.የኢሳት አማርኛ ዜና

የእህል ንግድ ድርጅት ከ6 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ስንዴ ለገባያ ሊያቀርብ ነው

ሰኔ ፲፱(አስራ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ የሚታየውን የዋጋ ንረት ለማረጋገት በማሰብ ስንዴ የማከፋፈሉ እንቅስቃሴ እንደሚቀጥል ድርጅቱ አስታውቋል። ከሚከፋፈለው 6 ሚሊዮን 500 ሺ ኩንታል ውስጥ 6 ሚሊዮን ኩንታል ከውጭ አገራት ከ700 ሚሊዮን ብር ያላነሰ ወጪ ወጥቶበት የተገዛ ነው። አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ በግንቦት20 በአል ላይ ኢትዮጵያ በምግብ ምርት ራሱዋን ችላለች ብለው መናገራቸው ይታወቃል።

Read More »

አብዛኛው ህዝብ ለመንግስት ጥላቻ አለው” ሲል አንድ ከኢህአዴግ የወጣ  ሰነድ አመለከተ

ሰኔ ፲፯(አስራ ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአማራ ክልል ለሚገኙ አመራሮችና አባላት የተደረገውን ስልጠና አስመልክቶ ከብአዴን ጽህፈት ቤት በቁጥር ብአዴን 145/10/ኢህ/06 ለኢህአዴግ ጽ/ቤት  አዲስ አበባ በሚል የተጻፈው ደብዳቤ “አብዛኛው ህዝብ አሁንም ለመንግስት ከፍተኛ ጥላቻ” ማሳየቱን ገልጿል። የብአዴን አመራር እና አባላቱ ከሰላም የዘለለ የልማት ለውጥ አለመምጣቱን፣ ኢህአዴግ ቢቀጥል ባይቀጥል ግድ እንደሌላቸው፣  እንዲሁም መንግስትን በትክክለኛ ዋጋው ሳይሆን በፍርሃት እንደሚያመሰግኑ በሰነዱ ላይ ተዘርዝሮ ...

Read More »

ከምእራብ እና ምስራቅ ወለጋ የተፈናቀሉ ዜጎች ፍትህ አሁንም ድረስ አለማግኘታቸውን ገለጹ

ሰኔ ፲፯(አስራ ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከምእራብ ወለጋ ዞን ከጊምቢ ወረዳ እንዲሁም ከቀሌም ወለጋ ዞን የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጅ ኢትዮጵያውያን ንብረታቸው ተዘርፎ ከአካባቢው እንዲወጡ ከተደረገ በሁዋላ፣ ችግራቸውን ለአማራ ክልል ርእሰ ማስተዳድር እንዲሁም ለፌደራሉ መንግስት ቢያመለክቱም የሚሰማቸው ማጣታቸውን ገልጸዋል። ኢሳት ካነጋገራቸው የተፈናቃዮች ተወካዮች መካከል አንዳንዶች እንደገለጹት የአማራ ክልልም ሆነ የፌደራሉ መንግስት በክልሎች ጉዳይ ጣልቃ አንገባም በሚል ምክንያት ለጥያቄያቸው መልስ ለመስጠት ፈቃደኞች ...

Read More »

በአዋሳ የታሰሩ የአንድነት አመራሮች ፍርድ ቤት ቀረቡ

ሰኔ ፲፯(አስራ ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ያለፍቃድ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ህገወጥ ቅስቀሳ አድርጋችሁዋላ በሚል የታሰሩት የአንድነት አመራሮች ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበው የ5 ሺ ብር ዋስትና እንዲያስይዙ እና እንዲፈቱ ተጠይቀዋል። የቀጠሮ ጊዜያቸው የፊታችን አርብ ቢሆንም፣ እስረኞቹ ያለቀጠሮ እንዲቀርቡ ተደርጎ ያዋስትና መብት ተፈቅዶላቸዋል። ባለፈው ሰኞ ችሎቱ የእስረኞችን የዋስትና መብት ከልክሎ ነበር። የአንድነት ፓርቲ አመራሮች ባለፈው እሁድ በአዋሳ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ ሲንቀሳቀሱ ...

Read More »

የደገሃቡር የጸጥታ አዛዥ ተገደሉ

ሰኔ ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከሶስት ቀናት በፊት የኦጋዴን ነጻ አውጭ ድርጅት ታጣቂዎች በደጋሃቡር ላይ ድንገት በፈጸሙት ጥቃት ከሞቱት 7 የመንግስት ታጣቂዎች በተጨማሪ የደጋሃቡር የጸጥታ ጉዳዮች ሃላፊ የሆኑት አቶ አሻር ፣ በታጣቂዎች ጥይት ቆስለው ወደ ደጋሃቡር ሆስፒታል ከተወሰዱ በሁዋላ ዛሬ ጠዋት ሰኔ 17 ቀን 2006 ዓም ማረፋቸውን የደረሰን ዜና አመልክቷል። የአካባቢው የልዩ ሚሊሺያ አዛዥ የሆኑት ሙሃመድ ዳይክ ክፉኛ ...

Read More »

ለጋሽ አገራት በኢትዮጵያ ስላለው የህዝብ መፈናቀል ምርመራ እንደሚያካሂዱ አስታወቁ

ሰኔ ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለኢትዮጵያ ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ የሚያደርጉ አገራት በጋራ እንዳስታወቁት በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ እየታየ ያለውን የህዝብ መፈናቀል ለማጣራት አንድ መርማሪ ቡድን ወደ አካባቢው ይልካሉ። ለስኳር ልማት በሚል ምክንያት መንግስት በአካባቢው የሚኖሩ የቦዲና ክዌጎ ጎሳ አባላትን ማፈናቀሉን ዜናውን ይፋ ያደረገው ሰርቫይቫል ኢንተርናሽናል አስታውቋል። አሜሪካ፣ እንግሊዝ፣ ጀርመን እንዲሁም የአለም ባንክን ያካተተው የለጋሾች ቡድን፣ የሚፈናቀሉና ወደ ሌሎች አካባቢዎች ...

Read More »

ዚምባቢዌ ኢትዮጵያውያንን ይዛ አሰረች

ሰኔ ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-37 ኢትዮጵያውያን በህወገጥ መልኩ የዝንባብዌን ድንበር በማቋረጣቸው መያዛቸውን ዴይሊ ኔሽን ዘግቧል። ኢትዮጵያውያኑ ባዞዎች በተሞላው የሊምፖፖ ወንዝ አቋርጠው ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመግባት ሙከራ ሲያደርጉ መያዛቸውን አገሪቱ ፖሊስ አስታውቋል። ጉዳያቸው እየታየ መሆኑን የገለጸው ፖሊስ፣ ምርመራው ሲጠናቀቅ ወደ ፍርድ ቤት እንደሚወስዳቸውም ገልጿል። በርካታ ኢትዮጵያውያን በእየአመቱ ወደ ደቡብ አፍሪካ እንደሚጎርፉ ይታወቃል። በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ስራ አጥነት፣ የኑሮ ...

Read More »

ኢቲቪ እንደእነ ቢቢሲ በኮርፖሬሽን ደረጃ ሊዋቀር ነው

ሰኔ ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ከእነቢቢሲ ያጠናውን  ልምድ መሰረት አድርጎ ስያሜው ወደ ኢትዮጽያ ብሮድ ካስቲንግ ኮርፖሬሽን እንዲቀየርለት የሚጠይቅ ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማው ቀረበ፡፡ ድርጅቱ ለ19 አመታት ሲጠቀምበ ትየቆየውን አዋጅ ማሻሻል ያስፈለገው አደረጃጀቱን በማስተካከል የሚጠበቅበትን ኃላፊነት በብቃት እንዲወጣ እንዲያስችለው ነው ተብሎአል፡፡ ለትርፍያልተቋቋመናተጠሪነቱለፓርላማውየሆነየመንግሥትየልማትድርጅትበመሆንበኮርፖሬሽንደረጃየሚዋቀረውኢትዮጵያብሮድካስቲንግኮርፖሬሽንየዚህኣይነትአደረጃጀትበልምድነትየቀሰምኩትከቢቢሲ፣ከኤስ፣ኤ፣ቢ.ሲ፣ከኬንያውኬ.ቢ.ሲእናከህንዱከኦልኢንዲያንስነውብሏል፡፡ አዋጁለዝርዝርዕይታለኮምቴተመርቷል።

Read More »

ለኢራቅ ችግር የፖለቲካ መፍትሄ እንደሚያሻው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተናገሩ

ሰኔ ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢራቅን እየጎበኙ የሚገኙት ጆን ኬሪ ይህን የተናገሩት አይ ኤስ ኤስ እየተባለ የሚጠራው በአብዛኛው በሱኒዎች የተሞላው ተዋጊ ሃይል የሰሜን ኢራቅን አካባቢዎች እየተቆጣጠረ መምጣቱን ተከትሎ ነው። ድርጅቱ ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት አለው በሚል አሜሪካ እንደ አሸባሪ በመመልከቷ እውቅና አልሰጠችውም። ጆን ኬሪ ኢራቃውያን የችግሩን አሳሳቢነት ተረድተው እየወሰዱት ያለው እርምጃ ሊደነቅ ይገባል አሉ ሲሆን፣ የኢራቅ ፖለቲከኞች በአስቸኳይ ፖለቲካዊ ...

Read More »

የሶማሊው ክልል መሪ የመንግስት ደህንነቶች ሊገድሉዋቸው እንደሚችሉ በመጠቆም ጠባቂዎቻቸውን ቀየሩ

ሰኔ ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሶማሊ ክልል መሪ አብዲ ሞሃመድ ኡመር የፌደራሉ መንግስት የደህንነት ሰዎች ሊገድሉኝ ይፈልጋሉ በማለት ቀድሞ ሲጠብቁዋቸው የነበሩ ጠባቂዎቻቸውን በመቀየር አካባቢው በታማኞቻቸው በአይነ ቁራኛ እንዲጠበቅ እያደረጉ ነው። ካለፉት ሳምንታት ጀምሮ ወደ የፕሬዚዳንቱ ቢሮ ወደሚገኝበት አካባቢ የሚዘዋወሩ ሰዎች ልዩ ፍተሻ እየተደረገባቸው ነው። አቶ አብዲ ባለፈው ሳምንት ከ9 ዞኖችና ከ68 ወረዳዎች የተውጣጡ 1 ሺ 500 የሚሆኑ ከመላው ...

Read More »