ነኅሴ ፳፪ (ሀያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኬንያ ሜሩ ግዛት ውስጥ በሕገወጥ የገቡ አርባ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን መያዙን የአካባቢው ፓሊስ አስታወቀ። ስደተኞቹ በሚዮኖዋ መንደር ውስጥ በሚስጥር ቤት ውስጥ ተደብቀው በአካባቢው ሕዝብ ጥቆማ ትብብር መያዛቸውን ፖሊስ ገልጿል። ስደተኞቹ ኬንያን አቋርጠው ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመሻገር የመጡ መሆናቸውን በቅርብ ጊዜም ሰማንያ ሕገወጥ ኢትዮጵያዊያን በተመሳሳይ መልኩ መያዛቸውን የጸጥታ ሰራተኞቹ አክለው ገልጸዋል ሲል የኬንያ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ስኳር ኮርፖሬሽን በዚህ አመት 7 ቢሊዮን ብር ኪሳራ ደረሰበት
ኢሳት ዜና (ነሐሴ 22 ፣ 2007) ከአራት አመት በፊት የተቋቋመውና አስር የስኳር ፋብሪካዎች ግንባታ ለማካሄድ ሃላፊነት የተሰጠው የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን በተጠናቀቀው የ 2007 አም በጀት አመት የሰባት ቢሊዮን ብር ኪሳራ እንደደረሰበት ምንጮች ለኢሳት ገለጹ። የሃገሪቱ ነባር የስኳር ፋብሪካዎች እንዲያስተዳድር ሃላፊነት ተሰጥቶት የነበረው ይኸው ኮሮፖሬሽን ለስራው ማስኬጃ ከተለያዩ የመንግስትና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጋር ለእቃ አቅርቦት መከፈል የነበረበትን ሶስት ቢሊዮን ብር በወቅቱ ...
Read More »እስካሁን 1.2 ቢሊዮን የጨረሰው ተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ለማለቅ ተጨማሪ ብድር ያስፈልገዋል ተባለ
ኢሳት ዜና (ነሐሴ 21 ፣ 2007) ግንባታው ለ 12 አመታት ያህል ሲካሄድ የቆየውና የእዳ መጠኑ 1.2 ቢሊዮን ብር አካባቢ የደረሰው የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ተጨማሪ ብድር ካልጸደቀለት በስተቀር ስራውን በተያዘለት እቅድ መሰረት እንደማይጀምር ምንጮት ለኢሳት ገለጡ። መንግስት የተንዳሆ የስኳር ልማት ፕሮዳክሽን በአምስት አመት የልማት እቅድ መሰረት ወደማምረት ደረጃ ለማሳደግ ቢጥርም ግንባታው በተለያዩ አስተዳደራዊ ችግሮች ሊያልቅ አለመቻሉን የልማት ባንክ ምንጮች ገልጸዋል። የህንዱ ...
Read More »በህወሃት ጉባኤ የአባይ ወልዱና የደብረጺዮን ቡድን አሸናፊ ሆኖ ወጣ
ነኅሴ ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ነባር አመራሮቹ በመመረጥና በመምረጥ መብት በድርጅቱ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ እንዲሳተፉ የፈቀደው ህወሃት፣ ከአቶ መለስ ዜናዊ ሞት በሁዋላ በስራ አስፈጻሚነት ሲያገለግሉ የነበሩ አብዛኞቹን መሪዎችን በድጋሜ መርጧል። አቶ አባይ ወልዱ የድርጅቱም የግንባሩም ሊቀመንበር ሆነው ሲመረጡ፣ ዶ/ር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል ደግሞ ምክትል ሆነው ተመርጠዋል። ቀድም ብሎ ህወሃትን ሊለቁ ነው በሚል ሲወራባቸው የቆዩት ወ/ሮ አዜብ መስፍን ...
Read More »አንድ የመከላከያ አባል የነበረ በፖሊሶች ተደብድቦ አይኑ ጠፋ
ነኅሴ ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሃምሌ 27 ቀን 2007 ዓም በደቡብ ክልል በጋሞጎፋ ዞን በጫኖ ሚሌ ቀበሌ ውብዬት ጩበሮ የተባለ የመከላከያ ሰራዊት አባል ፣ መከላከያን በመልቀቅ ወደ ቤተሰቦቹ ከተመለሰ ከሁለት ወር በሁዋላ፣ ፖሊሶች አንተ ተቃዋሚዎችን ትደግፋለህ ብለው በሰደፍ ደብድበው አንድ አይኑን እንዳፈሰሱት አባቱ አቶ ጩበሮ ጩኮ ለኢሳት ተናግረዋል። ወታደሩ ወደ ቀየው ከተመለሰ በሁዋላ፣ ከአባቱ ጋር እርሻ ...
Read More »በአዲስ አበባ ወረዳ 9 17 የንግድ ድርጅቶች ታሸጉ
ነኅሴ ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ነጋዴዎች ለኢሳት እንደገለጹት፣ የገዢው ፓርቲ ባለስልጣናት በድንገት በመምጣት በጉለሌ ክፍለከተማ ወረዳ ዘጠኝ ቀበሌ 02 የሚገኘውን የንግድ ድርጅታቸውን አሽገውባቸዋል። “በቂ ምክንያት ሳይኖርና በቂ የማስጠንቀቂያ ጊዜ ሳይሰጠን፣ ከአንድ ወር ላላነሰ ጊዜ ስራ ፈተን ቤተሰቦቻችን ለችግር ተጋልጠዋል” በማለት የሚናገሩት ነጋዴዎች፣ ጉዳዩን ለተለያዩ ባለስልጣናት ቢያመለክቱም መፍትሄ የሚሰጣቸው አላገኙም። የወረዳው የኢህአዴግ ጽ/ቤት ወኪል የሆኑት አቶ ተክለአብ፣ ...
Read More »የተቃዋሚ አባላትን እያደኑ ማሰሩ እንደቀጠለ ነው
ነኅሴ ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዛሬ ነሃሴ 21 ቀን 2007 ዓ.ም. በምዕራብ ጎጃም ዞን ሜጫ ወረዳ አብዮት ፋና ቀበሌ ሶስት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ታድነው መታሰራቸውን የዞኑ የፓርቲው አስተባባሪዎች ገልጸዋል፡፡ ሶስቱም የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ከሌሊቱ 11 ሰዓት ጀምሮ ቤታቸው በታጣቂ ተከቦ እንዳደረ የተገለፀ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት በቀበሌው ፖሊስ ጣቢያ ታስረው እንደሚገኙ ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል። ታድነው የታሰሩት የሰማያዊ ...
Read More »በሃማስ የታገተው ኢትዮ እስራኤላዊ ቤተሰቦች የጋዛን መተላለፊያ ዘጉ
ነኅሴ ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ዓመት መስከረም ወር ላይ በጋዛ ሰርጥ በሃማስ የታገተው ኢቲዮ እስራኤላዊ ወጣት አቭራም መንግስቱ ከሃያ በላይ የሚሆኑ ቤተሰቦቹ ልጃችን ይለቀቅ በማለት በጋዛ ኤርዝ መተላለፊያን ዘግተው ተቃውሟቸውን እያሰሙ ሲሆን የልጃቸውን መታገት በዓለማቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እንዲታወቅላቸውም ተማጽዕኖዋቸውን አሰምተዋል። የአቭራም ወንድም ”እኛ በነፃነት የመዘዋወር መብትን እናከብራለን፣ ሁላችንም ፍልስጤማዊያንም እስራኤላዊያንም ጭምር እኔ አሁን የምንጠይቀው ...
Read More »ህወሃቶች የአቶ መለስን የመተካካት ፖሊሲ ሲቀለብሱ ብአዴኖች ደግሞ አቶ በረከትን በማእከላዊ ኮሚቴ አባልነት ይዘው ለመጓዝ መሰኑ
ነኅሴ ፳ (ሀያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሟቹ ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ያስቀመጡት የመተካካት ፖሊሲ በህወሃት ነባር አመራሮች ሲተች፣ ብአዴኖች ፖሊሲውን ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ ማድረግ ባለመቻላቸው ግራ ተጋብተዋል። የአቶ መለስ የመተካካት ፖሊሲ በ2007 ዓም ሁሉም የድርጅቱ ነባር አመራሮች በአዳዲስ ወጣት አመራሮች ይተካሉ የሚል ነበር። ይሁን እንጅ ህወሃት እያካሄደ ባለው መደበኛ ጉባኤ በአቶ መለስ ወቅት ከአመራር ቦታቸው የተነሱት ነባር ታጋዮች በጉባኤው ...
Read More »በአቶ ማሙሸት አማረ የሀሰትና የተጠና ክስ መቅረቡን ጠበቃው ተናገሩ
ነኅሴ ፳ (ሀያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አይ ኤስ አይ ኤስን ለመቃወም መንግስት በጠራው ሰልፍ ላይ ህዝብን አነሳስቷል በሚል ክስ የተመሰረተበት አቶ ማሙሸት አማረ ነሃሴ 20/2007 ዓ.ም አራዳ ምድብ ችሎት ቀርቦ ክሱን ተከታትቷል። ከአራቱ ምስክሮች መካከል ሶስቱ ‹‹አቶ ማሙሸት አማረ 300 ብር ከፍሎ ሰልፍ እንድንወጣ አድርጎናል›› ሲሉ መስክረዋል፡፡ ይሁንና ምስክሮቹ ከማሙሸት ጋር በተገናኙበት ወቅት እንዲሁም ገንዘቡ ሲሰጣቸው፣ ሰልፉ ያለፈባቸውን ...
Read More »