ጥር ፳፭(ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰማያዊ ፓርቲ የምርጫ ቦርድ ያወጣው ረቂቅ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ውድድር የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ሰዓት አጠቃቀም ድልድል ፍትሃዊና በእኩልነት ላይ የተመሰረተ አለመሆኑን አስታውቋል። ነገረ ኢትዮጵያ እንደዘገበው ጥር 25 ቀን 2007 ዓ.ም የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሀገር አቀፍ ፓርቲዎችን በረቂቅ የሰዓት ድልድሉ ላይ ጊዮን ሆቴል ጋብዞ ውይይት አድርጓል፡፡ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ኃላፊዎች ባቀረቡት የፖለቲካ ፓርቲዎች ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ከአረብ ሃገር ተመላሾች መሬታችን በመነጠቃቸው ሰርተው ለመኖር አለመቻላቸውን ተናገሩ ፡፡
ጥር ፳፭(ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ፣ ሰሜን ወሎና ባቲ አካባቢዎች የሚኖሩ ከስደት ተመላሽ ወጣቶች ባሰሙት ቅሬታ፤ ከአረብ ሃገር ወደ ሃገራችሁ ግቡ የሚለውን የገዢው መንግስት ቅስቀሳ በመስማት ስራቸውን ጥለው ወደ ሃገር ቤት ቢመጡም፣ ከስደት በፊት ጥረው ግረው ያለሙትን ቦታ በኢንቨስትመንት ስም ለባለሃብቶች ተሰጥቶ በማግኘታችው አብዛኛው ወጣቶች ተመልሰው ሲሄዱ ሌሎች ደግሞ ለችግር ተዳርገዋል። 1 መቶ 80 ቅሬታ አቅራቢ ወጣቶች ...
Read More »ፖሊስ የህዝቡን ደህንነት አልጠበቀም በሚል የተቸ የጤና ባለሙያ እንዲታሰር ተባለ
ጥር ፳፭(ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባሳለፍነው ሳምንት በሲዳማ ዞን በአለታ ጩኮ ወረዳ በጩኮ 02 ቀበሌ በቡድን የተደራጁ ሰዎች የአንድን ነጋዴ ቤት በመዝረፍ ግምቱ 9 መቶ ሺህ ብር የሚያወጣ ንብረት ዘርፈውና ድብደባ ፈጽመው ከተሰወሩ በሁዋላ፣ ድርጊቱን የተቃወሙ የአለታ ጩኮ ጤና አጠባበቅ ጣብያ ሃላፊ አቶ ሰለሞን ጤና እንዲያዝ የእስር ትዕዛዝ ወጥቶበታል ። ዝርፍያው የተፈፀመው አቶ ተሾመ የተባሉ ግለሰብ መኖሪያ ...
Read More »475 ሚሊዮን ዶላር የወጣበት የቀላል ባቡር መስመር ምርቃት እያነጋገረ ነው
ጥር ፳፭(ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሶስት ተከፍሎ ከሚካሄደው የአዲስአበባ ቀላል ባቡር ግንባታ መካከል ከቃሊቲ እስከ ለገሃር ያለው መስመር ሙሉ በሙሉ ሳይጠናቀቅ በጥድፊያ ባለፈው እሁድ እንዲመረቅ መደረጉና የሙከራ ስራው ለቀጣይ ሶስት ወራት እንደሚቀጥል መታወቁ እያነጋገረ ነው። የባቡሩ ግንባታ የኤሌክትሮ መካኒካል ስራዎችና የመንገደኞች ተርሚናሎች እንዲሁም ከሀያት ወደ ጦር ሃይሎች እና ከፒያሳ የሚነሳው መስመር ግንባታው አልተጠናቀቀም። የባቡሩን መስመር ለማስመረቅ ጥድፊያ የተሞላበት ...
Read More »በክልሎች የሚገኙ የአንድነት አመራሮች ጽ/ቤታቸውን በአቶ ትእግስቱ ለሚመራው ቡድን እንዳያስረክቡ ተጠየቁ
ጥር ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአቶ በላይ ፍቃዱ የሚመራውና በምርጫ ቦርድ ዕውቅና የተነፈገው የአንድነት አመራር ጥር 29 ቀን 2007 ዓም የብሄራዊ ምክር ቤት ሰብሰባ ለማካሄድ እንዲሁም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ቀበና በሚገኘው ቢሮ ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠት ቀጠሮ ተይዞ የነበረ ቢሆንም፣ ቢሮው በፖሊስ በድንገት በመከበቡ ሳይሳካ ቀርቷል። የብሄራዊ ምክር ቤቱ ሰብሳቢ አቶ አበበ አካሉ ለኢሳት እንደገለጹት ስብሰባውን ለማካሄድ ታስቦ ...
Read More »የአርበኞች ግንቦት7 ሴት አባላት የትግል ጥሪ አቀረቡ
ጥር ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ገዢውን ፓርቲ በሃይል ለማንበርከክ በትግል ላይ የሚገኙ የአርበኞች ግንቦት7 ሴት አባላት ጥሪያቸውን ያቀረቡት የመስክ ጉብኝት ለማድረግ ለተንቀሳቀሱት የኢሳት ጋዜጠኞች ነው። ሴት አርበኞቹ በአገሪቱ ውስጥ እየተካሄደ ያለው አፈናና የመብት ጥሰት በስልጣን ላይ ያለውን የህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት በሃይል ለማንበርከክ ነፍጥ እንዲያነሱ እንዳስገደዳቸው ገልጸዋል። ለሁለት ወራት ያክል ከኢህአዴግ ታጣቂ የሰራዊት አባላት ጋር ጠንካራ ፍልሚያ ስታደርግ ቆይታ ...
Read More »በሰሜን አርማጭሆ ያለው ውጥረት እንደቀጠለ ነው
ጥር ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት በአማራ እና በትግራይ አዋሳኝ ቦታዎች ካለፉት ሁለት ወራት ጀምሮ የሚታየው ውጥረት እንደቀጠለ ሲሆን፣ ገዢው ፓርቲ የአካባቢውን ህዝብ ለአመጽ ያነሳሳሉ ያላቸውን ሰዎች ለመያዝ መመኮሩ ብዙ ወጣቶች ቀያቸውን እየተዉ እንዲሸፍቱ አስገድዷቸዋል። የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች የአካባቢውን ወጣት እየሰበሰቡ የግንቦት7ትን መመሪያ እያስፈጸማችሁ ነው በማለት እያስፈራሩዋቸው ሲሆን ፣ ነዋሪዎቹ ግን ጥር 16 ባወጡት ...
Read More »ምርጫ ቦርድ፣ ቦርዱን ያከብራሉ ያላቸውን በእነ ትግዕስቱ አወሉ ለሚመራው አንድነት እና በእነ አቶ አበባው መሀሪ ለሚመራው መኢአድ ዕውቅና ሰጠ፡፡
ጥር ፳፩(ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የቦርዱ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መርጋ በቃና እና የቦርዱ ጸሀፊና ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ነጋ ዱፊሳ በጋራ ዛሬ ጥር 21 ከቀኑ 10፡00 ሰኣት በአዲስ አበባ ሒልተን ሆቴል በሰጡት መግለጫ በእነአቶ በላይ ፍቃዱ የሚመራው አንድነት፤ የፓርቲውን ደንብና የምርጫ አዋጁን የጣሱ ተግባራትን እንደሚያከናውን፣ ፓርቲው ያካሄደውን ጉባዔ ለሰባት ወራት ሳያሳውቀው መቆየቱን፣ የቀድሞ ፕሬዚደንት ከሃላፊነታቸው የተነሱት ሕጉን ጠብቆ ...
Read More »መንግስት ከምርጫው በፊት አፈናውን ያቆማል የሚለው ተስፋ መሟጠጡን ሂውማን ራይተስ ወች አስታወቀ
ጥር ፳፩(ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ድርጅቱ ባወጣው የ2014 አለማቀፍ የሰብአዊ መብት አያያዝ ሪፖርት ላይ እንደጠቀሰው መንግስት ጋዜጠኞችን፣ ጸሃፊዎችን እና የተቃዋሚ ፓርቲ ደጋፊዎችን እንደፈለገ ያስራል፣ በሰላም ተቃውሞአቸውን ለመግለጽ በወጡ ዜጎች ላይ ፖሊስ የሃይል እርምጃ ይወስዳል፤ እንዲሁም ለማፈኛነት እየዋሉ ያሉትን በአለማቀፍ ማህበረሰብ ዘንድ የተወገዙትን አዋጆችን ለመለወጥ ምንም ምልክት አላሳየም ብሎአል። ባለፈው አመት የኢትዮጵያ መንግስት ማንኛውንም ተቃውሞ ለማፈን መሞከሩን ...
Read More »ሄሊኮፕተር በመያዝ ወደ ሶስተኛ አገር የጠፉት የአየር ሃይል ባልደረቦች በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ገለጹ
ጥር ፳(ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ወር ሄሊኮፕተር ይዘው የጠፉት ሻምበል ሳሙኤል ግደይ፣ መቶ አለቃ ቢልልኝ ደሳለኝ እና ቴክኒሻን ጸጋ ብርሃን ግደይ በተረጋጋ እና በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ለኢሳት ገልጸዋል። ፓይለቶቹ በሚገኙበት ሶስተኛ አገር ውስጥ ሆነው ከኢሳት ጋር ግንኙነት የመሰረቱ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚደረገው የነጻነት ትግል አስተዋጽኦ ለማድረግ መዘጋጃታቸውን ተናግረዋል። ሶስታችንም በአንድ ላይ የምንመደብበትን ጊዜ ስንጠብቅ ቆይተን ...
Read More »