.የኢሳት አማርኛ ዜና

ኢትዮጵያውያን 120ኛውን የአድዋ ድል አከበሩ

የካቲት ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢትዮጵያ ፋሺስት ጣሊያንን ድባቅ የመታችበት የአድዋ ድል 120ኛ አመት በኢትዮጵያ እና ከኢትዮጵያ ውጭ በሚኖሩ ዜጎች ተከብሯል። የአድዋን ድል በማስመልከት አርበኞች ግንቦት7 ባወጣው መግለጫ ፣ ሀገራችን ኢትዮጵያን ለመውረርና ህዝቧን በውርድትና በባርነት ለመግዛት የዘመተብንን የጣሊያንን ጦር አለምን ማስደነቅ ብቻ ሳይሆን የታሪክን አቅጣጫ ቀይሯል ብሎአል።አድዋ ሲነሳ ልንረሳው የማንችለው ነገር “በግር በፈረስ ከሀገራችን ልዩ ...

Read More »

የገዢው መንግስት አመራሮች ህብረተሰቡ የጦር መሳሪያ ግዥውን እንዲያቆም እየተማጸኑ ነው፡፡

የካቲት ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአማራ ክልል አመራሮች በክልሉ ጠረፋማ ከተሞች በመዘዋወር ህብረተሰቡ አጠናክሮ የያዘውን የመሳሪያ ግዥ እንዲያቆም ሲማጸኑ ተሰምተዋል፡፡ ወጣቱ አመቱን ሙሉ በተለያዩ ቦታዎች በመዘዋወር የቀን ስራ በመስራትና ከእርሻ የሚያገኙትን ገቢ በቀጥታ ለጦር መሳሪያ ግዥ ማዋላቸው የገዢውን መንግስት አመራሮችን አሳስቧቸዋል፡፡ በአሁኑ ሰዓት በመፋፋም ላይ ባለው ወቅታዊ ችግር ምክንያት በዜጎችና በመንግስት መካከል በሚታየው ፊት መዟዟር ...

Read More »

በኦህዴድ ውስጥ ሹም ሽሩ ቀጥሏል

የካቲት ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢህአዴግ አንዱ ክንፍ የሆነው የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) ስራ አስፈጻሚ አባል የሆኑት የኦሮሚያ ከልል አስተዳደርና ፀጥታ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ከሀላፊነታቸው ተነሱ። ምንጮቹን በመጥቀስ ሪፖርተር እንደዘገበው የክልሉ አስተዳደርና ፀጥታ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰለሞን ኩቹ ከሀላፊነታቸው የተነሱት ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ኦህዴድ በኦሮሚያ ክልል እየተነሳና ዳግም እያገረሻ የሚገኘውን የፀጥታ ሁኔታ አስመልክቶ ...

Read More »

የሰማያዊ ፓርቲ አደራጅ 7 አመት እስር ተፈረደበት

የካቲት ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአርባ ምንጭ የሰማያዊ ፓርቲ አደራጅ የሆነው አቶ በፍቃዱ አበበ የ7 አመት እስር ቅጣት ተበየነበት፡፡ የካቲት 22/2008 ዓ.ም ከፍተኛው ፍ/ቤት 14ኛ ወንጀል ችሎት ቅጣቱን ያስተላለፈ አቶ በፍቃዱ ለግንቦት ሰባት ‹‹ሲያደራጅና ሲመለምል›› ነበር በሚል ነው። አቶ በፍቃዱ ‹‹አሁንም ሆነ፣ ወደፊት አሸባሪ አይደለሁም፡፡ ግፍ ተፈጽሞብኛል›› ሲል ችሎት ፊት ተናግሯል፡፡ የዕለቱ ዳኛ በበኩላቸው ‹‹ግፍ ...

Read More »

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰላም አስከባሪነት ከተሰማሩ አገራት ድሃ አገራት ከፍተኛውን ቁጥር መያዛቸውን ጥናቶች አረረጋገጡ።

የካቲት ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በመላው ዓለማት ግጭት ባለባቸው አገራት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ስር ሆነው በሰላም አስከባሪን ከተሰማሩ አገራት ውስጥ ከፍተኛውን የሰራዊት ድርሻ ካሰማሩ አገራት ተርታ ኢትዮጵያ በቀዳሚነት ተሰልፋለች። ጥናቱ እንደ አውሮፓዊያን ዘመን አቆጣጠር በ2016 ዓ.ም በሰላም አስከባሪ ጦር የተሰማሩ አገራትን ዝርዝር ጥናታዊ አሃዝ አውጥቷል። ኢትዮጵያ 8 ሽህ 326 ሰራዊት በማሰለፍ በቀዳሚነት ደረጃ ላይ ስትመደብ ...

Read More »

በአሜሪካ ሜሪላንድ ሞንትጎመሪ ካውንቲ የመጋቢት ወር የአድዋ ድል ወር ተብሎ እንዲከበር ወሰነ

ኢሳት (የካቲት 22 ፥ 2008) ኢትዮጵያውያን በህብረት ወራሪውን የጣሊያንን ጦር የደመሰሱበት የአድዋ ድል በዓል ወርሃ መጋቢት (ማርች) ተሰይሞለት የአድዋ ድል ወር ተብሎ ታሪኩ እየተወሳ እንዲከበር የአሜሪካ ሜሪላንድ ግዛት ምንትጎመሪ ካውንቲ በአዋጅ ወሰነ። መታሰቢያው የካቲት 23 ወይም ማርች 1,  120ኛው የአድዋ ድል እንዲከበር በመጥቀስ አጼ ምኒሊክና እቴጌ ጣይቱ የመሩት ጦር በወራሪው ጣሊያን ላይ የተቀዳጀው ድል ኢትዮጵያን ከቅኝ ግዛት ነጻ ያወጣት ሃገር ...

Read More »

በእስራዔል የወንጀል ምርመራ እንዲቋረጥ መደረግን ተከትሎ ተቃውሞ ተደረገ

ኢሳት (የካቲት 22 ፥ 2008) በእስራዔል ከአንድ ኢትዮጵያዊ ሞት ጋር በተያያዘ ሲካሄድ የነበረ የወንጀል ምርመራ ኣንዲቋረጥ መደረግን ተከትሎ በእየሩሳሌም የሚኖሩ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ አባላት ማክሰኞ ምሽት ተቃውሞ አደረጉ። በከተማዋ በሚገኘው የፖሊስ ዋና ጽ/ቤት ከተጀመረው ተቃውሞ በተገናኘ ስምንት ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የእስራዔል መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። የሃገሪቱ ፖሊስ በፀጥታ ሃይሎች በደል ተፈጽሞበት ራሱን ባጠፋው ዮሴፍ ሳላምሳ ላይ ሲያካሄድ የነበረውን የወንጀል ምርመራ ምክንያቱ ...

Read More »

አፍሪካ ቫኬሽን የመዝናና ሆቴል ከባድ የእሳት ቃጠሎ አደጋ ደረሰበት

ኢሳት (የካቲት 22 ፥ 2008) በደቡብ ክልል ሃዋሳ ከተማ ላንጋኖ ሃይቅ ዳርቻ የተገነባውና የባለ አምስት ኮከብ ደረጃ ያለው አፍሪካ ቫኬሽን የመዝናኛ ሆቴል ሰኞ ምሽት ከባድ የእሳት ቃጠሎ አደጋ ደረሰበት። ምክንያቱ ባልታወቀው በዚሁ የእሳት ቃጠሉ የሆቴሉ የማረፊያና ሌሎች ክፍሎች ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸው እማኞች ዋቢ በማድረግ በሃገር ውስጥ ያሉ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። በዚሁ የመዝናኛ ሆቴል ላይ በአጠቃላይ የደረሰው ጉዳት ለማወቅ የተደረገ ጥረት ...

Read More »

በኦሮሚያ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ በተለያዩ ከተሞች መካሄዱን አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ዘገቡ

ኢሳት (የካቲት 22 ፥ 2008) በኦሮሚያ ክልል የተቀሰቀሰውና ሶስተኛ ወሩን ያስቆጠረው የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ተቃውሞ በተያዘው ሳምንት በተለያዩ የክልሉ ከተሞች መቀጠሉን አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ማክሰኞ ዘገቡ። የመንግስት ባለስልጣናት ተቃውሞን ለመቆጣጠር እርምጃን እንደሚወስዱ በተደጋጋሚ ቢያሳስቡም ይኸው ተቃውሞ በምስራቅና በምዕራብ ሃረርጌ አካባቢዎች እልባት አለመገኘቱ ታውቋል። የአዲስ አበባ ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኙ ከተሞች ሳይቀር በወታደራዊ ተሽከርካሪዎች እየጠበቁ እንደሚገኝ አፍሪካ ታይምስ ...

Read More »

ለሁለት ቀናት የተጠራው የአዲስ አበባ ታክሲ አሽከርካሪዎች አድማ ወደ ኦሮምያ ተዛመተ

የካቲት ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስ አበባ ለሁለት ቀናት የተጠራው የታክሲ አሽከርካሪዎች አድማ ለሁለተኛ ቀን ከቀጠለ በሁዋላ፣ ከሰዓት በሁዋላ በተለይም ከቀኑ 10 ሰአት ጀምሮ ታክሲዎች ቀስ በቀስ ስራ ጀምረዋል።በአዲስአበባ የተደረገውን አድማ ተከትሎ፣በኦሮምያ የተለያዩ ከተሞችም ተመሳሳይ የስራ ማቆም አድማ ተደርጓል።በሆለታ፣ ቡራዩ፣ግንጪ፣ አምቦ፣ ወሊሶና አካባቢዋ የትራንስፖርት አገልግሎት ተቋርጦ ውሎአል። በአዲስ አበባ ጠዋት አካባቢ ጥቂት ታክሲዎች ስራ ለመጀመር ...

Read More »