.የኢሳት አማርኛ ዜና

በአ/አ የነዳጅ እጥረት ተከሰተ ፡፡

ታኀሳስ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በከተማዋ የሚገኙ የተለያዩ ማደያዎች ነዳጅ በሚፈልጉ አሽከርካሪዎች ተጨናንቀው ውለዋል። እንዲህ አይነቱ ክስተት አልፎ አልፎ የሚያጋጥም ቢሆንም፣የዛሬው ከሌሎቹ ጊዜያት የሚለየው በበርካታ ማደያዎች ነዳጅ ባለመኖሩ ነው፡፡ የችግሩ ምክንያት በግልጽ ባይታወቅም አንዳንድ ምንጮች በኦሮሚያ አንዳንድ አካባቢዎች ከተከሰተው የጸጥታ ችግር ጋር በተያያዘ ነዳጅ መግባት ባለመቻሉ ነው ብለዋል።

Read More »

በኦሮምያ የሚካሄደው ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው።

ታኀሳስ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በምእራብ አርሲ ዞን ከሻሸመኔ በ60 ኪሜ ርቀት ላይ በምትገኘዋ አዳባ ከተማ ከፍተኛ ተቃውሞ የተካሄደ ሲሆን፣ የጸጥታ ሃይሎች በወሰዱት እርምጃ አንድ ሰው በጥይት መመታቱ ታውቃል። የቀበሌ ጽህፈት ቤቱ እና የወረዳው የፍርድ ቤት መዝገብ ሙሉ በሙሉ በቃጠሎ ወድሟል። ተመሳሳይ ተቃውሞ በነቀምትም በመካሄድ ላይ ሲሆን፣ ነዋሪዎች ወደ አምቦ የሚወስደው መንገድ በመዝጋት ተሽከርካሪዎች እንዳይተላለፉ አድርገዋል። ...

Read More »

በአንዋር መስኪድ ቦንብ ፈንድቶ ሰዎች ቆሰሉ

ታኀሳስ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በታላቁ አንዋር መስጊድ የሶላት ጸሎት በማድረስ ላይ በነበሩ ሙስሊም ዜጎች ላይ በደረሰ ጥቃት ቁጥራቸው በውል ያልተወቀ ሰዎች ተጎድተው ወደ ተክለሃይማኖት ሆስፒታል ተወስደዋል። አደጋውን ማን እንዳደረሰው የታወቀ ነገር የለም።ፖሊሶች በአካባቢው ተገኝተው ሲያጸዱ መታየታቸውን የአይን እማኞች ገልጸዋል።

Read More »

በሰሜን ጎንደር ዞን በተነሳው ግጭት ከ10 ያላነሱ ሰዎች መገደላቸው ተሰማ

ታኀሳስ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ገዢው ፓርቲ ሆን ብሎ እንደቀሰቀሰው በሚነገረው ግጭት ከትናንት ጀምሮ ከ10 በላይ ሰዎች የተገደሉ ሲሆን፣ የጎንደር መተማ መንገድ በመዘጋት የትራንስፖርት አገልግሎት ተቋርጧል። የመንግስት ካድሬዎች በቅማንትና አማራ መካከል ግጭት እንዲነሳ ለማድረግ ሰሞኑን ካድሬዎቹ መሳሪያ ታጥቀው ሰላማዊ ሰልፍ እንዲያደርጉ ተፈቅዶላቸው ነበር። ምንም እንኳ ህገመንግስቱ የጦር መሳሪያ ታጥቆ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ እንደማይቻል የሚደነግግ ቢሆንም፣ ካድሬዎች ...

Read More »

የፌደራል ፖሊሶችና የመከላከያ አባላት ሰላማዊ ተቃውሞ በሚያደርጉ ዜጎች ላይ ከባድ እርምጃ ወሰዱ

ኀዳር ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በወሊሶ ላለፉት አምስት ቀናት ሲካሄድ የነበረው ተቃውሞ ተጠናከሮ የቀጠለ ሲሆን፣ ከሰአት በሁዋላ የፌደራል ፖሊስ አባላት እርምጃ መውሰድ ጀምረዋል። በሰላማዊ ዜጎች ላይ በቀጥታ በመተኮስ በርካታ ቁጥር ያላቸው ነዋሪዎች ቆስለው ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል። እስካሁን አንድ ሰው መሞቱን ለማወቅ ቢቻልም፣ በሞትና በህይወት መካከል ያሉ በርካታ ወጣቶችና አዛውንቶች ሳይቀር መኖራቸው ታውቋል። ነዋሪዎቹ የውስጥ ለውስጥ መንገዶችንና ...

Read More »

በሰሜን ጎንደር ኢህአዴግ ያስታጠቃቸው ሰዎች በሰላማዊ ሰዎች ላይ ተኩስ ከፍተው ከፍተኛ ጉዳት አደረሱ

ኀዳር ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ታማኝ የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት በሰሜን ጎንደር መተማ ወረዳ ገዢው ፓርቲ ከተለያዩ አካባቢዎች አሰባስቦ መሳሪያ ያስታጠቃቸው ሰዎች አማራና ቅማንት በሚል ከፋፍሎ ግጭት ማስነሳቱን ተከትሎ ከባድ ጉዳት ደርሷል። ግጭቱ ሆን ተብሎ የተቀነባበረ ነው የሚሉት ምንጮች፣ ግጭቱ ወደ ጭልጋና አጎራባች ቀበሌዎች መዛመቱም ታውቋል። ግጭቱ በሽንፋና በኩመር አካባቢዎቸ ደም አፋሳሽ እንደነበር የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል።

Read More »

በኬንያ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን ቤት ለቤት ማደኑ ቀጥሏል

ኀዳር ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኬንያ ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን ሕጋዊ የመኖሪያ ፍቃድ የላቸውም በማለት የኬንያ ስደተኞች ቤት ለቤት አሰሳ በማድረግ ማሰር መጀመራቸውንና እስካሁን ድረስ ቁጥራቸው 54 የሚሆኑ ስደተኞች መታሰራቸውን የአገሪቱ ፓሊስ አስታውቋል። ኬንያን ለመሸጋገሪያነት በመጠቀም በታንዛኒያ አድርገው ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመሄድ የሚሞክሩ ሕገወጥ ስደተኞች ናቸው በማለት የጸጥታ ኃይሎች መግለጫ ቢሰጡም ከሌሎች ዜጎች በተለየ ኢትዮጵያዊያን ላይ ...

Read More »

አምነስቲ ኢንተርናሽናል መላው ዓለም በእስር ቤት ያሉትን ኢትዮጵያዊያን ጋዜጠኞችን እንዳይዘነጋ ጥሪውን አቀረበ

ኀዳር ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የዓለምአቀፍ የሰብዓዊ መብት ቀንን ምክንያት በማድረግ ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል በሽብር ሕግ ተከሶ ከአራት ዓመታት በላይ በእስር የሚማቅቀውን ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ጨምሮ ካለ ወንጀላቸው ከስራ ገበታቸው ታፍነው በወሕኒ የሚማቅቁትን ኢትዮጵያዊና ጋዜጠኞችንና የሰብዓዊ መብት ተሟጓቾችን መላው ዓለም ለአፍታም ሊዘነጋቸው እንደማይገባ መግለጫ አውጥቷል። ዓለምአቀፉ ማህበረሰብ ለሶስቱ የአልጀዚራ ጋዜጠኞች ፒተር ግሬትስ፣ ...

Read More »

በኦሮምያ የተነሳውን ህዝባዊ ተቃውሞ ለማብረድ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ተሰማሩ

ኀዳር ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት፣ የኦሮምያ ክልል ልዩ ሃይል እና የፌደራሉ አድማ ብተና ተቃውሞውን ለመቆጣጠር ባለመቻላቸውና የተቃውሞው አድማስ እየሰፋ በመሄዱ የመከላከያ ሰራዊት አባላት የፌደራል ዩኒፎርም ለብሰው ተቀላልቅለዋል። ለሳምንት የዘለቀው ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሎ ከአዲስ አበባ ወደ ሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል እንዲሁም ከጉደር ወደ ወለጋ የሚወስዱት መንገዶች በመዘጋታቸው የትራንስፖርት አግልግሎት ለሰአታት ተቋርጧል። መልከ ጡሪ አካባቢ ...

Read More »

የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ሰመጉ) መንግስት ለሰብዓዊ መብቶች መከበር ከቃል ያለፈ በተግባር እንዲያሳይ ጠየቀ

ኀዳር ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ቀንን ምክንያት በማድረግ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅቱ የኢትዮጵያ መንግስት ለሰብዓዊ መብቶች መከበር ከቃል ያለፈ በተግባር የተደገፈ አሰራርን እንዲከተል አሳስቧል። ሰመጉ ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ድንጋጌዎችን ከተቀበለች ከ68 ዓመታት በላይ እንደሆናትና መብቱ በሕገ መንግስቱ ውስጥ ቢካተትም ዜጎች ግን የሕግ ከለላው ተጠቃሚ መሆን አልቻሉም ብሎአል። እስካሁን ድረስ ...

Read More »