ሚያዝያ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የዞን ዘጠኝ ጦማርያን እና ሶስቱ ጋዜጠኞች ግንቦት 19/2007 ዓ.ም የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን፣ ፍርድ ቤቱ አቃቤ ህግ አሉኝ ባላቸው ሲ.ዲዎች እና ቀሪ ምስክሮቹ ላይ ብይን ሰጥቷል፡፡ ፍርድ ቤቱ አቃቤ ህግ ምስክሮቹን ለማቅረብ በተደጋጋሚ የሰጠውን እድል ባለመጠቀሙ እና ምስክሮቹን ላለማቅረቡ የሰጠው ምክንያትም በቂ ባለመሆኑ አቃቤ ህግ ያቀረበውን የተጨማሪ ጊዜ ቀጠሮ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
አቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝ ከምርጫ ጋር ተያይዞ ሁከትና ብጥብጥ ለመፍጠር ምልክት አሳይተዋል ያሉዋቸውን የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችና ደጋፊዎች አስጠነቀቁ፡፡
ሚያዝያ ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጠ/ሚኒስትሩ በፓርላማ ተገኝተው ከኢህአዴግ የም/ቤቱ አባላት ለቀረቡላቸውን ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡ ሲሆን በዚህ ምላሻቸውም በስም ያልጠቀሱዋቸውን ተቃዋሚዎች አስጠንቅቀዋል። የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ወደምርጫው የገቡት በግማሽ ልብ መሆኑን ፣ የብጥብጥና የሁከት አማራጭ ከተገኘ ያንን ለማካሄድ የሚያስቡ ናቸው ሲሉ ፈርጀዋቸዋል። ” የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎቹ በአንዳንድ አካባቢዎች ከወዲሁ እኛ አሸንፈናል፣ ከተሸነፍን ደግሞ ምርጫው ተጭበርብሮአል፣ ይህንን አውቃችሁ ...
Read More »በየመን 5 ኢትዮጵያውያን መገደላቸው ተዘገበ
ሚያዝያ ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ረዩተርስ ከካይሮ እንደዘገበው በሳውድ አረቢያ የሚመራው የጥምር ሃይል በየመን በአንድ አለማቀፍ የበጎ አድራጎት ጽህፈት ቤት ላይ በወሰደው ጥቃት 5 ኢትዮጵያውያን ሲገደሉ 10 የሚሆኑት ደግሞ ቆስለዋል። ጥቃቱ የሃውቲ ሚሊሺያዎች ዋና ደጋፊ ተደርጎ በሚቆጠረው ሃጅያ ግዛት ውስጥ በሚገኘው ማይዲ ከተማ ላይ በከባድ መሳሪያና በአየር መፈጸሙን የዜና ድርጅቱ ገልጿል። የሳውድ አረቢያ ጦር ከሃውቲ ሚሊሺያዎች ...
Read More »በቤንሻንጉል ጉሙዝ ለአማራው መፈናቀል ምክንያት የሆነው ክልሉ የፈረመበት ደብዳቤ ኢሳት እጅ ውስጥ ገባ
ሚያዝያ ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በ2005 ዓም ቁጥራቸው ከ20 ሺ ያላነሰ በአብዛኛው ከመስራቅና ምእራብ ጎጃም የመጡ ዜጎች፣ ክልሉን ለቀው እንዲወጡ በመታዘዛቸው ቁጥራቸው በውል ያልተወቁት መንገድ ላይ ሲሞቱ፣ ሌሎች ደግሞ ቤት ንብረታቸውን አጥተዋል። በጊዜው ኢሳትና ሌሎች የመገናኛ ብዙሃን ባደረሱት ተጽኖ መንግስት ተፈናቃዮች እንዲመለሱ ቢያደርግም፣ አጥፊዎችን ለፍርድ የማቅረቡ ጉዳይ ለረጅም ጊዜ ሲጓተት ቆይቶ በመጨረሻ መንግስት የተወሰኑ የወረዳ ባለስልጣናትን ...
Read More »የአየር ሃይልና የመከላከያ አባላት ክስ ተመሰረተባቸው
ሚያዝያ ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከግንቦት ሰባት ጋር ግንኙነት ፈጥረዋል፤ አባላትን መልምለዋል፤ ለሽብርተኛ ቡድኑ መረጃ አቀብለዋል፤ እንዲሁም ወደኤርትራ በመኮብለል የሽብር ድርጅቱን ፖለቲካዊና ወታደራዊ ስልጠና ለመውሰድ ተሰናድተው ሲንቀሳቀሱ ደርሼባቸዋለሁ በሚል የፌዴራል ዐቃቤ ሕግ በ7 የመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ ግንቦት 11 ቀን 2007 ዓ.ም በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ክስ መመሰርቱን ሰንደቅ ዘግቧል። ተከሳሾች መቶ አለቃ ...
Read More »በተቃዋሚ ፓርቲ ወጣት አባላት ላይ የሚወሰደው እርምጃ አስከፊ ሆኖ ቀጥሏል
ሚያዝያ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ገዢው ፓርቲ ከመጪው ምርጫ ጋር በተያያዘ ህዝቡን አስተባብረው ህዝባዊ አመጽ ያስነሱ ይሆናል በሚል የሚጠረጥራቸውን ወጣቶች ሁሉ እያፈሰ ከማሰር አልፎ ፣ አንዳንዶች እየተገደሉ ሌሎች ደግሞ አሰቃቂ ድብደባ እየተፈጸመባቸው ነው። በባህርዳር ዩኒቨርስቲ ዋናው ግቢ የሚማር አንድ የመድረክ አባል እንደሆነ የሚታወቅ የ3ኛ አመት ተማሪ ግቢው ውስጥ ወድቆ ከተገኘ በሁዋላ የተሻለ ህክምና ለማግኘት ባለመቻሉ ህይወቱ ...
Read More »ግንቦት 7ትን ለመቀላቀል ሲሄዱ ተያዙ የተባሉት እነ ብርሃኑ ተክለያሬድ ፍርድ ቤት ቀረቡ
ሚያዝያ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ነገረ ኢትዮጵያ እንደዘገበው ግንቦት 12/2007 ዓ.ም በልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት የቀረቡት በሃያዎቹ የእድሜ ክልል የሚገኙት ብርሃኑ ተክለያሬድ፣ እየሩሳሌም ተስፋው ፣ ፍቅረማርያም አስማማው እና ደሴ ካህሳይ ናቸው። ተከሳሾች “ኤርትራ ውስጥ መቀመጫውን ባደረገውና በሽብርተኝነት በተፈረጀው ግንቦት ሰባት ስር አባል ሆነው የሽብር ተልዕኮ ለመፈጸምና ለማስፈጸም ወስነው ከድርጅቱ ጋር ለመቀላቀል የኢትዮጵያንና የኤርትራን ...
Read More »መጭውን ምርጫ ተከትሎ በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል ከፍተኛ ውጥረት እየታየ ነው
ሚያዝያ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለኢሳት የሚደርሱት መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ከመጪው ምርጫ ጋር በተያያዘ በተለይ በሰሜን የአገሪቱ ክፍል አብዛኛው ህዝብ ረብሻ ይነሳል ብሎ ያምናል። በዚህም የተነሳ ቀድም ብለው ገንዘባቸውን ባንክ ያስቀመጡ ሰዎች ገንዘባቸውን እያወጡ ለምግብ የሚውሉ የእህል ዘሮችን፣ ጨውና ሌሎችንም እቃዎች እየገዙ ነው። ወፍጮ ቤቶች ሰሞኑን ተጨናንቀው ታይተዋል። አቅም ያለው ቤተሰብ ለሶስት ወር የሚበቃ እህል ሲያስፈጭ፣ ድሃው ...
Read More »የብአዴን አመራሮች ድርጅታቸው የገጠመውን ፈተና ተናገሩ
ሚያዝያ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን በባህርዳር ከተማ በተካሄደው የብአዴን ማእከላዊ የዞን ጽህፈት ቤት ሃላፊዎች ውይይት በቀጣይ ምን ማድረግ አለብን የሚለውን መመሪያ ለአባላቱ ባስተላለፈው የግንዛቤ ማስጨበጫ መልዕክት፣ ድርጅቱ በርካታ ችግሮች እንዳሉበት የድርጅቱ ልዩ ልዩ አመራሮች ተናግረዋል፡፡ የብአዴን ማእከላዊ ዞን ጽህፈት ቤቱ ሃላፊ ሲናገሩ የብአዴን አመራሮች በ1990 ዓ.ም ከታየው የጥገኝነት ዝቅጠት አንስቶ በርካታ ፈተናዎችን ለማለፍ እንደተገደዱ ገልጸው፤ ...
Read More »በእስራኤል የሚገኙ የኢትዮጵያ ቤተእስራኤላውያን የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ
ሚያዝያ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሺ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ቤተእስራኤላውያን ባደረጉት የተቃውሞ ሰልፍ በአገሪቱ ማህበራዊ ፍትህ እንዲሰፍንና ዘረና የሆነው ፖሊስ እንዲያዝ ጠይቀዋል። ከሳምንታት በፊት የተካሄደው ተመሳሳይ የተቃውሞ ሰልፍ ደም አፋሳሽ ሆኖ ቢጠናቀቅም ፣ የአሁኑ ሰልፍ በሰላም ተጠናቋል። ከ185 ሺ በላይ ቤተእስራኤላውያን በእስራኤል ምድር የሚኖሩ ሲሆን ከዘረኝነት ጋር በተያያዘ የተለያዩ አድሎዎች ይፈጸሙባቸዋል። ከዚህ ቀደም እናቶች ያለፈቃዳቸው የወሊድ መቆጣጠሪያ ...
Read More »