፋኤል ቤተክርስቲያን የድረሱልኝ ጥሪ አሰማች
ጥቅምት ፲፱(አስራ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የቦሌ ለሚ ቅ/ሩፋኤል የጻዲቁ አቡነ ኤዎስጣቲዎስ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ የሆኑት መልአከ ብርሀን ተከስተ ካሳሁን “የድረሱልን ጥሪን ይመለከታል” በሚል ርእስ ለለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የብጹዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ ረዳትና የጅማ ሀገረ ሰብከት ሊቀ ጳጳስ ለሆኑት ለ ብጹዕ አቡነ እስጢፋኖስ በጻፉት ደብዳቤ ላይ፣ የመንግስት ባለስልጣናት ቤተክርስቲያኑዋን በ7 ቀናት እንዲያፈርሱ እንዳዘዙዋቸው ተናግረዋል። ደብዳቤው ” ቤተከርስቲያኑ ከተመሰረተ ...
Read More »በሁለት አመታት ብቻ ከ400 ሺ በላይ ዜጎች በህገ ወጥ መንገድ ተሰደዋል
ጥቅምት ፲፱(አስራ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ባለፉት 2 ዓመታት ብቻ ከ400 ሺ በላይ ዜጎች ሲሆን፣ በህጋዊ መንገድ የተጓዙትን ሲጨምር አሀዙ በእጥፍ ሊጨምር ይችላል። መንግስት በቅርቡ ለስራ በሚል ወደ ውጪ በሚጓዙት ላይ እገዳ መጣሉ ይታወቃል። የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የስራ ስምሪት ማስፋፊያ ዳይሬክተር አቶ አበበ ሀይሌ እንዳሉት ፥ እገዳው ከተጣለባቸው ሀገራት መካከል ...
Read More »መምህራንን ለመቆጣጠር መንግስት አዲስ አደረጃጀት ተግባራዊ አደረገ
ጥቅምት ፲፱(አስራ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መምህራን ለኢሳት እንደገለጹት አደረጃጀቱ ተግባራዊ በሆነባቸው በጎንደር በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የኢህአዴግ አባላት ከሆኑ ከመምህራን አንድ፣ ከተማሪዎች አንድ ከፖሊስ አንድ እንዲሁም ከወላጆች አንድ በትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚገኙ መምህራንን የቀን ተቀን እንቅስቃሴ፣ ፖለቲካ አመለካከት እና ሌሎችንም ተያያዥ ጉዳዮች ይከታተላሉ። መመሪያው በሁሉም ትምህርት ቤቶች የወረደ ሲሆን፣ በአብዛኛው ትምህርት ቤቶች የአንድ ለአምስት አደረጃጀቱ ተግባራዊ ሆኗል። ...
Read More »በታች አርማጭ በደዊ ቀበሌ አንድ የጸጥታ ባለሙያ አንዱን ግለሰብ ከእስር ቤት በማውጣት መግደሉ ተሰማ
ጥቅምት ፲፱(አስራ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ለኢሳት ከስፍራው የደረሰው ዘገባ እንዳመለከተው ጋሻው የቆየ የተባለው የጸጥታ አስከባሪ የ28 አመቱን ጎሹ እያዩ የተባለውን አርሶ አደር ከመጠጥ ቤት ውስጥ እንዲወጣ ካደረገ በሁዋላ፣ ወደ እስር ቤት ወስዶታል። በመንግስት የተሾመው ታጣቂ ወጣት የጸጥታ ማስጠበቅ ስራ ለመስራት በሚል ለመስክ ስራ ተልኮ በነበረበት ወቅት ነው ወጣቱን ያለምክንያት ወደ እስር ቤት ካስገባው በሁዋላ፣ ከእስር ቤት አስወጥቶ ...
Read More »የቀድሞው የፌዴራል ቤቶች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር በሙስና ተጠርጥረው ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረቡ።
ጥቅምት ፲፱(አስራ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አቶ ተፈሪ ፍቅሬ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው የፌዴራል ቤቶች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር በመሆን ከ2002 እስከ 2005 ዓመተ ምህረት ያገለገሉት አቶ ተፈሪ ፍቅሬ የፌደራል የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና አቃቢ ህግ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ ወንጀል ችሎት ክስ እንደመሰረተባቸው የዘገበው ፋና ነው። የስነ ምግባርና ፀረሙስና ኮሚሽን አቃቤ ህግ በክሱ ፣ ተከሳሹ ህግ እና አሰራርን ...
Read More »የደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ አስተዳደር ከተማሪዎች አመጽ ጀርባ ኢሳት እና ሌሎች ሀይሎች እንዳሉበት ገለጸ
ጥቅምት ፲፰(አስራ ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ተማሪዎች የርሃብ አድማ በማድረግ ላይ ሲሆኑ ዩኒቨርስቲው ትክክለኛነቱን አረጋግጦዋል፡፡ የተማሪዎች አመጽ የተነሳው መንግስት ለዩኒቨርስቲ ተማሪዎች አዲስ የአለባበስ ፤ የአመጋገብ እና የአምልኮ ስርዓት ህግ ማውጣቱን ተከትሎ ነው። ” ተማሪዎች እምነታችሁ ተው ፣ ማተባችሁን በጥሱ” ተብለናል ይላሉ። በ2004 እና በ2005 ዓም ተማሪዎች ህጉን እንዲተገብሩ ሙከራ ቢደረግም ተማሪዎች ለመቀበል ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ህጉ ሳይተገበር ቀይቷል ሲሉ ...
Read More »