.የኢሳት አማርኛ ዜና

የአዲስ አበባ ፖሊስ አባሎቹን እየገመገመ ነው

ሰኔ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰኔ አንድ ተጀምሮ ሰኔ 20 የሚጠናቀቀው ግምገማ ከፍተኛ አመራሮችን፤አዛዦችን እንዲሁም ተራ የፖሊስ አባሎችን አካቷል። ከጉለሌ ፖሊስ መምሪያ የተገኘው መረጃ እንደሚያስረዳው የግምገማው ይዘት በፖሊስ ስነምግባር ዙሪያ ነው። በግምገማው ወቅት አንድ ባለ ሳጅን ማዕረግ ያለውና አንድ ኮንስታብል ፖሊስ በስልካቸው ውስጥ የግንቦት ሰባት፤የሰማያዊ ፓርቲና የሌሎች ተዛማጅ ድርጅቶች መረጃዎች በስልካቸው ውስጥ ተገኝቷል በሚል ተይዘው ወደ ማዕከላዊ ...

Read More »

በባህር ዳር ከተማ ለመኖሪያ ቤት ባለ ይዞታዎች ተሰጥቶ የነበረው የባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ ተመልሶ ተሰበሰበ

ሰኔ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የምርጫ 2007 ቅስቀሳን ተንተርሶ በህዝቡ ዘንድ የሚቀርቡትን ጥያቄዎች ለመመለስ በሚል ሲንቀሳቀስ የነበረው ኢህአዴግ፤ በከተማዋ በልዩ ልዩ ክፍለ ከተሞች ለረዢም አመታት ለኖሩ የይዞታ ባለመብቶች ከምርጫው በፊት ሰጥቶት የነበረውን በባለ ቀለም የብአዴን አርማና የኢትዮጵያ ሰንደቃላማ ያሸበረቀ የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ መልሶ በመውሰድ ውሳኔውን ለመሻር እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡ ኢህአዴግ “በየክፍለ ከተማው ከ380 በላይ አባወራዎችን የይዞታ ...

Read More »

አንድ የአረና ፓርቲ አባል ተገደሉ

ሰኔ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአረና ፓርቲ የአመራር አባል የሆነው አምዶም ገብረስላሴ በፌስ ቡክ ገጹ እንደጻፈው ፣ የ48 አመቱ አቶ ታደሰ ኣብርሃ የተባሉ የዓረና-መድረክ ኣባልና የምዕራባዊ ዞን የዓረና ኣመራር ኣባል ትናንት ማታ 09 / 10 / 2007 ዓ/ም በሶስት ሰወች ታንቀው ተገድለዋል። አቶ ታደሰ ኣብራሃ በቓፍታ ሑመራ ወረዳ ማይካድራ ቀበሌ ነዋሪ ሲሆኑ በዘንድሮው ምርጫ ወቅት በቀበሌው ኣስተዳዳሪዎች፣ ...

Read More »

በደብረማርቆስ የሰማያዊ እጩ ተወዳዳሪ ተገደለ

ሰኔ ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሃያዎቹ መጨረሻ የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኘው የሰማያዊ ፓርቲ የምስራቅ ጎጃም ዞን ጸሃፊ ሳሙኤል አወቀ ሰኔ 8/2007 ዓም ምሽት ላይ ሁለት ግለሰቦች ወደ ቤቱ ሲገባ ጠብቀው በፈጸሙበት ድብደባ ህይወቱ አልፎአል። የሳሙኤል ጓደኞችና የስራ ባልደረቦች ድርጊቱን የመንግስት ሃይሎች እንደፈጸሙት ምንም ጥርጣሬ እንደሌላቸው ተናግረዋል። ሳሙኤል ጀግና እና ለአገሩ የሚቆረቆር ጠንካራ ወጣት ነበር የሚሉት ጓደኞቹና የትግል ...

Read More »

አንድ የፌደራል ፖሊስ 3 ባልደረቦቹንና አንድ ቻይናዊ ገደለ

ሰኔ ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የትውልድ ቦታው አሶሳ አከባቢ የሆነ የፌዴራል ፖሊስ አባል ሌሎች ሶስት የፌዴራል ፖሊስ አባላትን እና አንድ ቻይናዊን በምዕራብ ሀረርጌ ሚኤሶ ወረዳ ልዩ ስሙ ቦርደዴ በተባለ ቦታ በጥይት ተኩሶ ከገደላቸዉ በሃላ መሰወሩን የአካባቢው ምንጮች ገልጸዋል:: የፌደራል ፖሊሶችና የኦሮምያ ፖሊስ ገዳዩን ለመያዝ በጭሮ፣ ሚኤሶ፣ በዴሳ፣ ገለምሶና አዋሽ ከተሞች ቤት ለቤት እየገቡ ፍተሻ በማካሄድ ላይ ናቸው። ...

Read More »

በከፋ ዞን ቦንጋ ከተማ የዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ የምርጫ አደራጅ በድብደባ ሆስፒታል ገባ

ሰኔ ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጊምቦ ገዋታና በቦንጋ የተራዘመው ምርጫ ባለፈው ሳምንት ከተጠናቀቀ በሁዋላ፣ የግል ተወዳዳሪው ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ የምርጫ ቀስቃሽና አደራጅ የሆነው ምትኩ ወልዴ ፣ ትናንት ከቀኑ 6 ሰአት ከ 30 ደቂቃ ላይ ፖሊሶች ከቤት አውጥተው የደበደቡት ሲሆን፣ ግለሰቡ በደረሰበት ከፍተኛ ድብደባ ቦንጋ ሆስታል ከገባ በሁዋላ፣ ወደ ጅማ ሪፈራል ሆስፒታል ተወስዷል። ግለሰቡ የደረሰበት ድበደባ ከፍተኛ በመሆኑ ...

Read More »

በሽብርተኝነት ስም የተከሰሱት እነ ብርሃኑ ተ/ያሬድ የክስ መቃወሚያ አቀረቡ

ሰኔ ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢትዮ-ኤርትራ ድንበርን ተሻግረው በሽበርተኝነት የተፈረጀውን የግንቦት ሰባት ወታደራዊ ክንፍ ሊቀላቀሉ ሲሉ ማይካድራ ላይ በጸጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ስር አውያቸዋለሁ ያላቸውን እነ ብርሃኑ ተክለያሬድ፣ አቃቤ ህግ ባቀረበባቸው ክስ ላይ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያቸውን አቅርበዋል። ዛሬ ሰኔ 9/2007 ዓ.ም በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የቀረቡት በእነ ብርሃኑ ተክለያሬድ የክስ መዝገብ የተካተቱት አራት ተከሳሾች ብርሃኑ ...

Read More »

በጭልጋ የፌደራል ፖሊስ በወሰደው እርምጃ ከ5 ያላነሱ ሰዎች ተገደሉ

ሰኔ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ቅዳሜ በሰሜን ጎንደር ዞን በጭልጋ ከተማ የፌደራል ፖሊሶች በወዱት እርምጃ ከ5 እስከ 6 የሚደርሱ ወጣቶች መገደላቸውን፣ ከ10 ያላነሱ ወጣቶች ደግሞ መቁሳላቸውን የአይን እማኞች ገልጸዋል። የቅማንት ተወላጆች የራስ አስተዳደር መብት ይሰጠን በሚል ላቀረቡት ጥያቄ ፣ የአማራ ክልል ምክር ቤት “ጥያቄያቸው በክልሉ ውስጥ እንደሚገኙት እንደ ሌሎች ብሄረሰቦች ሊታይላቸው” ይገባል የሚል ውሳኔ አሳልፏል። ጥያቄ ...

Read More »

በሊቢያ በርካታ ኢትዮጵያውያን በእስር ቤት እየተሰቃዩ ነው

ሰኔ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በትሪፖሊ አካባቢ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እንደተናገሩት ሰሞኑን እንደ አዲስ በተጀመረው አፈሳ ቁጥራቸው ከ90 በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ተይዘው ታስረዋል። በአካባቢው በሚገኙ የተለያዩ እስር ቤቶች ከ500 ያላነሱ ኤርትራውያንና ኢትዮጵያውያን እንደሚገኙም ገልጸዋል። ኢትዮጵያውያኑ የተያዙት በህወጥ አዘዋዋሪዎች ሲሆን፣ ገንዘብ ካላመጡ እንደማይለቀቁ እንደሚነገራቸው ገልጸዋል፡፡ አንድ ከእስር ቤት ያመለጠ ወጣት ሲናገር፣ በእስር ቤቱ ውስጥ ዱላ የቀን ተቀን ህይወት ነው፣ ...

Read More »

ፍርድ ቤቱ በዞን ዘጠኝ አባላትና ጋዜጠኞች ላይ ለብይን ቀጠሮ ሰጠ

ሰኔ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት ፣ ልደታ ምድብ ሰኔ 8/2007 ዓም በዞን ዘጠኝ ጦማርያን እና ሶስቱ ጋዜጠኞች ላይ በቀረበው የሽብረተኝነት ክስ ላይ ብይን ለመስጠት ለሐምሌ 13/2007 ዓ.ም ቀጠሮ መስጠቱን ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል። ጦማርያኑና ጋዜጠኞቹ ጥቁር ለብሰው ፍርድ ቤት የተገኙ ሲሆን፣ ፍርድ ቤቱም ከዚህ ቀደም በቀረበለት የቪዲዮ ማስረጃ ላይ ውሳኔ ሰጥቷል። አቃቤ ህግ ...

Read More »