ሐምሌ ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአዲስ አበባ ፖሊስኮሚሽንባለፉትወራትለተካታታይ 3 ወራትያክልለሁሉምመካከለኛናከፍተኛፖሊስመኮንኖች ለደህንነትስራእገዛበሚልስልጠናከሰጠ በሁዋላ፣ ከሃምሌ 26 ቀን 2006 ዓ.ምጀምሮደግሞበአዲስአበባምኒልክትምህርትቤትግቢአዳራሽውስጥበስሩለሚገኙትሁሉም የፖሊስአባሎችስልጠናእየሰጠእንደሚገኝ ታውቋል። ስልጠናውለሁሉምፖሊሶች በተለያየዙርእንደሚሰጥይጠበቃል፡፡የስልጠናው ዋና አላማ መጪውን ምርጫ ተከትሎ የፖሊሱን ሚና ማሳወቅ፣ የፖሊሶችን የፖለቲካ አቋም መገምገምና የደህንነት አጠባበቅ ስልጠና መስጠት ነው ። በስልጠናው ላይ አንዳንድ ፖሊሶች የሙስሊም ኢትዮጵያውያንን ተቃውሞ እንዲሁም የመልካም አስተዳደር፣ የኢኮኖሚና የመብት ጥሰቶችን እያነሱ ጥያቄዎችን ሲያቀርቡ እንደነበር መዘገባችን ይታወሳል።
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ጋዜጠኞች ክሳቸውን እንደማንኛውም ሰው በቴሌቪዥን መስማታቸውን ተናገሩ
ሐምሌ ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዓቃቤሕግ «ሕገመንግሥታዊሥርዓቱንበአመጽለመናድ…» በሚልክስመሰረትኩባቸውያላቸውአምስት መጽሔቶችእና አንድጋዜጣእስካሁንየክስቻርጅእንዳልደረሳቸውናጋዜጠኞቹ መከሰሳቸውንእንደማንኛውምሰውየሰሙት በቴሌቪዥንመሆኑንእየተናገሩነው፡፡ የኢሳት ዘጋቢ ከአዲስ አበባ የላከው ሪፖርት እንደሚያስረዳው ጋዜጠኞቹ እንደሚከሰሱ ያወቁት ከመገናኛ ብዙሃን መሆኑ አስገርሟቸዋል። የክስ ቻርጁን ለጋዜጠኞች ልኮ ከማሳወቅ ይልቅ ይህን አይነት አካሄድ ለመጠቀም ለምን እንደተመረጠ ግልጽ አልሆነም።
Read More »የአፍሪካ መሪዎች ስብሰባ የመገናኛ ብዙሃንን ትኩረት ሊስብ አልቻለም
ሐምሌ ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-50 የሚጠጉ የአፍሪካ መሪዎች በፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ግብዣ በዋይት ሃውስ እንዲሰበሰቡ ቢደረገም፣ አለማቀፍ እውቅና ያላቸው የመገናኛ ብዙሃን ብዙም ለጉባኤም ትኩረት አለመስጠታቸውን የሚወጡ ዘገባዎች ያመለክታሉ። አንድ ከአፍሪካ ውጭ ያለ መሪ አሜሪካን ሲጎበኝ የሚሰጠውን የመገናኛ ብዙሃን ሽፋን ያክል 50 የአፍሪካ መሪዎች ተደምረው ሊያገኙ አልቻሉም። ቢቢሲ ከአንድ መለስተኛ ዘገባ በስተቀር ሌሎች ዘገባዎችን ያላስተናገደ ሲሆን፣ ሲኤን ኤን ...
Read More »የኢድ አልፈጥር በዓል በመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ ተከበሮዋለ።
ሐምሌ ፳፩(ሃያ አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-1 ሺህ 435ኛው የኢድ አልፈጥር በመላው የእስልምና ተከታዮች ዘንድ እየተከበረ ነው። በአዲስ አበባ ስታዲየም የነበረው ክብረበአል በሰላም የተጠናቀቀ ሲሆን፣ ድምጻችን ይሰማ ምንም አይነት ተቃውሞ እንዳይካሄድ ባዘዘው መሰረት፣ በአዲስ አበባ ስታዲዮም ተቃውሞ ሳይካሄድ ቀርቷል። የኢህአዴግ የጸጥታ ሃይሎች ሰሞኑን በወሰዱት ጠንካራ እርምጃ በርካታ ሙስሊሞች የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን፣ ቁጥራቸው በውል ያልተወቀ ሙስሊም ዜጎች በእስር ቤት ...
Read More »መንግስት በአቶ አንዳርጋቸው ዙሪያ የተለመደውን የተቀነባበረ ፊልም ለህዝብ አቀረበ
ሐምሌ ፳፩(ሃያ አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የፖሊስ ፕሮግራም አቶ አንዳርጋቸውን በድጋሜ በማቅረብ፣ አቶ አንዳርጋቸው ከባድ ሚስጢር እንዳወጡ አድርጎ ማቅረቡ ብዙዎችን አስገርሟል። ይህ በእንዲህ እንዳለ አቶ አንዳርጋቸው በረሃ በነበረበት ወቅት ለአመታት ሲተኛበት የነበረውን ሰሌን ምንጣፍና ይለብሰው የነበረውን ብርድ ልብስ ኢሳት ፎቶውን ያገኘ ሲሆን፣ በረሃ ላይ የሚገኙ የግንቦት7 ታጋዮች እንደገለጹት ብርድ ልበሱን አንዳርጋቸው ከመቀበሉ በፊት ሌሎች 3 ሰዎች ሲጠቀሙበት ...
Read More »ወጣቶች “በጸረ ሰላም ሃይሎች” ላይ እርምጃ እንዲወስዱብአዴን ጠየቀ
ሐምሌ ፳፩(ሃያ አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የብአዴን ወጣቶች ሊግ ጽ/ቤት በከተሞች የሚገኙ አውራጅና ጫኝ፤ሊስትሮ፤ሱቅ በደረቴ፤ተጽእኖ ፈጣሪ ወጣቶችን፤ በተለያዩ አደረጃጀቶች የታቀፉ ወጣቶችን እና በአደረጃጀት ያልታቀፉ ሌሎች ወጣቶችን በወቅታዊ ጉዳዮች ዙርያ ግንዛቤ ለማስጨበጥ የተዘጋጀው ሰነድ ፣ “የጥፋት ፖለቲከኞች እንቅስቃሴ በመላ የከተማችን ሰላም ወዳድ ወጣቶች የተደራጀና የነቃ ተሳትፎ እንዲከሽፍ ካልተደረገ በመላ ቀልቡ ወደ ልማቱ የገባው ህዝባችን በተለይ ደግሞ ተጠቃሚ እየሆነ የመጣው ወጣቱ ...
Read More »የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በጋዛ ሰላም እንዲሰፍን ተማጸኑ
ሐምሌ ፳፩(ሃያ አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አካባቢውን ጎብኝተው የተመለሱት የተመድ ዋና ጸሃፊ ባንኪ ሙን በጋዛ ከፍተኛ ሰብአዊ ቀውስ መከሰቱን ጠቅሰዋል፡፡ ሁለቱም ተፋላሚ ሃይሎች ጦርነቱን እንዲያቆሙ በሰብአዊነት ስም እጠይቃለሁ በማለት ዋጻ ጸሃፊው ተናግረዋል። የኢድ አል ፈጥርን በአል ምክንያት በማድረግ ሁለቱም ሃይሎች ተኩስ እንዲያቆሙ አለማቀፍ ማህበረሰቡ የጠየቀ ሲሆን፣ ሃማስ የተኩስ ማቆም ስምምነቱን በመጣስ በእስራኤል ላይ ተወንጫፊ ሚሳኤሎችን መተኮሱ ታውቋል። ሃማስ ፣ ...
Read More »አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ደብረዘይት አየር ሃይል ግቢ ታስረው ከፍተኛ ስቃይ እየደረሰባቸው ነው
ሐምሌ ፲፰(አስራ ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የግንቦት7 ዋና ጸሃፊ የሆኑት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከሰኔ 18 ቀን 2006 ዓም ጀምሮ ደብረዘይት በሚገኘው የአየር ሃይል ግቢ ውስጥ በአንድ አነስተኛ ክፍል ውስጥ ታስረው ከፍተኛ ስቃይ እየደረሰባቸው እንደሚገኝ የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። ኢሳት የተለያዩ ምንጮችን አነጋግሮ ባሰባሰበው መረጃ አቶ አንዳርጋቸው በመጀመሪያዎቹ 10 ቀናት ከፍተኛ ድብደባ ከተፈጸመባቸው በሁዋላ ድበደባው ቆሞ፣ የማሰቃያ መርፌዎችን እየተወጉና በኤልክትሪክ ሾክ ...
Read More »የቋራ ነዋሪዎች በመልካም አስተዳደርና በማህበራዊ አገልግሎት እየተሰቃዩ መሆኑን ገለጹ
ሐምሌ ፲፰(አስራ ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸውና ሌሎች የብአዴን ከፍተኛ ሹሞች ለመጪው ምርጫ ይረዳቸው ዘንድ በተለያዩ የአማራ ክልል በሚገኙ ወረዳዎች የህዝብ ተወካዮችን እየዞሩ በማነጋገር ላይ ሲሆኑ፣ የህዝቡ ተወካዮች ግን ችግሮቹን ሳይፈራ እያቀረበ ነው። አንድ አስተያየት ሰጪ “የኢትዮጵያ መብራት ዝናብ የሚፈራ ነው” በሚል ዝናብ በዘነበ ቁጥር መብራት እንደሚጠፋባቸው ተናግረዋል። “ቋራ የሽፍታ አገር ነበረች” ያሉት አስተያየት ...
Read More »በእስራኤልና በሃማስ መካከል ሰላም ለማውረድ ጥረት እየተደረገ ነው
ሐምሌ ፲፰(አስራ ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከሳምንታት በፊት እስራኤል በሃመስ የሚወነጨፉ ሮኬቶችን ለማውደምና መሬት ለመሬት የተሰሩ መተላለፊያዎችን ለመዝጋት በሚል ምክንያት ጦሯን ወደ ጋዛ መላኩዋን ተከትሎ፣ ከፍተኛ ሰብአዊ ቀውስ እየደረሰ ነው። እስካሁን ድረስ ከ800 በላይ ፍልስጤማውያን የተገደሉ ሲሆን በብዙ ሺ የሚቆጠሩት ደግሞ ቆስለዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እንደሚለው አብዛኛው ሟቾች ህጻናትና ሴቶች ናቸው። በእስራኤል ወገን ደግሞ 35 ሰዎች የሞቱ ሲሆን፣ ከ2 ...
Read More »