.የኢሳት አማርኛ ዜና

ለመምህራን ተማሪዎች በሚሰጠው የፖለቲካ ስልጠና ምክንያት የትምህርት መጀመሪያ ጊዜ ተራዘመ

መስከረም ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስት በመላ አገሪቱ የሚገኙ የትምህርት ተቋማት መስከረም 5 ትምህርት እንዲጀምሩ ቀደም ብሎ ይዞት የነበረውን እቅድ በመሰረዝ አዲሱ የትምህርት ዘመን ከመስከረም 30 በሁዋላ እንዲጀመር ትእዛዝ አስተላልፏል። በትምህርት ሚ/ር ደኤታ ዶ/ር ካባ ኡርጌሳ ዲንሳ ለሁሉም ዩኒቨርስቲዎች መስከረም 5፣ 2007 ዓም የተጻፈው ደብዳቤ   የአንደኛ አመት ወይም አዲስ ገቢ ተማሪዎች ጥሪ ተደርጎ ከመስከረም 18 -20/2007 ዓም ምዝገባ ...

Read More »

ኢትዮጵያ የጸረ-ሽብር ህጉዋን፣ ሰብዓዊ መብቶችን ለማፈን መጠቀሙዋን እንድታቆም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አሳሰበ።

መስከረም ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የተመድ የሰብአዊ መብት  ኤክስፐርቶች  ኢትዮጵያ  የጸረ ሽብር ህግን  ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትን ለማፈን እና የማህበራት ነጻነትን ለመጋፋት እየተጠቀመችበት እንደሆነ በመጥቀስ፤ ህጉን አላግባብ መጠቀሙዋን እንድታቆም መጠየቃቸውን-ከጄኔቫ የወጣ መግለጫ ያመለክታል። የተመድ የሰብ ዓዊ መብት ባለሙያዎች አያይሰውም ኢትዮጵያ  በተያሰው ዓመት መጀመሪያ በሰብአዊ መብት ካውንስል አባላት የጸደቀውንና በ 193 ቱም የመንግስታቱ ድርጅት አባል ሀገራት እኩል ተፈጻሚ የሚሆነውን ...

Read More »

በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚፈጸሙ  ወንጀሎች ጨምሯል

መስከረም ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአማራ ክልል በቢቸና አውራጃ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ 2 የቀድሞ የቅንጅት አባሎች ተገድለዋል። ገዢው ፓርቲ እንዳደራጀ የሚነገረው ቡችሌ የተባለው ቡድን ክንዳየ አለሙና አባይነህ በተባሉ የቀድሞ የቅንጅት አባላት ላይ ስዋ ወንዝ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ግድያ መፈጸሙን ለማወቅ ተችሎአል። ሁለቱም ሰዎች በተመሳሳይ መንገድ አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ ተደብድበው መሞታቸው ታውቛል። ከ10 ቀናት በፊት በሻሸመኔ ከተማ አንድ ...

Read More »

በጋምቤላ የተፈጠረው ግጭት በአኒዋ ሰርቫይቫል እይታ

መስከረም ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አቶ ኒክ ኦቻላ ለኢሳት እንደገለጹት በኢትዮጵያ አዲስ አመት ደገኞች በፈጸሙት ጥቃት 8 የመዠንገር ተወላጆች ተገድለው ፣ ከ3 ሺ በላይ የሚሆኑት መሰደዳቸውን ገልጸዋል። 835 መዠንገሮች ቤተክርስቲያን ውስጥ ተጠግተው በምግብ እጥረትና በብርድ ሲሰቃዩ መቆየታቸውን አቶ ኒክ ተናግረዋል። አቶ ኒክ እንደሚሉት ለግጭቱ መንስኤ የኢትዮጵያ መንግስት ያወጣው የመሬት ቅርምት ፖሊሲ ነው። በዚህ ፖሊሲ የተነሳ በርካታ መዠንገሮች አካባቢውን ...

Read More »

የቋራ ህዝብ አቤቱታ

መስከረም ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከዚህ በላይ የት ሄደን አቤት እንደምንል ግራ ተጋብተናልም በማለት በመንግስት አሰራር ማዘናቸውንም ተናገረዋል፡፡ የቋራ ከተማ ነዋሪዎች ከወራት በፊት የክልሉ ርእሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በተገኙበት የጠየቋቸው የመልካም አስተዳደር ፣የመንገድ ፣የመብራት እና ስልክ ችግሮች ይፈታሉ በማለት አመራሮቹ ቃል ቢገቡም በዚህ አመት በተደለደለው የበጀት ቀመር ተጨማሪ በጀት ሳይያዝ መቅረቱ እንዳሳዘናቸው አንዳንድ የከተማዋ ነዋሪዎች እና የወረዳዋ ...

Read More »

በሶማሊ ክልል ያለው ውጥረት እንደቀጠለ ነው

መስከረም ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከክልሉ ባለስልጣናት የሚደረሱን መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ፕሬዚዳንቱ አቶ አብዲ ሙሃመድ ወደ አዲስ አበባ እንዲሄዱ ከጠ/ሚ ሃይለማርያም ደሳለኝ የቀረበላቸውን ጥሪ ባለመቀበል በክልላቸው የሚገኙ ሲሆን፣ ” በኢትዮጵያ ውስጥ ከህወሃቶች በስተቀር ማንም ከስልጣን ሊያነሳኝ የሚችል ሃይል የለም” በማለት፣ የአቶ ሃይለማርያምን ጥሪ ውድቅ አድርገዋል። በምስራቅ እዝ አዛዥ ጄ/ል አብርሃም ገብረማርያም እንደሚተማመኑ የገለጹት አቶ አብዲ፣ አቶ ሃይለማርያምን ጄኔራል ...

Read More »

በሶማሊ ክልል የተፈጸመው ኢሰብአዊ ድርጊት ” ገዢው ፓርቲ ለህዝብ ያለውን ንቀት ያሳያል” ተባለ

መስከረም ፯(ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቀድሞው የሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንት የህዝብ ግንኙነት ስራ አማካሪ እና የክልሉ የወጣቶች ሊቀመንበር በመሆን ካገለገለ በሁዋላ የተለያዩ የቪዲዮ ማስረጃዎችን በመያዝ ከአገር የወጣው ወጣት አብዱላሂ ሁሴን ፣ “ኦ ኦጋዴን” በሚል ኢሳት ያስተላለፈው አጭር የዶክመንታሪ ፊልም፣ በስልጣን ላይ ያሉት ገዢዎች ለሶማሊ፣ ለኢትዮጵያና በአጠቃላይ ለሰው ልጆች ያላቸውን ንቀት ያሳያል ብሎአል። ዘገባውን ከተመለከተ በሁዋላ ህመም እንደተሰማው የገለጸው አብዱላሂ፣ ...

Read More »

ኢህአዴግ ሕገመንግሥቱ የጸደቀበትን 20ኛ ዓመት ድል ባለ ዝግጅት ሊያከብር ነው

መስከረም ፯(ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ህገመንግስቱ የጸደቀበትን ህዳር 29 ቀን «የብሔር ብሔረሰቦች ቀን» በሚል በየዓመቱ ሲያከብረው የቆየው ኢህአዴግ ዘንድሮ  20ኛውን ዓመት በተለየ ድምቅት በማክበር ሕዝቦች በሕገመንግስቱ የተረጋገጡላቸውን ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች አተገባበር እንከን አልባ እንደነበሩ በማጉላት በመጪው ግንቦት ወር ይካሄዳል ተብሎ በሚገመተው ምርጫ ላይ ከፍተኛ ድል ለማግኘት አቅዶ እየተንቀሳቀሰ መሆኑ ለፌዴሬሽን ምክርቤት ቅርበት ያላቸው ወገኖች ገልጸዋል፡፡ ኢህአዴግ ባለፉት 20 ...

Read More »

የሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንት  ወደ አዲስ አበባ እንዲመጡ ቢጠየቁም ፈቃደኛ አልሆኑም

መስከረም ፮(ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አቶ አብዲ ሙሃመድ 7 የስራ አስፈጻሚ የኮሚቴ አባላትን ማበረራቸውን ተከትሎ ወደ አዲስ አበባ በአስቸኳይ እንዲመጡ ቢታዘዙም፣ የቀረበላቸውን ጥሪ ባለመቀበል ጅጅጋ ውስጥ እንደሚገኙ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ምንጮች ተናግረዋል። ለአቶ አብዲ ቅርበት ያላቸው የመከላከያ ባለስልጣኖች በተደጋጋሚ ስልኮችን በመደወል አቶ አብዲን ለማግባባት እየሞከሩ ሲሆን  አቶ አብዲ በበኩላቸው ” ኢትዮጵያ ውስጥ 30 መንግስት ነው ያለው እንዴ?” በማለት ...

Read More »

የመምህራንና የተማሪዎች ስልጠና በልዩነት እንደቀጠለ ነው

መስከረም ፮(ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ለሁለተኛ ዙር እየተካሄደ ያለው የኢህአዴግ ስልጠና በአንዳንድ ዩኒቨርስቲዎች በአለመግባባት ሲቀጥል፣ በሌሎች አካባቢዎች ደግሞ ተማሪዎች በመሰላቸት ውይይቶችን እንደማይከታተሉ ከተሳታፊዎች የሚደርሱን መረጃዎች ያመለክታሉ። የተለያዩ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ  ተማሪዎች  ውይይቱ አሰልቺ በመሆኑ አብዛኛው ተማሪ የግሉን ስራ እንደሚሰራና ውይይቱን እንደማይከታተል ገልጸዋል። ለመምህራን በሚሰጠው ስልጠና ደግሞ በአንዳንድ የማሰልጠኛ ቦታዎች መምህራን ሃሳብ ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው አሰልጣኞች ግፊት ...

Read More »