መጋቢት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ባልተለመደ መልኩ ወጣት የሰማያዊ ሴት አመራሮችና አባላት አለማቀፉን የሴቶች ቀን አስመልክቶ በተዘጋጀ ሩጫ ላይ የመብት ፣ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ፍትህ ጥያቄዎችን በማንሳት መንግስት አፋጣኝ መልስ እንዲሰጥ በተቃውሞ ድምጽ ማቅረባቸውን ተከትሎ በቁጥጥር ስር ውለው ለአምስት ቀናት በእስር ካሳለፉ በሁዋላ ዛሬ በድጋሜ ፍርድ ቤት ቀርበዋል። ፖሊስ በእስረኞቹ ላይ የማደርገው ምርመራ አልተጠናቀቀም ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ህዝቡ ለመለስ ፋውንዴሽን ገንዘብ እንዲያዋጣ እየተገደደ ነው
መጋቢት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢህአዴግ ካድሬዎች በተለይ በአዲስ አበባና በአጎራባች ከተሞች ባሉ ቤቶች እየዞሩ ለመለስ ፋውንዴሽን ማቋቋሚያ ከ50 ብር ጀምሮ እንዲከፍሉ እያስገደዱ ነው። እድሮች በነፍስ ወከፍ ከ8 ሺ ብር ጀምሮ እንዲከፍሉ መመሪያ ተላልፎላቸዋል። በዚህ መመሪያ የተሰላቹና የተበሳጩ ሰዎች “ወዴት እንሂድ” ሲሉ ለኢሳት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። የመለስ ፋውንዴሽን በወ/ሮ አዜብ መስፍን ሊቀመንበርነት የሚመራ ሲሆን የአቶ መለስን አስከሬን በቋሚነት የሚያርፍበትን ...
Read More »በሳውድ አረቢያ አንድ ኢትዮጵያዊት ራሱዋን አጠፋች
መጋቢት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ ከ10 ወራት በላይ የሰራችበትን ደሞዙዋን ባለመስጠታቸው ከአሰሪዎቹዋ ጋር ውዝግብ ውስጥ ገብታ የነበረችው ኢትዮጵያዊት ተማም በሚባል ከተማ በሚገኝ እስር ቤት ውስጥ ልብሷን ቀዳ ራሱዋን በመስቀል ማጥፋቱዋን በእስር ቤት ውስጥ የሚገኙ አንዳንድ እስረኞች ለኢሳት ገልጸዋል። ወርቅነሽ የምትባለዋ ሟች አስከሬን በትናንትናው እለት ምርመራ እንደተደረገበትና ፖሊሶች አስከሬኑን መውሰዳቸው ታውቋል። በዚሁ እስር ቤት ውስጥ አንዲት ወጣት ባለፉት ...
Read More »በምእራብ አርማጮ የሽፍታ ቤተሰቦች ናችሁ በሚል ብዙ ነዋሪዎች ታስረው በመሰቃየት ላይ ናቸው
ማጋቢት ፬ (አራት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮ-ሱዳን ድነበር አካባቢ ነዋሪ የሆኑ የምእራብ አርማጭሆ ነዋሪዎች እና በሽፍታ ቤተሰብነት የተጠረጠሩ ከ20 ያላነሱ ቤተሰቦች ታስረው እንደሚሰቃዩ ከአካባቢው ያገኘነው መረጃ ያሳያል። የሽፍቶቹ ቤተሰቦች ለእስር የሚዳረጉት ሽፍቶችን አሳምነው እጃቸውን ለመንግስት እንዲሰጡ ወይም ገድለው እንዲያቀርቡ ለማድረግ ነው። ይሁን እንጅ አብዛኞቹ ሽፍቶች እጃቸውን ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው በቤተሰቦቻቸው ላይ የሚደርሰው እንግልት እየጨመረ ነው። በእስር ላይ ከሚገኙት ...
Read More »በኢትዮጵያ ህጻናትን በማደጎነት የሚልኩ የውጭ ድርጅቶች ዘመቻ ሊጀምሩ ነው
ማጋቢት ፬ (አራት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በማህበራዊ የመገናኛ ብዙሀን የተለቀቀ አንድ የድምጽ ማስረጃ እንደሚያሳየው ህጻናትን በጉዲፈቻ ስም ወደ ውጭ አገራት የሚልኩ በተለይም የአሜሪካ ድርጅቶች የኢትዮጵያ መንግስት በቅርቡ ያወጣውን ህግ በመቃወም ዘመቻ ሊጀምሩ መሆኑን ውሳኔ ላይ ደርሰዋል። የኤጀንሲው ተወካዮች እንደሚገልጹት፣ መንግስት በቅርቡ የጣለው እገዳ በመገናኛ ብዙሀንና በህዝቡ ተጽእኖ የመጣ ነው። አንዳንድ የመንግስት ባለስልጣናት በቂ ገንዘብ እስከተከፈለ ድረስ የጉዲፈቻ ሂደቱ ...
Read More »በከፍተኛ ወጪ የተገነቡ ከ60 በላይ ቤቶችና ድርጅቶች ይፍረሱ መባሉ ውዝግብ አስነሳ
ማጋቢት ፬ (አራት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በንፋስ ስልከ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፣ ከለቡ አካባቢ ተነስቶ በቱሉ ዲምቱ አድርጎ አዳማ ድረስ ይሠራል በተባለው መንገድ ምክንያት፣ ከ60 የሚበልጡ መኖሪያ ቤቶችና የንግድ ድርጅቶች እንደሚፈርሱ በመገለጹ፣ ነዋሪዎችና ክፍለ ከተማው እየተወዛገቡ መሆናቸውን ሪፖርተር ዘገበ። የመኖሪያ ቤቶችና የንግድ ተቋማትን ለመገንባት ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ1994 ዓ.ም ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት አግኝቶ በ1997 ዓ.ም. የአካባቢውን ...
Read More »ዩክሬን 60 ሺህ ያህል ጠንካራ የመከላከያ ሀይል እንድትገነባ የአገሪቱ ፓርላማ አዋጅ አጸደቀ።
ማጋቢት ፬ (አራት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አዲሱ የመከላከያ አዋጅ ግንባታ የጸደቀው ሩሲያ በአወሳጋቢዋ ክሪሚያ የፊታችን እሁድ ሪፈረንደም ለማካሄድ በተሰናዳችበት ወቅት ነው። ክሪሚያ በአሁኑ ሰዓት በሩሲያ የጦር ሀይል ስር የምትገኝ ሲሆን፣ በመጪው እሁድ በሚካሄደው ሪፈረንደም ነዋሪዎቿ በሩሲያ ስር መተዳደር እንደሚፈልጉና እንደማይፈልጉ ድምፃቸውን ይሰጣሉ። ፕሬሲዳንት ቭላድሚር ፑቲን ፦ በየክሬን በተፈጠረው ቀውስ ሩሲያ ተጠያቂ እንዳልሆነች በተደጋጋሚ እየገለፁ ይገኛሉ። ፑቲን ይህን ቢሉም ...
Read More »በሃረር ከተማ የተከሰተውን የእሳት አደጋ ተከትሎ ግጭት ሊነሳ ይችላል የሚል ስጋት መኖሩን ነዋሪዎች ተናገሩ
ማጋቢት ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የተለያዩ የከተማዋ ነዋሪዎች ለኢሳት ስልክ በመደወል እንደገለጹት ከቃጠሎው በሁዋላ በከተማው የሚታየው ድባብ አስፈሪ ነው። በቃጠሎው ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ከመስተዳድሩ ምንም አይነት የሞራልና የገንዘብ ድጋፍ ለማግኘት አለመቻላቸው የህዝቡ ቁጣ እንዲጨምር አድርጎታል። በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠረውን ንብረት ያወደመውን እሳት የመስተዳድሩ ባለስልጣናት ሆን ብለው አስነስተውታል በሚል ትችት እየቀረበባቸው ነው። መስተዳድሩ በአፋጣኝ ለወደመው ንብረት ተገቢውን ግምትና ካሳ ...
Read More »የፕሬዚዳንቱን ስልጣን የሚሽር ረቂቅ ህግ ለፓርላማ ቀረበ
ማጋቢት ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አሁን በስራ ላይ የሚገኘውን የይቅርታ ስነስርዓት አዋጅ ቁጥር 395/1996 አዋጅ የሚያሻሻልና የኢትዮጵያን ፕሬዚደንት ስልጣን የሚቀንስ ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ ቀረበ፡፡ በፍትህ ሚኒስቴር ተዘጋጅቶ በሚኒስትሮች ም/ቤት ታይቶ ወደፓርላማ የተመራው ረቂቅ አዋጅ እንደሚያሳየው አሁን በስራ ላይ ባለው አዋጅ የፍትህ ሚኒስቴር ይቅርታ ቦርድ ጽ/ቤት ይቅርታ የጠየቁ ታራሚዎችን ጉዳይ መርምሮ የውሳኔ ሃሳብ ለፕሬዚደንቱ ሲቀርብ በፕሬዚደንቱ ውሳኔ ይቅርታው ...
Read More »ወደ ክልል ተዘዋውረው የሚሰሩ የታክሲ አሽከርካሪዎች እየተያዙ ነው
ማጋቢት ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አንዳንድ ሾፌሮች ለኢሳት እንደገለጹት በባህርዳር ከተማ ወደ ሌሎች ክልሎች ወይም ተዘዋውረው በመስራት ላይ ያሉ ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ የታክሲ አሽከርካሪዎች ታስረው 10 ሺ ብር የሚደርስ ቅጣት እንዲከፍሉ እየተደረገ ነው። በአገራችን እንደልባችን ከክልል ክልል ተዘዋውረን እንዳንሰራ በፖሊሶች ታግደናል የሚሉት ሾፌሮች፣ ለምን ብሎ የጠየቀ ሰው ድብደባ እንደሚፈጸምባቸው ይናገራሉ በሌላ በኩል ደግሞ በሸዋ ሮቢት ከተማ የሚገኙ ...
Read More »