በእስራኤል የሚገኙ የኢትዮጵያ ቤተእስራኤላውያን የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ

ሚያዝያ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሺ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ቤተእስራኤላውያን ባደረጉት የተቃውሞ ሰልፍ በአገሪቱ ማህበራዊ ፍትህ እንዲሰፍንና ዘረና የሆነው ፖሊስ እንዲያዝ ጠይቀዋል።
ከሳምንታት በፊት የተካሄደው ተመሳሳይ የተቃውሞ ሰልፍ ደም አፋሳሽ ሆኖ ቢጠናቀቅም ፣ የአሁኑ ሰልፍ በሰላም ተጠናቋል።
ከ185 ሺ በላይ ቤተእስራኤላውያን በእስራኤል ምድር የሚኖሩ ሲሆን ከዘረኝነት ጋር በተያያዘ የተለያዩ አድሎዎች ይፈጸሙባቸዋል።
ከዚህ ቀደም እናቶች ያለፈቃዳቸው የወሊድ መቆጣጠሪያ መርፌ እንዲወጉ መደረጋቸው ፣ ኢትዮጵያውያን የለገሱት ደም እንዲደፋ መደረጉ እንዲሁም በቅርቡ ደማስ ፈቃደ በተባለ ወታደር ላይ አንድ ፖሊስ የፈጸመው ድብደባ ኢትዮጵያውያን
በስርአቱ ላይ ተቃውሞ እንዲያነሱ ካደረጉዋቸው ምክንያቶች መካከል ይጠቀሳሉ ።