ኢሳት ዜና (ጥቅምት 2 ፣ 2008 ዓም) በኢትዮጵያና ግብጽ መካከል በአባይ ግድብ ዙሪያ ሊካሄድ የነበረው ድርድር መዘግየትን ተከትሎ፣ የግብፁ ፕሬዚዳንት አብደል ፋታህ አልሲሲ ከሱዳን ጋር የሚመክር የልዑካን ቡድን ወደ ሃገሪቱ ላኩ። በሃገሪቱ የመስኖ ልማት ሚኒስትር ሆሳም ሞግሃዚ የተመራው ይኸው ልዩ የልዑካን ቡድን፣ ከፕሬዚዳን አልሲሲ የተላከን ልዩ መልዕክት በመያዝ ከሱዳን ባለስልጣናት ጋር ለመምከር ካርቱም መግባቱን አል-አህራም የተሰኘ የግብጽ ጋዜጣ ዘግቧል። ግብፅ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በሶማሊያ በኢትዮጵያ ሰራዊትና አልሻባብ መካከል ከፍተኛ ውጊያ መካሄዱ ተገለጸ
ኢሳት ዜና (ጥቅምት 2, 2008ዓም) በቅርቡ ወደሶማሊያ የተሰማራው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በደቡባዊ የሃገሪቱ ክፍል ለሁለተኛ ሳምንት ከባድ ውጊያ ኣያካሄደ ኣንደሚገኝ የሶማሊያ ወታደራዊ ባለስልጣናት ትናንት ገለጹ። ለሁለተኛ ሳምንት ቀጥሎ የሚገኘው ግጭት ልዩ ስሙ አልዩ ዲዮ በተባለ ደቡባዊ ምዕራብ የሶማሊያ አካባቢ እየተካሄደ እንደሚገኝ እነዚሁ ወታደራዊ ባለስልጣናት ለጋዜጠኞች አስታውቀዋል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስቴር በበኩሉ በአካባቢው እየተካሄደ ባለው ውጊያ፣ የኢትዮጵያ አየር ሃይልና የሶማልያ ብሄራዊ ጦር ...
Read More »በኢትዮጵያ የእለት ደራሽ ዕርዳታ የሚሹ ወገኖች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ አሻቀበ፡፡
ጥቅምት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስትና አለማቀፍ ድርጅቶች በሰጡት መረጃ መሰረት የተረጂው ጠቅላላ ቁጥር 8 ነጥብ 2 ሚሊየን ደርሷል፡፡ መረጃዎች ግን ከዚህ በላይ መሆኑን ያመለክታሉ። የተጠቀሰው አሃዝ ቀደም ሲል በሴፍቲኔት ፕሮግራም ታቅፈው የሚረዱ ወደ 3 ነጥብ 8 ሚሊየን ኢትዮጵያዊን ወገኖችን ይጨምራል ተብሎአል። ይሁን እንጅ መንግስት ያዘጋጀው እና አለማቀፍ ለጋሽ ድርጅቶች የሚጠቅሱት ሰነድ በምግብ ለስራ የታቀፉ ዜጎች ቁጥር ...
Read More »በአዳ- በርጋ ወረዳ 30 ወጣቶች ታሰሩ
ጥቅምት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኦሮምያ ክልል በምዕራብ ሸዋ ዞን አዳ በርጋ ወረዳ 30 ወጣቶች በኦሮምያ ልዩ ሃይሎች በሌሊት ታፍነው መወሰዳቸውን ሂውማን ራይትስ ሊግ ኦፍ ዘ ሆርን ኦፍ አፍሪካ ገለጸ። ድርጅቱ ለኢሳት በላከው መግለጫ አብዛኞቹ የታሰሩት ወጣቶች የናይጀሪያዊው ባለሀብት ንብረት የሆነው የዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ ሰራተኞች እና ለእረፍት ወደ ቤተሰቦቻቸው የሄዱ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ናቸው። ወጣቶችን በማፈን መመሪያ የሰጠው ...
Read More »ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የእስር ቤት አያያዙ አስከፊ መሆኑን የሙያ አጋሮቹ ገለጹ
ጥቅምት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሽብር ወንጀል ተከሶ በእስር ላይ የሚገኘው ታዋቂው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የእስር ቤት አስተዳዳሪዎች በሚያሳድሩበት ጫና ለተጨማሪ ስቃይ እየተዳረገ መሆኑን የሙያ አጋሮቹ ተናግረዋል። የቀለም ቀንድ ጋዜጣ ስራ አስኪያጅ አቶ አበበ ውቤ እንደገለጹት፣ እስክንድርን ከሁለት የቅርብ የቤተሰብ አባላት ውጭ ሌሎች ሰዎች እንዳይጥቁት ተከልክለዋል። በሃይማኖት አባቶችም ሆነ በጠበቃ እንደማይጎበኝ የገለጸው ጋዜጠኛ አበበ፣ በእስር ቤት ውስጥ ...
Read More »አዳማ በ6 አመታት ውስጥ 7ኛው ከንቲባ ተሾመላት
ጥቅምት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኦህዴድ ላለፉት 2 አመታት ከተማዋን ሲመሩ የነበሩትን አቶ አብርሃም አዱላን ወደ ክልል ቢሮ በማዛወር የሻሸመኔ ከንቲባ የሆኑትን ለከተማዋ ከንቲባ አድርጎ ሾሟል። አዲሱ ከንቲባ በሻሸመኔ የሚገኙ ሙስሊም ኢትዮጵያውያንን በማሰቃት የሚወነጀሉ ሲሆን፣ ለአዳማ የተወሳሰበ ችግር መፍትሄ ያመጣሉ ተብሎ እንደማይታመን ምንጮች ይገልጻሉ። ነባሩ ከንቲባ፣ በደባል ሱሶች በመጠመድ ያለፉትን ሁለት አመታት ይህ ነው የሚባል ስራ ሳይሰሩና ...
Read More »በቴፒ አንድ የፖሊስ አባል ሲገደል አምስት ፖሊሶች መታገታቸው ተሰማ
ጥቅምት ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለአመት የዘለቀው የቴፒ ግጭት በአካባቢው ለሰፈረው የፌደራል ፖሊስ እና ለፌደራል ባለስልጣናት እንቆቅልሽ ሆነ በቀጠለበት በዚህ ወቅት፣ ባለፈው ቅዳሜ ከሌሊቱ 6 ሰአት ከ45 ደቂቃ ላይ ሚሊኒየም ጎዳና ላይ ወይም ሚካኤል አካባቢ ካሳሁን የተባለ የከተማው ፖሊስ አባል ተገድሏል። ፖሊሱ በቅርቡ ለከተማው ተመድቦ የመጣ ነበር። እርምጃውን የወሰዱት ራሳቸውን የቴፒ ወጣቶች ብለው የሚጠሩ ታጣቂዎች ናቸው። ታጣቂዎቹ ...
Read More »በፍቼ ከተማ የኦሮምያ ፖሊስና የመከላከያ አባላት ተጋጩ
ጥቅምት ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ቅዳሜ በተነሳው ግጭት ከፖሊስና ከመከላከያ አንዳንድ ወታደሮች ቆስለዋል። የግጭቱ መንስኤ ሁለት የመከላከያ ፖሊስ አባላት በፖሊሶች መደብደባቸው ነው። ከዚህ ቀደም አንድ ፈጥኖ ደራሽ ፖሊስ ፍቼ አካባቢ ሰፍሮ የሚገኘውን የመከላከያ ሰራዊት አባል ከገደለው በሁዋላ፣ በመከላከያና በፖሊስ መካከል ለወራት የዘለቀ ቁርሾ እንዲፈጠር አድርጓል። ባለፈው ቅዳሜ ሁለት የመከላከያ ሰራዊት አባላት በከተማው እየተዝናኑ በነበረበት ወቅት፣ ፖሊሶቹ ...
Read More »ለምዕራብ አርማጮኾ ነዋሪዎች በጤና ዙሪያ ለሚሰጠው አገልግሎት ገዢው መንግስት በቂ በጀት አለመመደቡ በነዋሪው ላይ ችግር እየፈጠረ መሆኑ ተነገረ፡፡
ጥቅምት ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሃገሪቱ ከሚገኙ አምራች አካባቢዎች አንዱ በሆነው በየዓመቱ ከሰኔ እስከ ህዳር ወር ድረስ ከፍተኛ የሰራተኛ ቁጥር የሚያስተናግደው የምዕራብ አርማጮኾ ወረዳ ውስጥ በሚገኙ ቀበሌዎች የሚገኙ የጤና ተቋማት ተገቢውን አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችላቸውን በጀት የክልሉ መንግስት ባለመመደቡ በየአመቱ ተገቢውን አገልግሎት መስጠት እንዳልቻሉ የወረዳው የጤና አመራሮችና ባለሙያዎች ተናገረዋል፡፡ በምዕራብ አርማጮኾ ወረዳ ያለው ነዋሪ አርባ አምስት ሽህ አካባቢ ...
Read More »የአንጋፋው ጋዜጠኛ የአቶ ሙሉጌታ ሉሌ የቀብር ስነ-ስርአት በአሜሪካ ቨርጂኒያ ግዛት ተፈጸመ
ኢሳት ዜና (ጥቅምት 27 ፣ 2008) በዋሺንግተን ዲሲ አቅራቢያ አርሊንግተን በተካሄደው በዚህ የቀብር ስነ-ስርአትና በአሌክሳንድሪያ ከተማ በተከናወነው የጸሎት ፕሮግራም ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ መገኘቱንም ለማየት ተችሏል ። ከአውሮፓ፣ ከካናዳና፣ ከተለያዩ የአሜሪካ ግዛት የመጡ እንዲሁም በዋሺንግተን ዲሲ ዙሪያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት የጸሎትና የቀበር ስነ-ስርአት የአቶ ሙሉጌታ ወዳጆች ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል። የአንጋፋው ጋዜጠኛና ደራሲ እንዲሁም የፖለቲካ ተንታኝ የአቶ ሙሉጌታን ሕልፈት በተመለከተ በተዘጋጀው የጸሎት ...
Read More »