ነኅሴ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሽብርተኝነት ወንጀል ተከሰው በእስር ላይ የሚገኙት የመኢአድ ፓርቲ የአመራር አባላት በእስር ቤት ውስጥ ከፍተኛ ድብደባ እንደተፈጸመባቸው የአይን እማኞች ለኢሳት ገልጸዋል። ወጣት ተስፋየ ታሪኩ፣ ቀድም ብሎ በእስር ቤት ውስጥ እየተደበደቡ መሆኑን ለፍርድ ቤት ማመልከቱን ተከትሎ ፣ ፖሊሶች ዘቅዝቀው በጠመንጃው ሳንጃ በሽፋኑ ጀርባውን ደብድበውታል፣ እጁና እግሮቹም ተጎድተዋል። ተስፋየን ፍርድ ቤት አካባቢ እንዳገኘውና መደብደቡን ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የኢትዮጵያ ሰራተኞች የውጭ አገር ኩባንያዎች ባሪያዎች ሆነዋል ተባለ
ነኅሴ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቢቢሲ ሬዲዮ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ አስመልክቶ በሰራው ዘገባ ፣ የአገሪቱ ሰራተኞች በአለም ላይ እጅግ ዝቅተኛ የሆነ ክፍያ ከሚያገኙ አገሮች ቀዳሚ መሆናቸውን ጠቅሶ፣ የውጭ አገር ኩባንያዎች ሰራተኞቹን እንደ ባሪያ እንደያዙዋቸው ገልጿል። ከ11 ሚሊዮን በላይ ስራ አጥ ባለበት የሰራተኛውን የመጨረሻ የክፍያ ወለል ማስተካከል ፈታኝ መሆኑን የገለጸው ቢቢሲ፣ ወጣቱ በ50 ዶላር ወርሃዊ አማካኝ ክፍያ ህይወቱን ...
Read More »የኢትዮጵያ ወታደሮች ከአፍሪካ ኅብረት የሰላም አስከባሪ ጦር አሚሶም ተልኮ ውጪ እየተንቀሳቀሱ ነው ተባለ
ነኅሴ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ ወታደሮች በሶማሊያ ሂራን ክልል ውስጥ ከአፍሪካ ኅብረት የሰላም አስከባሪ ጦር፣ አሚሶም ተልኮ ውጪ እየተንቀሳቀሱ መሆኑን የአሚሶም ምድብ አራት የጦር አዛዥ የሆኑት አብዱራህማን አብዲ ዲምቢሊ ቅሬታቸውን አሰሙ። ጅቡቲያዊው የጦር አዛዥ ኮማንደር አብዱረህማን ፣ ካለ ህብረቱ ጦር ትእዛዝ በሂራን ግዛት የኢትዮጵያ ወታደሮች አልሸባብን ደምስሰው አካባቢውን ከተቆጣጠሩት በኋላ ለሶማሊያ መንግስት ወታደሮች አስረክበው እነሱ ...
Read More »የሙያ ብቃት ምዘና በአመለካከትና ክህሎት ሰፊ ክፍተት እንዳለበት ተጠቆመ፡፡
ነኅሴ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመላ ሃገሪቱ በ2001 ዓ.ም የተቋቋመው የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ኤጀንሲ የታሰበለትን ሃገራዊ ፋይዳ በተገቢው ሁኔታ ለማድረስ እንዳልቻለ የአማራ ክልል የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ኤጀንሲ ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ የሽዋስ ተናገሩ፡፡ ዳይሬክተሩ በክልሉ በልዩ ልዩ ቦታዎች በተካሄደው ውይይት ለተሳታፊዎች እንደገለጹት በአመለካከትና ክህሎት ዙሪያ ሰፊ ክፍተት አለ ብለዋል። መዛኝ የኤጀንሲውን ሰራተኞች በየጊዜው ለምዘና ለመላክ ...
Read More »የደቡብ ሱዳኑ ኢንፎርሜሽን ሚንስትር የስዩም መስፍንን አምባገነናዊ ሽምግልና እንደማይቀበሉት ገለፁ
ነኅሴ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሚኒስትሩ ሚካኤል ማኩዊ የምስራቅ አፍሪካ በየነ መንግስታት ኅብረት ኢጋድ ዋና አደራዳሪ የሆኑትስዩም መስፍን በተደራዳሪዎች ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድሩ ይሞክራሉ ሲሉ ወቀሳቸውን አሰምተዋል። ሚካኤል ማኩዊ ” የኢጋድ አደራዳሪዎች ደቡብ ሱዳንን የሙከራ ምድር ለማድረግ ይሞክራሉ።አንዳንዶቹ በጭራሽ ዓለማቀፋዊ ተቀባይነት የሌላቸው ናቸው።የግድ መፈረም አለባችሁ ብሎ ለተደራዳሪዎች አስገዳጅ ውል ማቅረብ፣ ካልፈረማችሁ እኛ አንጠቀምም እንደ ማለት ሲሆን ዓለማቀፋዊ ...
Read More »በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል በመንግስት ሃይሎች ግድያ እየፈጸመ ነው ተባለ
ኢሳት ዜና (ነሐሴ 12 ፣ 2007) በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል መንጌ ወረዳ የመንግስት ሃይሎች አርብ እለት በሰነዘሩት ጥቃት 12 ሰዎች ተገደሉ። ከሟቾቹ ውስጥ 5ቱ ህይወታቸው ያለፈው እስር ቤት ከተወሰዱ በኋላ በምግብ ተመርዘው እንደሆነ የቤኒሻንጉል ህዝቦች ነጻነት ንቅናቄ አስታወቀ። የቤኒሻንጉል ህዝቦች ነጻነት ንቅናቄ (ቤሕነን) ሊቀመመንበር አቶ አብዱልዋህድ መሃዲ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እንደገለጹት አርብ ነሐሴ 8 ቀን 2007 የመንጌ ወረዳ ነዋሪዎች በስርዓቱ ...
Read More »አንድ የህወሃት አባል በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ በሻንጣው ይዞ ሲገባ ለንደን ላይ ተያዘ
ነኅሴ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከፍርድ ቤት ጋር በተያያዘ ለጊዜው ስሙ እንዳይገለጽ የጠየቁ ምንጮች እንደገለጹት ፣ አንድ የህወሃት አባል 5 ሚሊዮን የእንግሊዝ ፓውንድ የሚገመት ጥሬ ገንዘብና ወርቅ በሻንጣው ይዞ ወደ ለንደን ሲገባ ጋትዊክ አየር ማረፊያ ላይ በፖሊሶች ተይዟል። ግለሰቡ ፍርድ ቤት ቀርቦአል። ዳኛው ” ይህን ያክል ገንዘብ እንዴት በሻንጣ ልትይዝ ቻልክ የሚል ጥያቄ ሲያቀርቡ ፣ ግለሰቡ ...
Read More »በለጋምቦ ወረዳ ውጥረቱ እንደቀጠለ ነው
ነኅሴ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ሳምንት በደቡብ ወሎ ለጋምባ ወረዳ ከዩኒቨርስቲ ግንባታ መቋረጥ ጋር በተያያዘ በተፈጠረ ለውጥ የተጀመረው ተቃውሞ በተለያዩ መንገዶች እየቀጠለ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። በተለያዩ አጎራባች ወረደዎችና ቀበሌዎች ህዝቡ መኪና መንገዶችን በድንጋይ በመዝጋትና መኪና እንዳይተላለፍ በማድረግ እንዲሁም በጋራ በመሰባስብና ድምጻቸውን በማሰማት ተቃውሞአቸውን ሲገልጹ የነበቱ ሲሆን፣ ዛሬም ዩኒቨርስቲው በሚገነባበት አካባቢ ተቃውሞ እንደነበር፣ ጉጉፍቱ አካበባ ...
Read More »በሽብር ወንጀል የተከሰሱት ድርጊቱን ፈጽመናል ወንጀለኞች ግን አይደለንም አሉ
ነኅሴ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ብርሃኑ ተክለያሬድ፣ እየሩሳሌም ተስፋው፣ ፍቅረማርያም አስማማውና ደሴ ካህሳይ ልደታ ፍርድ ቤት 14ኛ ወንጀል ችሎት ቀርበው ፣ የተጠቀሰውን ድርጊት መፈጸማቸውን ነገር ግን ወንጀለኞች አለመሆናቸውን ተናግረዋል። በወጣቶቹ ላይ የቀረበው ክስ ግንቦት 7 የተባለውን አሸባሪ ቡድን ለመቀላቀል ሲሄዱ ማካይድራ በተባለው የድንበር ከተማ ላይ ተይዘዋል የሚል ነው። ነገረ ኢትዮጵያ እንደዘገበው አንደኛ ተከሳሽ ብርሃኑ ተክለያሬድ፣ ‹‹ሀገሬ ...
Read More »20 ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተከሰሱ
ነኅሴ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፍርድ ቤት በቅርቡ ከፍተኛ ቅጣት የጣለባቸው የድምጻችን ይሰማ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት እንዲፈቱ የጠየቁ 20 ሙስሊም ኢትዮጵያውያን የሽብርተኝነት ክስ ተመስርቶባቸዋል። ህዝበ ሙስሊሙ በመንግስት ላይ እንዲነሳ ቀስቅሰዋል በሚል በ14ኛ ወንከል ችሎት የተከሰሱት ከድር መሃመድ፣ ነዚፍ ተማም፣ ካሊድ መሃመድ፣ ፉአድ አብዱልቃድር፣ ኢብራሂም ካሚል፣ አብዱ ጁባር፣ ሁሴን አህመድ፣ ሃሚድ ሙሃመድ፣ ቶፊቅ ሚስባህ፣ ዑስማን አብዱ፣ ...
Read More »