ታህሳስ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሰንደቅ ጋዜጣ አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ የመሩትን ስብሰባ በዝርዝር ያቀረበ ሲሆን፣ ከጋዜጣው ለመረዳት እንደተቻለው ሰራተኛው በሚያነሳቸው ቅሬታዎችና መንግስት በሰጣቸው መልሶች መካከል ከፍተና ክፍተት አለ። የሰራተኞቹ ተወካዮች የሰራተኛው የመደራጀት መብት እንዳልተከበረና ሕገ-መንግስታዊ መብታቸው እንደሚጣስ ገልጸዋል። የሰራተኛው የመደራጀት መብት ሲጣስም በመንግስት በኩል አርኪ ምላሽ አይሰጥም ብለዋል። ተወካዮቹ የኑሮ ውድነቱን መቋቋም ባለመቻላቸው መንግስት ድጎማ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የመንግስት የፕሬስ ተቋማት የግል መጽሄቶችን በጽንፈኝነት ፈረጁ
ታህሳስ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መንግስታዊዎቹ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እና በሕግ በፈረሰ ድርጅት ስም የሚጠቀመው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በጋራ አስጠንተነዋል ባሉት ጥናት መሰረት በአገር ውስጥ ከሚታሙት መጽሄቶች መካከል አዲስ ጉዳይ፣ፋክት፣ሎሚ፣ቆንጆ፣ጃና፣እንቁ እና ሊያ የተባሉ መጽሔቶች ጽንፈኛ ፖለቲካ አራማጆች መሆናቸውን አረጋግጠናል ብለዋል። አዲስዘመን ጋዜጣ በረቡዕ ታህሳስ 30 ቀን 2006 ዕትሙ መጽሔቶቹ በብዙ ባህርያቸው የጽንፈኛ ፖለቲካ ፓርቲ ልሳናት ...
Read More »በቦረናና በቡርጂዎች መካከል የተነሳውን ግጭት ለማብረድ የመንግስት ባለስልጣናት መንቀሳቀሳቸው ተሰማ
ታህሳስ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ወደ አካባቢው በማቅናት ለችግሩ እልባት ለመስጠት ጥረት እያደረጉ ነው። ይህንንም ተከትሎ በዛሬው እለት አንጻራዊ ሰላም መስፈኑን ነዋሪዎች ተናግረዋል። አካባቢያቸውን ጥለው የወጡት የቡርጂ ተወላጆች ሙሉ በሙሉ ወደ ቀያቸው ባይመለሱም ፣ እስከ ትናንት የነበረው ግጭት በዛሬው እለት መብረዱን ነዋሪዎች ተናግረዋል። የዞኑ ባለስልጣናት ሆን ብለው አስነስተውታል ...
Read More »ተስፋ የተጣለበት የደቡብ ሱዳን የሰላም ስምምነት አደጋ ውስጥ መውደቁ ተሰማ
ታህሳስ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን አዲስ አበባ ውስጥ ተካሂዶ የነበረው የሰላም ድርድር ውጤት ሊያመጣ ይችላል ተብሎ ተገምቶ የነበረ ቢሆንም ፣ የመንግስት ሀይሎች ቤንቲዩ እየተባለች የምትጠራውን የነዳጅ ዘይት የሚገኝበትን ቦታ ለመቆጣጠር ጥቃት መጀመራቸው በሰላም ስምምነቱ ላይ ያለው ተስፋ እንዲጨልም አድርጎታል። የፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ተቀናቃኝ የሆኑት ሪክ ማቻር ደጋፊዎች ካልተፈቱ የሰላም ስምምነት ለመፈራረም እንደሚቸገሩ አማጺያኑ ቢገልጹም መንግስት ግን ...
Read More »በኢትዮጵያ የአደገኛ እጾች ተጠቃሚ ቁጥር በአስደንጋጭ ሁኔታ እየጨመረ ነው ተባለ
ታህሳስ ፳፰( ሃያ ስምንት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የአደገኛ እጾች ተጠቃሚ ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ተከትሎ በህጻናት እና በሴቶች ላይ የሚደረሰውም ጉዳት ጨምሯል። የተወካዮች ምክር ቤት በቅርቡ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል አሰፋ አብዩ ለተወካዮች ምክር ቤት ያቀረቡትን ሪፖርት ሰንደቅ ጋዜጣ በስፋት ዘግቦታል። በኢትዮጵያ በሶስት አመታት ውስጥ ብቻ 543 ሺ 439 ኪሎ ግራም ወይም 5 ሺ ...
Read More »የአቶ አያሌው ጎበዜ ስልጣን መልቀቅ ከድንበር ጋር የተያያዘ ነው ብሎ የአማራ ክልል ህዝብ እንደሚያስብ መንግስት ያስጠናው ጥናት አመለከተ
ታህሳስ ፳፰( ሃያ ስምንት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የመንግስት ኮሚኒኬሺን ጉዳዮች የህዝብ አስተያየት መረጃ ክፍል በቅርቡ ከስልጣናቸው በወረዱት አቶ አያሌው ጎበዜ እና አሁን በአስቸኳይ ጉባኤ በተተኩት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ላይ ባሰባሰበው የህዝብ አስተያየት እና ለመንግስት ባቀረበው የአሉታ እና አውንታ ትንታኔ እንደገለፀው የስልጣን መተካካቱ ዋና አላማ መንግስት በትግራይ እና በአማራ ክልሎች መካከል ያለውን የድንበር ውዝግብ ለማሳካት ይረዳው ዘንድ ያደረገው ነው ...
Read More »በደቡብ ሱዳን የሚካሄደው ጦርነት እንደቀጠለ ነው
ታህሳስ ፳፰( ሃያ ስምንት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የመንግስትና የተቃዋሚ ደጋፊዎች በአዲስ አበባ ለድርድር ቢገኙም ቦር እየተባለ በሚጠራው አካባቢ አሁንም ከፍተኛ ጦርነት እየተካሄደ መሆኑን የሚደረሱን መረጃዎች ያመለክታሉ። ሰሞኑን በተቀሰቀሰው ጦርነት ኢትዮጵያን እንደተገደሉ የሚደረሱን መረጃዎች ያመለክታሉ። ሁለቱን ተፋላሚ ሀይሎች ፊት ለፊት በማገናኘት ጦርነቱ እልባት ያገኛል የሚል ተስፋ ቢያዝም እስካሁን ድረስ በተጨባጭ የታየ ነገር የለም። በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በሚገኙበት በዋና ከተማው ...
Read More »እስራኤል ውስጥ የሚገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ አፍሪካውያን የተቃውሞ ሰልፍ እያደረጉ ነው
ታህሳስ ፳፰( ሃያ ስምንት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ካለፉት ሶስት ቀናት ጀምሮ የስራ ማቆም አድማ እና የተቃውሞ ሰልፍ በማድረግ ላይ የሚገኙት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩት አፍሪካውያን የእስራኤል መንግስት ያወጣውን አዲስ ህግ እንዲቀይር፣ የታሰሩት እስረኞች እንዲፈቱ እንዲሁም የስደተኞች ጉዳይ በጅምላ ከሚታይ ይልቅ በግለሰብ ደረጃ ታይቶ ውሳኔ እንዲሰጥበት የሚሉት እንደሚገኙበት በሰልፉ ላይ ተገኝቶ የነበረው አቶ አቦየ አስምረው ለኢሳት ገልጸዋል። “በሰላማዊ ሰልፍ ውጤት ...
Read More »በሞያሌ ከተማ የኦነግ ታጣቂዎች የፈጸሙትን ጥቃት ተከትሎ ከተማዋ በመከላከያ ሰራዊት ስትታመስ ዋለች
ታህሳስ ፳፭( ሃያ አምስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ረቡእ ታጣቂዎቹ ከቀኑ 10 ሰአት ገደማ ወደ ከተማዋ በመግባት 3 ጠባቂዎችን በመግደልና አንደኛውን ታጣቂ መሳሪያውን በመቀማትና ልብሱን በማስወለቅ ” ሂድና ለአለቆችህ ንገር” በማለት ጉዳት ሳያደርሱበት መልቀቃቸውን የከተማዋ ነዋሪዎች ገልጸዋል። ታጣቂዎቹ አንድ ድግን መትረጊስ፣ አንድ ላውንቸርና አንድ ባዙቃ ማርከው ወስደዋል። ይህንን ተከትሎ በአካባቢው የደረሱት የመከላከያ ሰራዊት አባላት አንዳንድ የከተማ ነዋሪዎችን እየደበደቡ ...
Read More »ኢህአዴግ በመንግስት ወጪ ለመጪው ዓመት ምርጫ ሕዝብ የማደራጀትና የመቀስቀስ ስራ ጀመረ
ታህሳስ ፳፭( ሃያ አምስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ ከ2007 አገር አቀፍ ምርጫ ጋር በተያያዘ በተለይ በአዲስአበባ ከተማ ሕዝብ ቅሬታ የሚያቀርብባቸውን የመልካም አስተዳደር፣ የሙስናና የልማት ችግሮችን ለመፍታት ከፍተኛ በጀት መድቦ እየተንቀሳቀሰ ነው። የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር የ2006-2007 ዕቅድ አካል እንዲሆን በተደረገው ይህ ከመጪው ዓመት ምርጫ ጋር በቀጥታ የተያያዘው ዘመቻን በብቃት እንዲያስፈጽሙ ለክፍለከተማና ወረዳ አመራሮች ግልጽ መመሪያ ከመተላለፉም ባሻገር በአቅም ግንባታ ...
Read More »