.የኢሳት አማርኛ ዜና

የሃዘን መግለጫ

መስከረም 27, 2008 አንጋፋው ጋዜጠኛ፣ ሃያሲ፣ ደራሲና፣ የፖለቲካ ተንታኝ ሙሉጌታ ሉሌ በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት በመለየታቸው የኢሳት ማኔጅመንት፣ ጋዜጠኞችና፣ መላው የኢሳት ቤተሰብ ከፍተኛ ሃዘን ተሰምቶታል። አቶ ሙሉጌታ ሉሌ በተባ ብዕራቸው ሃገራዊ ፍቅርን፣ አንድነትን፣ ነፃነትንና፣ ፍቅርን የሰብኩ፥ በአንደበታቸው ስለኢትዮጵያ የመሰከሩ፣ እስከመጨረሻ እስትንፋሳቸው ድረስ ኢትዮጵያን ያገለገሉና፣ ኢትዮጵያን ተቀምተው በስደት የቀሩ ሃገራዊ ሃብት ነበሩ። የሙያ አባታችን ሙሉጌታ ሉሌ የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥንና ሬዲዮ (ኢሳት) ...

Read More »

በ በቆጂ በተነሳው ተቃውሞ ብዙ ወጣቶች ታሰሩ

መስከረም ፳፰ (ኅያ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኦሮምያ ክልል በ በቆጂ ከተማ ከቤት ማፍረስ ጋር በተያያዘ በተነሳ ተቃውሞ ከ20 በላይ ወጣቶች በፖሊሶች ተደብድበው ሆስፒታል የገቡ ሲሆን፣ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ነዋሪዎች ደግሞ ተደብድበዋል። ግጭቱ የተከሰተው የወረዳው ባለስልጣናት ቤት አፍራሽ መኪኖችን በመላክ ህገወጥ ቤቶች ያሉዋቸውን ቤቶች ማፍረስ መጀመራቸውን ተከትሎ ሲሆን፣ ነዋሪዎች ድንጋይ በመወርወር ተቃውሞቸውን ገልጸዋል። አንድ የፖሊስ መኪናም በድንጋይ ተመታለች። ...

Read More »

በሃመር ወረዳ በመንግስት ባለስልጣናትና በነዋሪዎች መካከል መተማመን ሊፈጠር አልቻለም

መስከረም ፳፰ (ኅያ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከጸጥታ እና ከደህንነት ዋስትና ማጣት ጋር በተያያዘ፣ ስራ ያቋረጡት የመንግስት ሰራተኞች፣ ከወረዳው ባለስልጣናት ጋር ተናንት የተወያዩ ቢሆንም፣ መተማመን ላይ ባለመድረሳቸው አብዛኞቹ ዛሬም ስራ ሳይጀምሩ ቀርተዋል። አንዳንድ የመንግስት ሰራተኞች በግዴታ ስራ እንዲጀምሩ ቢደረግም፣ ብዙዎቹ በአድማው ቀጥለውበታል። የሀመር ወረዳ አርብቶአደሮች በየጊዜው በሚሰነዝሩት ጥቃት የፖሊስ፣ የመከላከያና የልዩ ሃይል አባላትን ጨምሮ ነዋሪዎች ተገድለዋል። በየጊዜው የሚፈጸመው ...

Read More »

በመጪው ወር የሚጠበቀው ከፍተኛ ዝናብ ተጨማሪ አደጋ ደቅኗል

መስከረም ፳፰ (ኅያ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ የተከሰተውና ከ4 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ ሕዝብ ለምግብ እጥረት የዳረገው የድርቅ ችግር በቀጣይ ወራትም ሊስፋፋ እንደሚችል ከፍተኛ ስጋት ፈጥሯል። ከብሔራዊ ሚቲሮዎሎጂ ኤጀንሲ የወጡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ከኤልኒኖ ክስተት ጋር ተያይዞ ከቀጣይ ጥቅምት ወር ጀምሮ ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍሎች እንደሚያጋጥም ዓለም አቀፍ ትንበያ መኖሩን በመጥቀስ፣ ይህ ሁኔታ ድርቁ በሌሎች አካባቢዎች ...

Read More »

አንድ የቀድሞ የመኢአድ አባል በደህንነቶች በከፍተኛ ሁኔታ ተደበደበ

መስከረም ፳፰ (ኅያ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በዳንግላ ዙሪያ ነዋሪ የሆነው አቶ ደግአረገ በአካባቢው ያሉ ወጣቶችን በትጥቅ ትግል ለሚታገሉ ሃይሎች እየመለመልክ ትልካለህ በሚል አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ ተደብድቧል። ማንነታቸውን በውል ለይቶ የማያውቃቸው ሰዎች አይኑን በጨርቅ ሸፍነው ወደ ባህርዳር እንደወሰዱትና በመጨረሻም መረጃ ሲያጡ ፣ አይኑን ሸፍነው እንደለቀቁት ገልጿል።

Read More »

በዲመካ የተጀመረው የስራ ማቆም አድማ 3ኛ ቀኑን ያዘ

መስከረም ፳፯ (ኅያ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ክልል በሃመር ወረዳ በዲመካ ከተማ ማክሰኞ የተጀመረው የስራ ማቆም አድማ እስከ ዛሬ የቀጠለ ሲሆን፣ የዞኑ ባለስልጣናት ነዋሪውን ለማነጋገር ስብሰባ ጠርተዋል። የስራ ማቆም አድማው መንስኤ ካለፉት 6 ወራት ጀምሮ በአካባቢው በመካሄድ ላይ ያለው ግጭት ስራቸውን ለመስራት ስላላስቻላቸው ነው። የመንግስት ሰራተኞች እንደሚሉት ካለፈው ሰኔ ወር ጀምሮ በወረዳው ባሉ ቀበሌዎች ተዘዋውሮ ስራ መስራት ...

Read More »

በሳዑዲ በሃጂ ስነ-ስርዓት ላይ የሞቱ ኢትዮጵያውያን በሀገር አቀፍ ደረጃ አለመታሰባቸው ሙስሊሞችን አሳዝኗል

መስከረም ፳፯ (ኅያ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከሁለት ሳምንት በፊት በሳዑዲ አረቢያ ሚና አካባቢ በሀጂ ስነ-ስርዓት ወቅት በተከሰት ግፊያና መጨናነቅ በደረሰ አደጋ ህይወታቸውን ያጡ ኢትዮጵያዊያን ቁጥራቸው ከ47 በላይ የበለጠ ቢሆንም ፣ የኢህአዴግ መንግስት ለዚህ ከባድ ሐዘን የሰጠው ትኩረት ማነስ እንዳሳዘናቸው ዘጋቢያችን ያነጋገራቸው በአዲስአበባ የሚኖሩ ሙስሊሞች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመጅሊሱን ወሬ በመያዝ ለሞቱት ወገኖች መጽናናትን ይመኛል ከማለት ...

Read More »

የዞን 9 ጦማሪያን “ዳኞች ስልጠና ላይ ናቸው” በሚል ምክንያት ፍርድ ቤት ለ38ኛ ጊዜ ተቀጠሩ

መስከረም ፳፯ (ኅያ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በነሶልያ ሽመልስ የክስ መዝገብ በሽብረተኝነት በተከሰሱት ወጣት ጸሃፍት ላይ ውሳኔ ይሰጣል ተብሎ ሲጠበቅ ዳኞች “አዳማ ስልጠና ላይ ናቸው” በሚል ለ38 ኛ ጊዜ እንዲራዘም ተደርጓል። ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ለመስጠት ለ5ኛ ጊዜ ቀጠሮ አራዝሟል። በአንድ መዝገብ ከተከሰሱት መካከል የተወሰኑት መለቀቃቸው፣ ቀሪዎቹም ይለቀቃሉ የሚል ተስፋ አሳድሮ ነበር። ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድን ጸሃፊዎቹ እንዲፈቱ ጥያቄ ...

Read More »

አልሸባብ በደፈጣ ውጊያ ሁለት የኢትዮጵያ የጦር መኪኖችን ማውደሙን ገለፀ

መስከረም ፳፯ (ኅያ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሶማሊያ ሰላም አስከባሪ ሰራዊት አሚሶል ስር ያለውን ንብረነታቸው የኢትዮጵያ ጦር ሰራዊት የሆኑትን ሁለት ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችን በደቡባዊ ምዕራብ ሶማሊያ በጌዶ ግዛት በደፈጣ ውጊያ ማውደሙን አልሸባብ አስታውቋል። ጥቃቱ የተፈፀመው በአሊላን መንደር ውስጥ በአልሸባብና በኢትዮጵያ ሰራዊት መሃከል ለሰዓታት የቆየ የተኩስ ልውውጥ ተደርጎ ነው። በአርፒጂ የጦር መሳሪያ ተሽከርካሪዎቹ መመታታቸውን የአካባቢው የዐይን እማኞች ተናግረዋል። በአልሸባብ ጥቃት ...

Read More »

በዲላ ከተማ መብራት በመጥፋት ነዋሪዎች ችግር ላይ መውደቃቸውን ተናገሩ

መስከረም ፳፯ (ኅያ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ላለፉት 4 ቀናት ያለማስጠንቀቂያ የተቋረጠው ኤሌክትሪክ፣ በንግድ ቤቶች እና በነዋሪዎች የእለት ተለት ህይወት ላይ ችግር ማስከተሉን ነዋሪዎች ገልጸዋል። የኤሌክትሪክ አገልግሎቱ የተቋረጠበት መንስኤ ለህዝቡ አለመገለጹንም ተናግረወዋል። ከዚህ በፊት በከተማው በተደጋጋሚ የ ኤሌክትሪክ መቋረጥ የሚከሰት ሲሆን ፣ ያሁኑ ደግሞ የተለየ ነው ሲሉ ነዋሪዎች በምሬት ይገልጻሉ። በከተማው በሳምንት አንድ ቀን ይቀርብ የነበረው የውሃ ስርጭትም ...

Read More »