ኢሳት (መጋቢት 8 ፥ 2008) ከህዳር ወር 2008 ዓም ጀምሮ እስካሁን በቀጠለው የኢትዮጵያ ኦሮሚያ ክልል የተቃውሞ እንቅስቃሴ ከ342 ወረዳዎች በ33ቱ ላይ ብቻ በተደረገ ምርመራ የ103 ሟቾች ዝርዝር ይፋ ሆኗል። እናትና ልጅን ጨምሮ ከ8 ዓመት ህጻን እስከ 78 ዓመት አዛውንት በመንግስት ሃይሎች ግድያ እንደተፈጸመባቸው የሰብዓዊ መብት ጉባዔ በሳምንቱ መጀመሪያ ይፋ አድርጓል። መከላከያ ሰራዊት በተለይም የአጋዚ ክፍለ ጦርና ፌዴራል ፖሊስ በግድያው አብይ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ህወሃት ለቀድሞ ታጋዮቹ ጥሪ አደረገ
ኢሳት (መጋቢት 8 ፥ 2008) ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ለነባር ታጋዮቹ ጥሪ ማድረጉ ተገለጸ። ታጋዮቹ ካለፈው መጋቢት 10 ጀምሮ በተጀመረው የህወሃት ማዕከላዊ ኮሜቴ አባላት ስብሰባ ላይ እንዲገኙ መጠራታቸውም ታውቋል። የቀድሞ የህወሃት መስራችና አመራር አባል የነበሩት አቶ አሰግደ ገብረስላሰ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እንደገለጹት፣ በጭንቀት ውስጥ የሚገኙት የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ መሪዎች በውስጣቸው ቀውስና መከፋፈል ሲፈጠር ሜዳ ላይ የጣሏቸውን ነባር ታጋዮችን ...
Read More »ወደኬንያ የሚጎርፉ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በማስመልከት ኬንያና ኢትዮጵያ ውይይት እያደረጉ ነው
ኢሳት (መጋቢት 8 ፥ 2008) ከኢትዮጵያ ወደጎረቤት ኬንያ የሚሰደዱ ኢትዮጵያውያን ቁጥር መጨመረን ተከትሎ የሁለቱ ሃገራት በችግሩ ዙሪያ ምክክርን በማካሄድ ላይ መሆናቸውን የኬንያ መገኛኛ ብዙሃን ዘገቡ። በኬንያ የድንበር አካባቢ በምትገኘው ማንዴራ ግዛት የሚገኙ የኢሚግሬሽን ሃላፊዎች ከዶሎ ከተወከሉ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር በኬንያ ምክክር እያደረጉ መሆኑን ዘስታር የተሰኘ ጋዜጣ ባቀረበው ሪፖርት አመልክቷል። ባለፈው ወር ብቻ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ወደ ኬንያ የተሰደዱ ሲሆን፣ የሃገሪቱ ...
Read More »ዴቪድ ካሜሩን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን በማስመልከት ለኢትዮጵያ መንግስት ሁለት ጊዘ ደብዳቤ መጻፋቸው ተነገረ
ኢሳት (መጋቢት 8 ፥ 2008) በቅርቡ በኢትዮጵያ ጉብኝትን ያደርጋሉ ተብለው የሚጠበቁት የብሪታኒያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሩን በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጉዳይ ያላቸውን ስጋት በመግለጽ ለኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ሁለት ጊዜ ደብዳቤ መጻፋቸውን የሃገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ሃሙስ ዘገቡ። የሃገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሲያደርግ የቆየው ጥረት ውጤት አለማምጣቱን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ደብዳቤውን እንደጻፉ በዝ ፊድ ኒውስ የተሰኘ ጋዜጣ አስነብቧል። የብሪታኒያ ውጭ ...
Read More »አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ የአለም አቀፍ ማህበረሰብ አፋጣኝ የእርዳታ ድጋፍን እንዲያደርግ ጠየቁ
ኢሳት (መጋቢት 8 ፥ 2008) በኢትዮጵያ እየተባባሰ የመጣውን የድርቅ አደጋ ተከትሎ የሃገሪቱ ባለስልጣናት የአለም አቀፍ ማህበረሰብ አፋጣኝ ድጋፍን እንዲያደርግ ጥያቄ ማቅረባቸውን አሶሼየትድ ፕሬስ ሃሙስ ዘገበ። በድርቁ አደጋ ዙሪያ ከዜና አውታሩ ጋር ቃለ-ምልልስን ያደረጉ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ በአለም ዙሪያ ሌሎች ቀውሶች ቢኖሩም ሃገራቸው በምንም መልኩ ችላ መባል እንደሌለበት ገልጸዋል። በሃገሪቱ ያሉ ከ10 ሚሊዮን በላይ ተረጂዎች በቂ እርዳታን እያገኙ እንዳልሆነ ...
Read More »በደቡብ ኦሞ ዞን መሬትና የባንክ ብድር ከወሰዱት ባለሃብቶች መካከል ከ98 በመቶ በላይ የሚሆኑት የህወሃት አባላት ናቸው ተባለ
በደቡብ ኦሞ ዞን መሬትና የባንክ ብድር ከወሰዱት ባለሃብቶች መካከል ከ98 በመቶ በላይ የሚሆኑት የህወሃት አባላት ናቸው ተባለ መጋቢት ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአካባቢው ተወላጅ ባለሙያዎች ከዞኑ ግብርና፣ የህብረት ስራና የኢንቨስትመንት ቢሮ ባለሙያዎች ያገኙትን መረጃ አጠናክረው ለኢሳት በላኩት ዝርዝር ሪፖርት እንዳመለከቱት ከ2006 ዓም ጀምሮ በደቡብ ክልል፣ በደቡብ ኦሞ ዞን 20 ኢንቨስተሮች ያሉ ሲሆን፣ ከእነዚህ መካከል 16 ቱ ...
Read More »በሃረር አዲስ የመከላከያ ሰራዊት አባላትን ለመመልመል የተደረገው ጥረት አልተሳካም
መጋቢት ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአካባቢው ወከል እንዳለው፣ ሰሞኑን አዲስ ምልምል ወታደር ለመቅጠር ተደጋጋሚ ማስታወቂያ ቢወጣም፣አልተሳካም። የመንግስት ካድሬዎች በመኪኖች ላይ እየዞሩ ” ለወታደሮች ቤት እንደሚሰጡ” እየገለጹ፣ እንዲመዘገቡ ቢቀሰቅሱም፣ እስካሁን የሚመዘገብ ወጣት መጥፋቱን ምንጮቹን ዋቢ አድርጎ ጠቅሷል። ትናንት በተለያዩ ምክንያቶች የተገለሉ የቀድሞ ወታደሮችና የፖሊስ አባላትን ለስብሰባ ተጠርተው የነበረ ቢሆንም፣ በቂ ተሰብሳቢ ሊገኝ ባለመቻሉ ተሰርዟል። በሌሎችም ወረዳዎች ተመሳሳይ ...
Read More »አቶ ካሳ ተክለብርሃን “መንግስት ችግር አለብኝ፣አርሙኝ ማለቱ ውድቀቱን አያሳይም” አሉ
መጋቢት ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፌደራል ጉዳዮችና አርብቶአደሮች አካባቢ ልማት ሚኒስትር አቶ ካሳ ተክለብርሃን መንግስት ችግር አለብኝ፣አርሙኝ ማለቱ እንደውድቀት እንደማይታይ ተናግረዋል። ሚኒስትሩ ከመንግስታዊው አዲስዘመን ጋዜጣ የመጋቢት 8/2008 ዓም እትም ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ መንግስት ይሄ ችግር አለብኝ ብሎ አርሙኝ፣ አስተካክሉኝ፣ማለቱ ታላቅነት ነው፣ውድቀት አይደለም ብለዋል። አንዳንዶች መንግስት ጉድለት አለብኝ ስላለ መምራት አይችልም፣ወድቆአል በማለት የህብረተሰቡን ስሜቶች ወደሌላ ለመውሰድ የሚፈልጉ ...
Read More »የአዲስአበባ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ቆጠራ ውጤት የአዲስአበባን ህዝብ እያነጋገረ ነው
መጋቢት ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አስተዳደሩ ባለፉት 11 አመታት ከ143ሺህ በላይ ኮንዶሚኒየም ቤቶችን በመገንባት በእጣ ማከፋፈሉን ሲገልጽ የቆየ ቢሆንም፣ ቤቶቹ በትክክል ስለመተላለፋቸው በቂ መረጃ አልነበረውም።ይህን ተከትሎ ቆጠራ እንዲካሄድ በተወሰነው መሰረት በ15 ቀናት ቆጠራ ብቻ ከ1 ሺ 200 በላይ ቤቶች ለተጠቃሚዎች ሳይተላለፉ ለአመታት ተዘግተው የተገኙ ሲሆን ፣98 ቤቶች ደግሞ በማይታወቁ ሰዎች ተይዘው ሲጠቀሙባቸው ተገኝተዋል። ከ800ሺህ በላይ እጣ ...
Read More »በዲላ ውሃ ቀጅዎች የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ
መጋቢት ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዲላ በውሃ ችግር ከተመታች ወራት ቢቆጠሩም፣ ችግሩ ግን እስካሁን አልተቀረፈም። በአካባቢው ጋሪ ያላቸው ሰዎች ውሃ ከወንዝ በመቅዳት ለከተማው ህዝብ እየሸጡ፣ የውሃ ችግሩን ለመቅረፍ ጥረት ቢያደርጉም፣ የከተማው መስተዳደር ግን፣ የውሃ ችግሩን ሳይቀርፍ፣ ውሃ ሻጮች ውሃ ከወንዝ አትቀዱም በማለት ክልከላ አስቀምጧል። በዚህ የተበሳጩት ከ70 በላይ የሚሆኑ ውሃ ነጋዴዎች፣ ጋሪዎቻቸውን አሰልፈው ሰላማዊ ሰልፍ አድርገዋል። ...
Read More »