.የኢሳት አማርኛ ዜና

የጋዜጠኛ ኤፍሬምን ህይወት ለማትረፍ የሚደረገው መዋጮ አርኪ አይደለም ተባለ

ጥቅምት ፳፮(ሃያ ስድስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጥቅምት 20 ቀን 2006 ዓ.ም በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የቀረበባቸውን የስም ማጥፋት ክስ ፍ/ቤት ቀርበው ምላሽ ለመስጠት ወደ ሐዋሳ ያመሩት የኢትዮ ምህዳር ጋዜጣ ባልደረቦች ከደረሰባቸው የባጃጅ ተሸከርካሪ አደጋ ጋር በተያያዘ በተለይ ኤፍሬም በየነ ላይ የከፋ ጉዳት መድረሱን ተከትሎ በመዋጮ ህይወቱን ለማትረፍ እየተደረገ ያለው ጥረት እስካሁን ውጤቱ አመርቂ አለመሆኑን አንድ የዕርዳታ አሰባሳቢ ኮምቴ አባል አስታወቀ፡፡ ጋዜጠኛ ኤፍሬም ...

Read More »

ህወሀት በእነ አቶ ስየ ላይ የጀመረውን ዘመቻ ቀጥሎበታል

ጥቅምት ፳፮(ሃያ ስድስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ህወሀት በውስጡ የተነሳበትን መከፋፈል ለማስቀረት በእነ አቶ ስብሀት ነጋ የሚመራው ቡድን የቀድሞ ታጋዮችን በማሰባሰብ ህወሀትን ለማዳን በሚረባረብበት ጊዜ፣ በአቶ ስየ አብርሀ እና ቤተሰቦቻቸው ላይ የተጀመረው ዘመቻ ግን እንደቀጠለ መሆኑ ታውቋል። አቶ ስየ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴያቸው በእጅጉ የተገታ ቢሆንም፣ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ( ኢቲቪ) ” የነቀዙ ሀይሎች” በሚል በእርሳቸውና በአቶ ታምራት ላይኔ ላይ የዶክመንታሪ ፊልም ...

Read More »

ኢትዮጵያ እና ግብጽ በአባይ ጉዳይ ሳይስማሙ ቀሩ

ጥቅምት ፳፮(ሃያ ስድስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሱዳን፣ ኢትዮጵያ እና ግብጽ መካከል በካርቱም የተካሄደው የአንድ ቀን ስብሰባ ያለውጤት ተጠናቋል። በኢትዮጵያና ግብጽ መካከል ልዩነቶች የተፈጠሩ ሲሆን፣ ልዩነቶችን ለማጥበብ ስለሚወሰደው እርምጃም አልተስማሙም። ብዙ ክብደት ተሰጥቶት የነበረው ስብሰባ በአንድ ቀን መጠናቀቁ በሁለቱ አገራት መካካል ያለው ልዩነት እየሰፋ መሄዱን የሚያሳይ ነው ተብሎአል። ምንም እንኳ ከአንድ ወር በሁዋላ አገራቱ ተመልሰው እንደሚገናኙ ቢገለጽም፣ ግብጽ ዬያዘችው ...

Read More »

መሀመድ ሙርሲ የግብጽ ፕሬዳንት ነኝ ሲሉ ተናገሩ

ጥቅምት ፳፮(ሃያ ስድስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከወራት በፊት በግብጽ የተቀሰቀሰን አመጽ ተከትሎ በወታደራዊ ሀይሉ ጣልቃ ገብነት ከስልጣን የተወገዱትና በእስር ላይ የሚገኙት መሀመድ ሙርሲ  በካይሮ ጉዳያቸውን እንዲያስችል በተሰየመው ፍርድ ቤት ቀርበው የግብጽ ፕሬዳንት መሆናቸውን ተናገሩ። ሙርሲ፦የተከሰሱበት መንገድ ህገወጥ መሆኑንና እርሳቸው የግብጽ ህጋዊ ፕሬዳንት ሆነው መቀጠል እንዳለባቸው ነው ለዳኞች የተናገሩት። እንደ ቢቢሲ  ሪፖርት ሙርሲና ሌሎች 14 የሙስሊም ብራ ዘር ሁድ  ...

Read More »

አዲሱ የመከላከያ አዋጅ በአንድ ብሄር የበላይነት ላይ የተመሰረተውን አደረጃጀት አይቀይረውም ተባለ

ጥቅምት ፳፭(ሃያ አምስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የህዝብ ተወካዩች ምክር ቤት የውጭ መከላከያ ደህንነት እንዲሁም የህግ፣ ፍትህ እና የአስተዳደር ጉዳዩች ቋሚ ኮሜቴዎች አባላት ሰሞኑን እንዲወያዩበት በተደረገው የመከላከያ አዋጅ 98 በመቶ የሚሆኑት ወታደራዊ አዛዦች ከአንድ ብሄር የሆኑበትን አወቃቀር እንደማይለውጠው ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው መኮንኖች ተናግረዋል: የመከላከያ ሚኒስቴር ሹሞች በበኩላቸው አዋጁ እስከ ዛሬ የነበሩትን ህጎች ሁሉ የሚለውጥና መከላከያን የሚያሳድግ ነው ይላሉ። ከማእረግ ...

Read More »

በአማራ ክልል ቴሌቪዥን ጋዜጠኞች እና አመራሮች መካከል መተማመን እንደሌለ ጋዜጠኞች ተናገሩ

ጥቅምት ፳፭(ሃያ አምስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአማራ ክልል ጋዜጠኞች እና በፖለቲካ ታማኝነት ተሹመው በሚያገለግሉ መሪዎች መካከል መተማመን የለም ሲሉ ጋዜጠኞች ለኢሳት ተናግረዋል፡፡ በጋዜጠኞች እና በአመራሩ መካከል ለተፈጠረው ልዩነት በርካታ ምክንያቶች ቀርበዋል። ጋዜጠኞቹ ለክልሉ ቴሌቪዥን ስርጭት ልዩ ምልክት ወይም ሎጎ ሁኖ እንዲያገለግል የተመረጠው የሰማእታት ሃውልት አርማ የአማራን ህዝብ የሚወክል አይደለም በማለት ተቃውሞ እያሰሙ ነው፡፡ በአመራሮች በኩል በሚታየው ከባድ የሙስና ...

Read More »

በኢህአዴግ ላይ እምነት እያጣ የመጣውን እና ተቃውሞውን በመግለጽ ላይ ያለውን አርሶ አደር ለማፈን አዲስ የስልጠና መርህ ተግባራዊ እየተደረገ ነው፡፡

ጥቅምት ፳፭(ሃያ አምስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመላው ኢትዩጵያ ተግባራዊ እንዲደረግ በኢህአዴግ ጽ/ቤት በኩል ለ14 ቀናት የሚቆይ ሰልጠና ተቀርጾ ወደ ታች በመውረድ ተግባራዊ እየተደረገ ነው፡፡ ቅድሚያ እንዲያስተገብር ትዕዛዝ የተላለፈለት የአማራ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች ለሚገኙ አርሶ አደሮች ስልጠናውን እየሰጠ ነው። ስልጠናው የኢትዩጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ  ወይም ኢህአዴግ የተጋድሎ ታሪክ  ላይ የሚያተኩር ሲሆን አርሶ አደሮች በኢህአዴግ ላይ ተቃውሞ እያሰሙ በመምጣታቸው ስልጠና ...

Read More »

በግንባታ እቃዎች ላይ የሚታየው የዋጋ ንረት ዘረፉን እየጎዳው ነው

ጥቅምት ፳፭(ሃያ አምስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በ ግንባታ ዘርፍ በየጊዜው እየናረ የመጣው የግብአቶች ዋጋ ንረት በተለይ በብድር የሚሰሩ በርካታ ግንባታዎችን እያስተጓጎለ እንደሚገኝ ታውቋል። ከመንገዶች ባለስልጣን የተገኘ መረጃ እንዳመለከተው የግንባታ ግብአቶች ዋጋ ባለፉት አምስት ዓመታት ብቻ ከ100 እስከ 237 በመቶ የዋጋ ንረት አሳይቶአል፡፡ መረጃው እንደአብነት ከዘረዘራቸው ግብአቶች መካከል ነዳጅ እ.ኤ.አ በ2009 ዓ.ም በሊትር 7.13 ብር የነበረው እ.ኤ.አ በ2013 ወደ 16.91 ብር ...

Read More »

ኦህዴድ በግምገማ እየተናጠ ነው

ጥቅምት ፳፪(ሃያ ሁለት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ኦህዴድ ከወረዳ ጀምሮ ያሉ አባላቱን እየገመገ ሲሆን፣ ግምገማው በእርስ በርስ ሽኩቻና መጠላላፍ እየተካሄደ ነው። ከድርጅቱ አመራሮች መካከል አንዱ ለኢሳት እንደገለጹት ድርጅቱ ህልውና አደጋ ውስጥ ወድቋል።የዝምድና አሰራር እንዲሁም በቡድን ተደራጅቶ አንዱ ሌላውን የሚያጠቃበት ሁኔታ በሰሞኑ ግምገማ በስፋት የታየ ሲሆን፣ አብዛኛው ከታች እስከ ላይ ያለው አመራር በሙስና የተዘፈቀ በመሆኑ አንዱ ...

Read More »

በአቶ መለስ ሞት የውጭ ምንዛሬ እጥረት ተፈጥሮ እንደነበር አይኤም ኤፍ ገለጸ

ጥቅምት ፳፪(ሃያ ሁለት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አለማቀፉ የገንዘብ ተቋም ባወጣው የ2004-2005 ግምገማ ኢትዮጵያ ድህነትን ለመቅረፍ የምታደርገውን ጥረት አድንቋል። በኢኮኖሚው ረገድ ስኬት እየታየ መሆኑን፣ አገሪቱም የ7 በመቶ እድገት ማስመዝገቡዋን የገለጸው አይ ኤም ኤፍ፣ የዋጋ ግሽበትን ለመቆጣጠር መንግስት የወሰደውን እርምጃንም አድንቋል። የአቶ መለስ ሞት በፈጠረው መደናገጥ ሁሉም የውጭ ምንዛሬ ለመግዛት መገደዱን በዚህም ሳቢያ የተፈጠረው የምንዛሬ እጥረት ተጽኖ መፍጠሩን ገልጿል። የግሉ ...

Read More »