ጥር ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በዛሬው የሰደቃ እና ዱአ መርሀ ግብር በተለያዩ የአገሪቱ ክፍል በብዙ ሺ የሚቆጠሩ የሚገኙ ሙስሊሞች በእስር ላይ የሚገኙ የመፍትሄ አፈላላጊ የኮሚቴ አባላትን አስበው ውለዋል። እጆቻቸውን ወደ ላይ በማንሳትም ለፈጣሪያቸው ተመጽኖ አቅርበዋል። በአዲስ አበባ በታላቁ አንዋር መስጊድ በመቶሺዎች የሚቆጠር ህዝብ ተገኝቶ ድዋ አድርጓል። መንግስት የሙስሊሙን እንቅስቃሴ ተቆጣጥሬዋለሁ በማለት መግለጫዎችን ሲሰጥ ቆይቷል። የተለያዩ ፊልሞችን በመስራትም ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ከቁጫ ችግር ጋር በተያያዘ በአርባምንጭ እስር ቤት የታሰሩ የ232 ሰዎች ስም ዝርዝር ታወቀ
ጥር ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከማንነት፣ ከልማትና መልካም አስተዳዳር ጋር በተያያዘ በአርባምንጭ እስር ቤት የታሰሩ የ232 የቁጫ ወረዳ ነዋሪዎች ስም ዝርዝር የወጣው ከራሳቸው ከእስረኞች ነው። ለኢሳት ከተላከው ስም ዝርዝር ለመረዳት እንደተቻለው አብዛኞቹ እስረኞች አርሶ አደሮች ቢሆኑም፣ 5 የሃይማኖት አባቶች፣ 7 መምህራን፣ 6 ነጋዴዎች፣ 25 ተማሪዎች፣ 22 በልዩ ልዩ የመንግስት ስራ ላይ የሚገኙ፣ 5 መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ...
Read More »በይርጋጨፌ መምህራን ለሁለተኛ ጊዜ የስራ ማቆም አድማ አደረጉ
ጥር ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለአባይ ግድብ ማሰሪያ በሚል ያለፍላጎታቸው ደሞዛቸው የተቆረጠባቸው የይርጋ ጨፌ ሁለተኛ ደረጃ መምራህራን ከወር በፊት የስራ ማቆም አድማ ማድረጋቸውን ተከትሎ ፣ የተቆረጠባቸው ደምዞ ተመልሶ እንደሚሰጣቸው ቃል ተገብቶላቸው የነበረ ቢሆንም፣ የወረዳው አስተዳዳሪ ገንዘቡ በዝግ አካውንት የገባ በመሆኑ፣ ገንዘብ ለመክፈል አንችልም በሚል ምላሽ መስጠታቸውን ተከትሎ መምህራኑ ከትናንት ጀምሮ የስራ ማቆም አድማ አድረገዋል። አድማው ዛሬም ...
Read More »የአዲስ አበባ መስተዳደር 285 የተለያዩ መኪኖችን ለሰራተኞቹ ገዛ
ጥር ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መስተዳድሩ መኪኖችን የገዛው በተለያዩ የሃላፊነት ደረጃ ላይ ለሚገኙት ሰራተኞቹ ነው። ከተገዙት መኪኖች መካከል 18፣ የ2013 ምርት የሆ ኑ ፕራዶ መኪኖች፣ 2 መቶ 40 ባለ ሁለት ጋቢና ማዝዳ ፒክ አፕ፣ 27 ያሪስ ቶዮታ መኪኖች የቢሮ ሃላፊዎች፣ም/ቢሮ ሃላፊዎችና ፣የክፍለ ከተማና ወረዳ አመራሮች እንዲሁም የካቢኔ አባላት እንዲጠቀሙባቸው አየተሰራጩ ነው። መኪኖቹ በጉምሩክ በኩል ከገቡ በኋላ ...
Read More »የሰንደቅ ጋዜጣ አዘጋጆች በማእከላዊ ምርመራ ቀርበው ቃላቸውን ሰጡ
ጥር ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የጋዜጣው አዘጋጆች በማህበራዊ ድረገጾች ላይ በለቀቁት ዜና “በሰንደቅ ጋዜጣ ቁጥር 434 ታህሳስ 23 ቀን 2006 ዓ.ም በወጣው “ጉዲፈቻ፤ በኢ-ሰብአዊነት ላይ የተመሰረተ የኪራይ ሰብሳቢዎች ዋሻ ተንኳኳ” በሚል ርዕስ በገጽ 5 በፖለቲካ ዓምድ ላይ በሰፈረው ጽሁፍ መነሻነት የሴቶች፣ ሕፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስቴር የሰንደቅ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ፍሬው አበበ እና በም/ዋና አዘጋጁ ፋኑኤል ክንፉ ...
Read More »የቁጫ ወረዳ ችግር ተባብሷል ቀጥሎአል
ጥር ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጋሞ ጎፋ ዞን በቁጫ ወረዳ ከመብት ጋር በተያያዘ የሚደርሰው ስቃይ እንደቀጠ ነው። የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት በፖሊሶች ወከባ የተነሳ አንዳንድ ነዋሪዎች ሌሊቱን የሚያሳልፉት ጫካ ውስጥ ነው። ፖሊሶች ሌሊት ቤት እያስከፈቱ እንደሚፈትሹ ነዋሪዎች ይናገራሉ ከአንድ አመት በላይ በዘለቀው የቁጫ ችግር ከ40 በላይ የሚሆኑ የአገር ሽማግሌዎችና ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ ወጣቶችም ታስረው ይገኛሉ። ከሰኔ ወር 2005 ...
Read More »በርካታ የየረር ባሬ ጎሳ አባላት ታሰሩ
ጥር ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሶማሊ ክልል በቀላፎ አካባቢ የሚኖሩ የየረር ባሬ ጎሳ የአገር ሽማግሌዎች ለጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ያስገቡት ደብዳቤ ለኢሳት መድረሱን ተከትሎ የክልሉ ባለስልጣናት ወደ አካባቢው በመንቀሳቀስ በርካታ የአገር ሽማግሌዎችን ማሰራቸው ተሰማ። የአገር ሽምግሌዎቹ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በጻፉት ደብዳቤ የሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንት አብዲ ሙሀመድ ኡመር እና ጄኔራል አብርሀም በቅጽል ስማቸው ኳታር የሚመራው ልዩ ሚሊሺያ እየተባለ የሚጠራው ...
Read More »በቦረናና በቡርጂዎች መካከል የተነሳውን ግጭት ተከትሎ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች አካባቢያቸውን ለቀው ተሰደዱ
ጥር ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ በቦረናና በቡርጂ ማህበረሰብ አባላት መካከል የተነሳውን ግጭት ተከትሎ ከ4 ሺ በላይ ነዋሪዎችም ቀያቸውን ጥለው ከተፈናቀሉ በሁዋላ፣ የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ወደ ቦታው በመሄድ ለማረጋጋት ሙከራ አድርገው የነበረ ቢሆንም፣ ችግሩ እንደገና በመቀስቀሱ ከ1ሺ በላይ የቡርጂ ጎሳ አባላት አካባቢውን ለቀው ወደ ደቡብ ክልል አምርተዋል። ከሜጋ ከተማ ወደ 12 ኪሎሜትሮች ርቀው ከሚገኙት ጎዳቤሮ፣ ባታንጋላዶ ...
Read More »የኢትዮጵያ ጦር በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት የሰላም አስከባሪ ሃይልን ተቀላቀለ
ጥር ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ያለ ህብረቱ እውቅና ከሁለት ዓመታት በፊት ዘምቶ የቆየው 4 ሺ የሚጠጋው የኢትዮጵያ ጦር በመጨረሻም በህብረቱ ስር እንዲሆን ተፈቅዶለታል። የኢትዮጵያ ጦር ሲደመር በሶማሊያ አልሸባብን ለመዋጋት የዘመተው የህብረቱ ጦር 22 ሺ ይደርሳል። የኢትዮጵያ ጦር በደቡብ ምእራብ የሶማሊያ ግዛት ፣ በጌዶ፣ ቤይ እና ባኮል ግዛቶች ይቆያል። የአፍሪካ ህብረት ጦር አልሸባብን ከሞቃዲሾ ቢያስወጣውም፣ ጦሩ ግን ...
Read More »የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከ250 በላይ ሰዎችን አሰረ
ጥር ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኮሚሽኑ ተጠርጣሪዎቹ የተሳሩት በአዲስ አበባ የተለያዩ ክፍለከተሞች በመኪና ስርቆት፣ ማጅራት በመምታትና ሌሎች ወንጀሎች መፈጸማቸውን ጥናት ካካሄድኩ በሁዋላ ነው ብሎአል። ተያዙ የተባሉት ተጠርጣሪዎች ፍድር ቤት ስለመቅረባቸው ኮሚሽኑ ያስታወቀው ነገር የለም። በአዲስ አበባ ውስጥ ከጊዜወደ ጊዜ ሚታየው ስርቆት ነዋሪዎች ማስመረሩን የሚደርሱን መረጃዎች ያመለክታሉ። በከተማዋ ውስጥ ዘመናዊ ስለኮችን በአደባባይ መያዝ፣ ውድ ጌጣጌጦችን አድርጎ መጓዝ ...
Read More »