.የኢሳት አማርኛ ዜና

በቦንጋ መምህራን አድማ ሊጠሩ ነው

ህዳር ፳፯(ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በከፋ ዞን በቦንጋ ከተማ የሚገኙ መምህራን ፣ መንግስት ለአባይ ግድብ በማለት ያለፈቃዳቸው የቆረጠባቸውን ደሞዝ በአስቸኳይ ካልመለሰ ሰኞ የስራ ማቆም አድማ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል። መምህራኑ ዛሬ ወርሀዊ ደሞዛቸውን ለመቀበል ወደ ባንክ ሲሄዱ ለአባይ ግድብ በሚል ደሞዛቸው ተቆርጦ ተሰጥቷቸዋል። በሁኔታው የተበሳጩት መምህራን ወደ ትምህርት ጽህፈት ቤት ሲያመሩ መስተዳድሩ ያዘዘው በመሆኑ ምንም ማድረግ አንችልም የሚል መልስ ተሰጥቷቸዋል። ...

Read More »

በ2006 ዓ.ም ከስድስት ሚልየን በላይ ህፃናት ትምህርት አቋረጡ

ህዳር ፳፯(ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅድመ መደበኛ ት/ቤት ገብተው መማር ከሚገባቸው እድሜያቸው ለትምህርት ከደረሱ ሀፃናት ውስጥ 23 በመቶዎቹ ወደ ትምህርት ቤት አለመምጣታቸውን ከትምህርት ሚኒስቴር የተገኘው ሰነድ ያስረዳል። ከ1ኛ አስከ 4ኛ ክፍል ድረስ የትምህርት ገበታቸው ላይ የተገኙ ተማሪዎች ቁጥር አነስተኛ መሆኑን የሚያሳያየው ሰነዱ፣ከ5ኛ አስከ 8ኛ ክፍል ድረስ ገብተው መማር የነበረባቸው ተማሪዎች   ቁጥር አነስተኛ መሆኑንም  ያመለክታል ፡፡ በዚህ ዓመት መድረስ ...

Read More »

ከሳውድ አረቢያ ከሚመለሱ ኢትዮጵያውያን ጋር በተያያዘ የመንግስት እንቅስቃሴ እየተተቸ ነው

ህዳር ፳፮(ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የመኖሪያና የስራ ፈቃድ የላችሁም በሚል ከሳዑዲዓረቢያ ወደ አገራቸው የሚመለሱ ኢትዮጵያዊያን ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ሲሆን ቁጥሩ መንግስት አስቀድሞ ካሰበው እጅግ አሻቅቧል፡፡ በዚህ ም ምክንያት ተመላሾቹን ለመቀበልና ለማቋቋም  መንግስት በቂ በጀት አለመያዙ እንደ አገር አሳፋሪ መሆኑን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገልጸዋል፡፡ መንግስት የተመላሾቹ ቁጥር 23 ሺ ገደማ መሆኑንና እነዚህም ወገኖች ለመመለስ መመዝገባቸውን በመግለጽ ለተመላሾቹ ...

Read More »

ጅጅጋ በከፍተኛ ወታደራዊ ጥበቃ ስር ናት

ህዳር ፳፮(ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-8ኛውን የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ለማክበር በሚል የጅጅጋ ከተማ በፌደራል ፖሊስ  አባላት መወረሯን ነዋሪዎች ገልጸዋል። የፌደራል ፖሊስ አባላት ከተማውን ከተቆጣጠሩት በሁዋላ ልዩ ፖሊስ እየተባሉ የሚጠሩት ሀይሎችን ወደ ዳር የገፉዋቸው ሲሆን፣ ፖሊሶቹ በየተወሰኑ ሜትሮች ቁጥጥር እያደረጉ ነው። የጸጥታ ጥበቃው በሄሊኮፕተር ላይ በሚደረግ ቅኝት የታጀበ ሲሆን፣ በየ አቅጣጫውም በዙ 23 እና በሌሎች ከባድ መሳሪያዎች ጥበቃ እየተደረገ ...

Read More »

የመርካቶ ነጋዴዎች በእሳት አደጋ ሰራተኞች ላይ ክስ ሊመሰርቱ ነው

ህዳር ፳፮(ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመርካቶ በተለምዶ ጆንያ ተራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ትላንት ከቀትር በኃላ የደረሰውን የእሳት አደጋ በወቅቱ ከመቆጣጠር ይልቅ ጉቦ ለማግኘት የእሳት አደጋ ሰራተኞች በድርድር ጊዜ በማጥፋታቸው ንብረታችንን እንድናጣ አድርጎናል ያሉ ነጋዴዎች የአዲስአበባ ከተማ እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ኤጀንሲን ለመክሰስ መወሰናቸውን አስታወቁ፡፡ ከተጎጂ ነጋዴዎች መካከል አንዱ የሆኑት ለአዲስ አበባው ዘጋቢ እንደተናገሩት እሳት አደጋው በግምት ከቀኑ ...

Read More »

መንግስት ለቀድሞ የኢትዮጵያ የጦር ሰራዊት አባላት የጡረታ መብታቸውን ለማስከበር እንቅስቃሴ መጀመሩ ታወቀ

ህዳር ፳፮(ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ አገሪቱን እንደተቆጣጠረ ተሀድሶ አልወሰዱም በሚሉና በተለያዩ ሰበቦች የጡረታ መብታቸው ላልተከበረላቸው የቀድሞ የኢትዮጵያ ጦር ሰራዊት አባላት፣ የጡረታ መብታቸውን ለማስከበር መንግስት ጥሪ ማቅረቡ ታውቋል። የመንግስት ሹሞች የቀድሞ ወተዳሮቹን  ፎርም እንዲሞሉ እያደረጉዋቸው መሆኑን አንዳንድ ወታደሮች ለኢሳት ገልጸዋል። መንግስት በአሁኑ ጊዜ ይህን እርምጃ ለምን ለመውሰድ እንደፈለገ አልታወቀም። ለጉዳዩ  ቅርበት ያላቸው ሰዎች በኤርትራ የሚንቀሳቀሱ የተቃዋሚ  ሀይሎች የፈጠሩት ...

Read More »

በላይ አርማጭሆ ትክል ድንጋይ ወረዳ አንድ አውቶቡስ ተገልብጦ የ6 ሰዎች ህይወት አለፈ

ህዳር ፳፮(ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአካባቢው ምንጮች እንደገለጹት በአደጋው 40 ሰዎች የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል። የአደጋው መንስኤም ከአቅም በላይ ጭነት መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል። በጭልጋ ወረዳ ደግሞ አንድ ነዳጅ የጫነ ቦቴ መኪና ተገልብጦ ተሽከርካሪዎች ለመተላላፍ ባለማቻላቸው መቸገራቸውን ለማወቅ ተችሎአል። መኪናው ነዳጅ እንደጫነ በመገልበጡ እሳት ይፈጠራል የሚል ስጋት ማሳደሩን የአካባቢው ሰዎች ግልጸዋል።

Read More »

ሳውድ አረቢያ የውጭ ዜጎችን ማስወጣቱዋን እንደምትቀጥል አስታወቀች

ህዳር ፳፭(ሃያ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ካለፈው ወር ጀምሮ ህጋዊ ወረቀት የላቸውም በሚል የውጭ ዜጎችን ማባረር የቀጠለችው ሳውድ አረቢያ፣ ከአለማቀፍ የሰብአዊ መብቶች ድርጅት ትችት ቢደርስባትም፣ ዜጎችን ማስወጣት እንደምትቀጥል አስታውቃለች። አረብ ኒውስ እስካሁን በተወሰደው እርምጃ 126 ሺ ሰዎች ከአገሪቱ መውጣታቸውን ገልጿል። የኢትዮጵያ መንግስት በበኩሉ 90 ሺ ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው መግባታቸውን ገልጸዋል። አረብ ኒውስ አንድ ባለስልጣንን ጠቅሶ እንደዘገበው ውጭ ዜጎችን የማስወጣት ...

Read More »

በኢትዮጵያ የሚታየው የግብር አሰባሰብና ሙስና ህዝቡን እያስመረረ ነው

ህዳር ፳፭(ሃያ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ በደብረማርቆስ ከተማ ተደርጎ በነበረው የህዝብ ስብሰባ ላይ ነርካታ ነጋዴዎች በታክስ መማረራቸውን ገልጸዋል። መቶ አለቃ ስመኝ መኩሪያው እንዳሉት መንግስትን አክብረን በቫት ብንገባም በአንድ አነስተኛ የንግድ ሱቅ በየወሩ እስከ 73 ሺ ብር ተጠይቀን ፤ መንቀሳቀስ አልቻልንም የምንነግደውን ሊወርሰን የሚሽከረከረው መንግስት  ሚዛኑ የሚጥልብን ግብር አስመርሮናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ “የምንሰራውን ስራ በማቋረጥ አሰረክበን እንድንቀመጥ አሰገድዶናል ፣ ሃገራችንን ...

Read More »

በመርካቶ በደረሰ ቃጠሎ መጠኑ ያልታወቀ ንብረት ወደመ

ህዳር ፳፭(ሃያ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቦንብ ተራና እና ጆንያ ተራ የሚባሉት አካባቢዎች ዛሬ ቀን ላይ በከፍተኛ የእሳት አደጋ የተጠቁ ሲሆን የከተማዋ የእሳት አደጋ በጊዜው ባለመድረሱም በነዋሪዎች ከፍኛ ተወቅሷል። የመስተዳድሩ የእሳትና ድንገተኛ አደጋ የህዝብ ግኑኝነት ሰራተኛ አቶ ንጋቱ ማሞ በ10 ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን ተናግረው ጥሪው የደረሳቸው አደጋው ከደረሰ ከ45 ደቂቃ በሁዋላ መሆኑን ተናግረዋል። አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች እንደሚሉት ግን ...

Read More »