.የኢሳት አማርኛ ዜና

ግብጽ ኢትዮጵያና ሱዳን በአባይ ግድብ ዙሪያ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን አስታወቁ

የካቲት ፳፯(ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ካርቱም ሱዳን ውስጥ ሲደረግ የነበረው ሶስቱ አገራት ድርድር በስኬት መጠናቀቁን የሶስቱም አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አስታውቀዋል። የግብጽ የውሃ ሃብት ሚኒስትር  ስምምነቱ ግብጽ በግድቡ ላይ ያላትን ስጋት ያስወገደ ነው ብለዋል። የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሊ ካርቲ በሶስቱ አገራት መካከል ሙሉ ስምምነት መደረሱን ገልጸዋል። የተስማሙባቸውን መርሆዎች ለሶስቱን አገራት መሪዎች በማቅረብ እንዲጸድቁ እንደሚደረግ ሚኒስትሩ ተናግረዋል። ...

Read More »

በአፋር ወጣቶች ለስለላ እየታፈሱ ነው

የካቲት ፳፯(ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአፋር ነጻ አውጭ ድርጅቶች በአካባቢው እያደረሱት ያለው ተጽአኖ ያሰጋው መከላከያ፣ በአፋር የተለያዩ የጠረፍ ከተሞች የሚገኙ ወጣቶችን በማፈስ ላይ ነው። ስማቸው ለደህንነት ሲባል እንዳይጠቀስ የጠየቁት ወላጆች በደርግ ጊዜ የቀረው አፈሳ በክልሉ እንደ አዲስ መጀመሩን ተናግረዋል። በርካታ ወጣቶች አፈና በመፍራት ጫካ መግባታቸውንም ነዋሪዎች አክለዋል። አርዱፍ፣ አፋር ጋድሌና የአፍዴራ ወጣቶች በቅርቡ ግንባር መፍጠራቸውን ኢሳት መዘገቡ ...

Read More »

የደቡብ ሱዳን ተፈላሚ ሃይሎች በሃምሌ ወር የሽግግር መንግስት እንዲመሰርቱ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ጠየቁ

የካቲት ፳፯(ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኢጋድ ሊቀመንበርነታቸው ለመገናኛ ብዙሃን እንደተናገሩት የደቡብ ሱዳንን መንግስትና ተቃዋሚውን ሃይል ለማቀራረብ ለወራት ሲደከምበት የነበረው የሰላም ድርድር ያለውጤት  ተበትኗል። ፕሬዚዳንት ሳልቫኪርና ተቀናቃኛቸው ሪክ ማቻር ያለፉትን 4 ቀናት በአዲስ አበባ ያሳለፉ ቢሆንም፣ መሰረታዊ በሚባሉት የስልጣን ክፍፍል፣ ፌደራሊዝም እንዲሁም በሰራዊት ውህደትላይ መግባባት ሳይችሉ ቀርተዋልአቶ ሃይለማርያም  ያለንን ሃይል ሁሉ ተጠቅመን የደቡብ ሱዳን መንግስት በሃምሌ ...

Read More »

በፖለቲካ አመለካከታቸው የተነሳ በትግራይ አርሶ አደሮች ሰብሎቻቸውን የመስኖ ውሃ እንዳያጠጡ መከልከላቸውን ተናገሩ

የካቲት ፳፮(ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአጽቢ ወንበርታ ወረዳ በሩባ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑ በርካታ ቁጥር ያላቸው አርሶ አደሮች ለኢሳት እንደገለጹት፣ የአረና ፓርቲ አባላት ናቸው በሚል የመሰኖ ውሃ እንዳያጠጡ በመከልከላቸው፣ ሰብሎቻቸው እየደረቁ ነው። 12 አርሶ አደሮችን በመወከል ለኢሳት የተናገረው አቶ ህድሮም ሃይለስላሴ የተቃዋሚ አባላት ብቻ በመሆናችን አትክልቶቻችንን የመስኖ ውሃ እንዳያጠጡ፣ ከእነሱ መካከል ሁለቱ ብቻ የተቃዋሚ አባላት ቢሆኑም፣ ዘመዶቻቸው ሁሉ ...

Read More »

ኦህዴድ ለ25ኛ አመት በአሉ ገንዘብ እንድናወጣ እያስገደደን ነው ሲሉ ባለሃብቶች ገለጹ

የካቲት ፳፮(ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቀድሞ የሸእቢያ ምርኮኞች የተመሰረተው ኦህዴድ 25ኛ አመት የእዮቤልዩ በአሉን ድል ባለ ድግስ ለማክበር በማሰቡ በክልሉ የሚገኙ ባለሃብቶችን ስብሰባ የጠራ ሲሆን፣ የድርጅቱ ካድሬዎች ህዝቡ ገንዘብ እንዲያዋጣ በመቀስቀስ ላይ ናቸው። የክልሉ ፕሬዚዳንት የካቲት 29 ቀን 2007  ዓም ባለሃብቶች በአሉን ስፖንሰር እንዲያደርጉ ለመጠየቅ በአዲስ አበባ ኢሊሊ ሆቴል ስብሰባ ጠርተዋል። ድርጅቱ ” ድርጅታችን ኦህዴድ/ኢህአዴግ 25ኛ ኣመት ...

Read More »

በተለያዩ የአገሪቱ ክፍል የደን ቃጠሎ ተነሳ

የካቲት ፳፮(ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኦሮምያ ክልል በዝቋላ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ዙሪያ የሚገኘው ደን ካለፉት 3  ቀናት ጀምሮ በእሳት እየወደመ ሲሆን፣ የአካባቢው ነዋሪዎች እና የጸጥታ ሃይሎች እሳቱን ለማጥፋት በመረባረብ ላይ ናቸው። ይህን መረጃ እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ ምን ያክል ስፋት ያለው ደን እንደወደመ ለማወቅ አልተቻለም። በባሌ ዞን በወረዳ ሼዳ ቀበሌ አካባቢም ተመሳሳይ ቃጠሎ ተነስቶ በቁጥጥር ስር ...

Read More »

ሶስት ሚሊየን ብር የሚጠጋ ወጭ የወጣበት ድልድይ የጥራት ችግር አለበት ተባለ

የካቲት ፳፮(ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአባይ  ወንዝ ላይ የተሰራዉ 108 ሜትር ርዝመት እና አንድ ነጥብ ስድስት  ሜትር ስፋት ያለው ተንጠልጣይ ድልድይ  በሃገሪቱ ብቸኛዉ የተንጠልጣይ  ድልድይ በመስራት በሚታወቀው  ሄልቬታስ ሲዊዝ ኢንተርኮኦፕሬሽን በተሰኘ መንግስታዊ ባልሆነ ድርጅት ባለፈው ታህሳስ ወር መጨረሻ በይፋ ተመርቆ ስራ ቢጀምርም፣ በምረቃው ስነስርዓት የተገኙ ባለሙያዎች ድልድዩ የጥራት ችግር እንዳለበት መናገራቸው ነዋሪዎችንና በቦታው ተገኙ አመራሮችን አስደንግጧል፡፡ ...

Read More »

ፈገግ  ሚያሰኘው ዜና

የካቲት ፳፮(ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የመከላከያ  ሰራዊት  ከፍተኛ  መኮንኖች  እና  መንግስት  ከፍተኛ  አመራሮች  በተገኙበት  በተደረገው  የምስጋና  ሲመፖዝየም  በከተማዋ  ከሚገኙ  ክፍለ  ከተማዎች  የተመረጡ  የገዢው  ፓርቲ  አባላትና  አቀንቃኞች እንዲሁም ከየመምርያው  የተወከሉ አባላት በተገኙበት መከላከያ ሰራዊቱ ለሃገሪቱ ዘብ የቆመ፣ በልማቱ ተሳታፊና ሁለንተናዊነቱን በማንሳት መወድሰ- መከላከያ ሰራዊት ሲደረግ ውሎአል። በዚህ የሰራዊቱን አመራሮች የማድነቅ ስነስርዓት ላይ ንግግራቸው በጭብጨባ እንዲታጀብ እጠየቁ ተሰብሳቢውን ሲያነቃቁ ...

Read More »

በሱዳናዊው የመኪና አሽከርካሪ ጥቃት የደረሰባት ኢትዮጵያዊት አረፈች

የካቲት ፳፭(ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የካቲት 24 ፣ 2007 ዓም በሱዳናዊ ሹፌር በአሰቃቂ ሁኔታ ጥቃት የተፈጸመባት ኢትዮጵያዊት ወጣት ማረፉዋን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። ወጣቷ በአሰቃቂ ሁኔታ በጩቤ ተወጋግታ መሞቱዋን የገለጹት የወረታ ነዋሪዎች፣ ሹፌሩ በቁጥጥር ስር ውሎአል ቢባልም በትክክል ስላለበት ሁኔታ ማወቅ እንዳልቻሉ ገልጸዋል። ኢትዮጵያዊቷ ወጣት ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ ማዳበሪያ ጭኖ ይጓዝ የነበረውን መኪና ሹፌር ወደ ባህርዳር እንዲወስዳት  እንፍራንዝ ...

Read More »

ከፍተኛ  የመንግስት  ባለስልጣናት  አበል ካልተሰጠን ፍርድ ቤት አንቀርብም አሉ

የካቲት ፳፭(ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በከሳሽ ኣቃቤ  እና  ህግ በተከሳሽ አቶ ኣስገደ ገ/ሥላሴ መካከል ሲደረግ በነበረው ክርክር  ለምስክርነት የተጠሩት ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ሊቀርቡ ባለመቻካቸው  በፖሊስ ተይዘው እንዲቀርቡ  ቢታዘዝም፤  ባለስልጣናቱ  ከለመዱት ምቹ ህይወት አኳያ ማቅረብ ሳይቻል ቀረ። የህወሀት የደህንነት ሰራተኛው ብስራት አማረ  የመሰረተባቸውን ክስ  ተከትሎ ላለፉት ሶስት ዓመታት ሲከራከሩ  የቆዩት የቀድሞው የህወሀት ታጋይና የአሁኑ የሰማያዊ ፓርቲ አባል አቶ ...

Read More »