ጥቅምት ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአፍሪካ ሕብረት የሰላም አስከባሪ ጦር አሚሶም ስር እንደ አውሮፓዊያን ዘመን አቆጣጠር በ2012 ዓ.ም የሴራሊዮን መከላከያ ሰራዊት አባል በመሆን በደቡባዊ ሶማሊያ በግዳጅ ላይ እያለ ሕይወቱን ላጣው ሴራሊዮናዊ ወታደር ፣ የአፍሪካ ሕብረት የሰጠውን የሃምሳ ሽህ ዶላር የደም ካሳ የሴራሊዮን የመከላከያ ሚንስቴር የሆኑት ሌቴናል ጄኔራል ሳሙኤል ኦማር ዊሊያምስ ለሟቹ ባለቤት በክብር ስነስርዓት ገንዘቡን አስረክበዋል። ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ሰመጉ ከአንድ አመት በፊት 65 ሰዎች የየረር ጎሳ አባላት መገደላቸውን አረጋገጠ
ጥቅምት ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቀድሞው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ የአሁኑ ሰመጉ ኢሳት ከአንድ አመት በፊት የሰራውን፣ በሶማሊ ክልል በየረር ጎሳ አባላት ላይ የደረሰውን እልቂት የተመለከተውን ዘገባ ሰራተኞቹን ወደ ስፍራው ልኮ ያረጋገጠበትን ዘገባ ይፋ አድርጓል። ኢሳት ጥቃቱ እንደተፈጸመ ወዲያውኑ ዜናውን ይፋ አድርጎ የነበረ ሲሆን ፣ በታህሳስ ወር 2006 ዓም የየረር ባሪ የአገር ሽማግሌዎችን አነጋግሮና ለጠቅላይ ሚኒስትር ...
Read More »በአዲስ አበባ በርካታ ፖሊሶች መልቀቂያ አቀረቡ
ጥቅምት ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት የፖሊስ ምንጮች እንደገለጹት አንድ የአየር ጤና የፖሊስ ባልደረባ በህክምና እጦት መሞቱን ተከትሎ፣ የክፍለከተማው ፖሊሶች ስራ በማቆም ተቃውሞአቸውን ከገለጹ በሁዋላ፣ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች ፖሊሶች መልቀቂያ አስገብተዋል። የመቀሌ ከተማ ተወላጅ የሆነው ኦፊሰር የማነ በኩላሊት ህመም ሲሰቃይ ከቆዬ በሁዋላ፣ በፖሊስ ሆስፒታል ተገቢውን ህክምና ባለማግኘቱ፣ በግል ለመታከም 16 ሺ ብር ቢጠይቅም ለማግኘት አልቻለም። ይህን ...
Read More »አልሸባብ በኢትዮጵያ ወታደራዊ ተሽከርካሪ ላይ በፈጠረው ጥቃት በርካታ የሰራዊት አባላት ሙትና ቁስለኛ ሆኑ
ጥቅምት ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሂራን ግዛት ዋና ከተማ በሆነችው በለደወይኒ ፣ የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት ወታደሮችን ጭኖ ሲጓዝ በነበረ ወታደራዊ ተሽከርካሪ ላይ አልሽባብ ባደረሰው የደፈጣ ውጊያ ጥቃት ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ ወታደሮች መገደላቸውን የአካባቢውን የዓይን እማኞችን ጠቅሶ ሸበሌ ሬዲዮ ዘግቧል። ከማክሰኞ ከሰዓት በኋላ ጀምሮ እስከ ረቡዕ ጠዋት ድረስ በአካባቢው አዲስ ውጊያ መቀስቀሱንና በሁለቱ አንጃዎችና በሕዝቡም መሃከል ...
Read More »በመንግስት ወጪ ለብአዴን ከተማ አቀፍ ድግስ ተዘጋጀ
ጥቅምት ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ መስተዳድር ስር ባሉ የመንግስት መ/ቤት ውስጥ የሚገኙ የብአዴን አባላትና ደጋፊዎች ስለ ብአዴን የትግል ታሪክ እና ድርጅቱ በአሁኑ ወቅት ለኢህአዴግ እያደረገ ስላለው አስተዋጽኦ፣ ከዚህ ቀደም ብአዴን ስላበረከተው ድርጅታዊ አስተዋጽኦ እንዲሁም የክልሉ ህዝብ ለድርጅቱ ያበረከተው አስተዋጽኦ የጎላ ነበር የሚል አጠቃላይ ይዘት ያለው እውቅና ለመስጠት በሚል የተዘጋጀውን ከተማ አቀፍ ድግስ የአዲስ አበባ ...
Read More »የልማት ኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ከአዲስ ዘመን ጋዜጠኞች ጋር በፈጠሩት ጸብ ሰራተኛው እየታመሰ ነው
ጥቅምት ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአዲስ ዘመን ጋዜጠኞች ለዜና ዝግጅት በፌደራል ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ኤጀንሲ ባመሩበት ወቅት ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ገብረመስቀል ጫላ ” ልማታዊ ጋዜጠኛ ማሟላት የሚገባውን ስነ ምግባር ፈጽሞ የላችሁም የሚል ቁጣና ማስፈራሪያ አዘል” ንግግር የተናገሩዋቸው ሲሆን፣ ጋዜጠኞችም ” በድርጅቱ ውስጥ የመልካም አስተዳደር ችግር አለ ብለው ሰራተኞችን አነጋግረው ከዘገቡ በሁዋላ፣ ዋና ዳይሬክተሩ በገዛ ስልጣናቸው ...
Read More »በደቡብ አፍሪካ ታግተው የተወሰዱ ሁለት ኢትዮጵያዊያን ለጥቂት ከሞት ተረፉ
ጥቅምት ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ዓመት በደቡብ አፍሪካ በአስከፊ ሁኔታ በስደተኞች ላይ ያነጣጠረው ግድያና ዝርፊያ ድጋሜ የማገርሸት አዝማሚያው ምልክቶች ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ እየታየ ሲሆን፣ በቀድሞዋ ዋና ከተማ ጆሃንስበርግ ውስጥ ታግተው የተወሰዱ ሁለት ኢትዮጵያዊያን በፖሊስ ጣልቃገብነት ለጥቂት ከሞት ተርፈዋል። የግል ሱቅ በመክፈት ሥራ የሚተዳደረው ፈይሳ ሊሬና ጓደኛው በሁለት አጋቾች ከስራ ቦታቸው ታግተው ከከተማ ውጪ ከተወሰዱ በኋላ ...
Read More »የኤሌክትሪክ ታሪፍ መጨመር የዋጋ ንረት ማስከተሉ አይቀርም ተባለ
ኢሳት (ጥቅምት 24 2008) የኢትዮጵያ መንግስት ኤለክትሪክ አገልግሎት ታሪፍን ከ 50 በመቶ በላይ ለመጨመር መወሰኑ ከተጠቃሚው ህዝብና ባለሀብቶች ተቃውሞ እንደገጠመው ተገለጠ። አገልግሎቱ ለበርካታ አመታት በመንግስት ድጎማ መቆየቱን የገለጸው የኢትዮጵያ ኤለክትሪክ ሀይል መስሪያ ቤት በበኩሉ በአሁኑ ወቅት ቢያንስ ወጪውን የሚሸፍን ታሪፍ በማስፈለጉ 50 በመቶና ከዚያም በላይ ሊደርስ የሚችል ጭማሪ በቅርቡ ተግባራዊ እንደሚደረግ ይፋ አድርጓል። በኤሌክትሪክ አገልግሎት መቆራረጥ ለአመታት ያህል ቅሬታቸውን ሲያቀርቡ ...
Read More »የአቶ ፋንታሁን ልጅና አንድ የሰማያዊ የምክር ቤት አባል በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ
ጥቅምት ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአንድነት መግባባትና መተባበር ሊቀመንበር የሆኑት የአቶ ፈንታሁን ብርሃኑ የ13 አመት ሴት ልጅ በአንድ ወጣት በስለት በአሰቃቂ ሁኔታ ስትገደል፣ ሌላው የሰማያዊ ፓርቲ የምክር ቤት አባል አቶ አበራ ሃይለማርያምም በዚሁ ወጣት ተገድለዋል። አቶ ፋንታሁን ለኢሳት እንደተናገሩት ጎረቤታቸው የሆኑት አቶ አበራ የተገደሉት ምናልባትም ጩኸት ሰምተው ልጃቸውን ለመታደግ በመሞከራቸው ሳይሆን አይቀርም። ወጣቱ ግድያውን የፈጸመው ትናንት ...
Read More »ብአዴን የተነሳበትን አቅጣጫ መሳቱ ተነገረ፡፡
ጥቅምት ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ብአዴን በአሁኑ ጊዜ የደረሰበት ደረጃ ሁሉንም ነገር በዘመድ አዝማድ የሚሰራበት የተሳሳተ አቅጣጫ የተከተለበት ሁኔታ ላይ መድረሱን ነባር ታጋዮች ተናገሩ፡፡ ከመጀመሪያዎቹ የትግል ዓመታት ጀምረው እስከ ድሉ ማግስት ድረስ ለድርጅታቸው ታማኝ በመሆን የአካልና የህይወት መስዋዕትነት የከፈሉ የቀድሞ ታጋዮች እንደተናገሩት ፤በስርዓቱ ከጥቃቅን ነገሮች ጀምሮ እሰከ ከፍተኛ ደረጃ ያሉ ጉዳዮች ካለሙስና የማይሰራበት ደረጃ መድረሱ እንዳሳዘናቸው ...
Read More »