.የኢሳት አማርኛ ዜና

የአሜሪካ ሴናተሮች በኢህአዴግ እየተወሰደ ያለውን የሰብዓዊ መብት ረገጣ በጽኑ አወገዙ

ኢሳት (ሚያዚያ 13 ፥ 2008) 11 የአሜርካ ሴናተሮች የኢህአዴግ መንግስት የአገሪቷን ህገ-መንግስቱን በመጠቀም ሃሳባቸውን በገለጹት ሰላማዊ ሰልፈኞች፣ ጋዜጠኞች፣ እና የሲቪክ ማህበረሰብ አባላት ላይ እያደረሰ ያለውን የጉልበትና የጠብ-አጫሪነት እርምጃ በጽኑ አወገዙ። የሜሪላንድ ግዛት ሴናተር ቤን ካርዲን፣ እንዲሁም ሲናተር ሩቢዮ  ሌሎች 9 ሴናተሮች  ለአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ጽ/ቤት በጻፉት ደብዳቤ፣ ህወሃት/ኢህአዴግ ፈጽሟል የተባለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰትና ግድያ የአሜርካ መንግስት እንዲያጣራ ጠይቀዋል። የኢትዮጵያ ...

Read More »

በጋምቤላ ታፍነው የተወሰዱትን ህጻናት ለማስመለስ የተወሰደ ወታደራዊ እርምጃ የለም ተባለ

ኢሳት (ሚያዚያ 13 ፥ 2008) ባለፈው ሳምንት በጋምቤላ ክልል ተፈጽሞ በነበረው ጥቃት ታፍነው የተወሰዱ ከ100 በላይ ህጻናት ያሉበት ስፍራ ታውቋል ቢባልም በአካባቢው የተወሰደ ወታደራዊ እርምጃ አለመኖሩን የሱዳን መገናኛ ብዙሃን ሃሙስ ዘገቡ። ጥቃቱን ከደቡብ ሱዳን መነግስት ጋር በጋራ ለማካሄድ ምክክር በማካሄድ ላይ ሲሆን በዚሁ ጥቃት ልጆቻቸው ታፍነው የተወሰዱባቸው ወላጆች በበኩላቸው ልጆቻቸውን በህይወት እናገኛለን የሚል ተስፋ እንደሌላቸው ለቢቢሲ ገልጸዋል። ህጻናቱ በህይወት ለመታደግ ...

Read More »

ታንዛኒያ 74 ኢትዮጵያውያንን ወደኬንያ ድንበር አባረረች

ኢሳት (ሚያዚያ 13 ፥ 2008) በቅርቡ ወደሃገሯ በሚገቡ ስደተኛ ኢትዮጵያውያን ቁጥር መጨመር ስጋቷን ስትገልፅ የቆየችው ታንዛኒያ 74 ኢትዮጵያውያንን በኬንያ ድንበር አሰፈረች (ጣለች)። የታንዛኒያ መንግስት ማክሰኞ የወሰደው ይህንኑ እርምጃ ተከትሎም በሃገሪቱና በኬንያ መንስታት በኩል ዲፕሎማሲያዊ አለመግባባት መፍጠሩ ታውቋል። ”ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ወደሃገራቸው መመለስ ሲገባቸው በኬንያ ድንበር መጣላቸው ተገቢ አይደለም ስትል ኬንያ በታንዛኒያ መንግስት ላይ ተቃውሞዋን እንደገለጸች ኒውስ 24 የተሰኘ ጋዜጣ በዘገባው አስፍሯል። ...

Read More »

በጋምቤላ የተጨፈጨፉትን ወገኖች በተመለከተ የመከላከያ ሰራዊቱን ገመና የሚያጋልጡ መረጃዎች እየወጡ ነው

ሚያዚያ ፲፫(አሥራ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአካባቢው የሰፈረው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በተለያዩ ውስጣዊና ውጫዊ ምክንያቶች የሙርሌ ጎሳ አባላት በተደጋጋሚ የሚፈጽሙትን ጥቃት ለመከላከል አለመቻሉን የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚናገሩ ምሁራን ገልጸዋል። በደቡብ ሱዳን የሚገኙ የሙርሌ ጎሳ አባላት በኑዌር ኢትዮጵያውያን ላይ ፣ ሚያዚያ 7፣ 2008 ዓም ባደረጉት ጥቃት ከ230 በላይ ሰዎች ሲገደሉ፣ ከ140 በላይ ህጻናትና ሴቶች ደግሞ በታጣቂዎቹ ተወስደዋል። መንግስት የተጠለፉት ዜጎች ...

Read More »

ኦፌኮ በኦሮምያ የሚደረገውን ተቃውሞ ለማዘናጋት መንግስት የሚወስደውን የማዘናጊያ እርምጃ ነቀፈ

ሚያዚያ ፲፫(አሥራ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ባወጣው መግለጫ ፣ በኦሮሚያ ክልላዊ መስተዳድር ዉስጥ ያለዉን ሕዝባዊ መነሳሳት ለማዘናጋትና ለማዳፈን ሲል መንግስት በሚቆጣጠራቸዉ የዜና ማሰራጫዎች ተጎጂ የሆነዉን ሕዝባችንን በይበልጥ ለመጉዳት ታስቦ በሚመስል መልኩ ሰፊ የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ ተከፍቷል ብሎአል። መንግስት መልካም አስተዳደርን ያጓደሉ ናቸዉ በማለት በመጀመሪያ 300 ባለሥልጣኖችን አሁን በቅርቡ ደግሞ 863 ባለሥልጣኖችንና ኃላፊዎችን ከሥልጣን አባርሬአለሁ በማለት መንግስት ...

Read More »

የእስር ጊዜያቸውን ያጠናቀቁ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ታንዛኒያና ኬንያ ድንበር ላይ መጣላቸው ተዘገበ

ሚያዚያ ፲፫(አሥራ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሕገወጥ መንገድ የታንዛኒያን ድንበር አቋርጣችሁ ገብታችኋል ተብለው በታንዛኒያ ፍርድ ቤት የተበየነባቸውን የእስር ጊዜያት ያጠናቀቁ 74 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በታንዛኒያና ኬንያ ድንበር ታቬታ በምትባል የድንበር አዋሳኝ ስፍራ ላይ ተጥለዋል። የታንዛኒያ መንግስት በገባችሁበት በኬንያ ተመለሱ በማለት ሰብዓዊ መብታቸውን በመጣስ ከሕግ ውጪ ስደተኞቹን ከግዛቱ ሲያባርር፣ የኬንያ መንግስት በበኩሉ ስደተኞቹ የእስር ጊዜያቸውን እንደጨረሱ ወደ ትውልድ አገራቸው መላክ ...

Read More »

የተባበሩት መንግስታት የህጻናት መርጃ ድርጅት በጋምቤላ ታፍነው የተወሰዱት ህጻናት ጉዳይ አሳስቦኛል አለ

ኢሳት (ሚያዚያ 12 ፥ 2008) ከአምስት ቀን በፊት ከጋምቤላ ክልል ታፍነው የተወሰዱት ወደ 100 አካባቢ የሚጠጉት ህጻናት ደህንነት አሳስቦት እንደሚገኝ የተባበሩት መንግስታት የህጻናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) አስታወቀ። በክልሉ የተፈጸመውን ግድያ ያወገዘው የህጻናት መርጃ ድርጅቱ ከቀያቸው ታፍነው የተወሰዱ ህጻናት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ እንዲፈቱም ጥሪውን አቅርቧል። የኢትዮጵያ መንግስት ታፍነው የተወሰዱ ህጻናትን ለመታደግ ዘመቻ መክፈቱን ቢገልጽም ድርጊቱን ፈጽመዋል የተባሉ ታጣቂዎች የሚገኙበትን ስፍራ ...

Read More »

በጋምቤላ የሰዎች መገደልና መታፈን አዲስ አይደለም ሲሉ የክልሉ ፕሬዚደንት አስታወቁ

ኢሳት (ሚያዚያ 12 ፥ 2008) በድንበር ዘለል የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች ጥቃት ኢትዮጵያ ግዛት ገብተው ሰዎች ሲገድሉም ሆነ ታፍነው ሲወስዱ ይህ የመጀመሪያቸው አለመሆኑን የጋምቤላ ክልል ፕሬዚደንት ገለጹ። ከሰሞኑ ጥቃት በፊት ባሉት 20 ቀናት ብቻ ታጣቂዎቹ 21 ኢትዮጵያውያን ገድለው፣ 17 ህጻናትን አፍነው መውሰዳቸውን ለመንግታዊና ለፓርቲ ሚዲያዎች በሰጡት ቃለምልልስ አመልክተዋል። የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጋትሉዋክ እንደተናገሩት አርብ ሚያዚያ 8 ፥ 2008 ከተገደሉት ...

Read More »

ስደተኛ ኢትዮጵያውያን በቃሊቲና በሌሎች የኢትዮጵያ ወህኒ ቤቶች የደረሰባቸውን ሰቆቃ ገለጹ

ኢሳት (ሚያዚያ 12 ፥ 2008) የህወሃት ኢህአዴግን መንግስት በመሸሽ በኬንያ ተሰደው የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በቃሊቲና በሌሎች የኢትዮጵያ ወህኒ ቤቶች የደረሰባቸውን ሰቆቃ ኦኬ አፍሪካ ለተባለ ጋዜጣ በዝርዝር ገለጹ። በኢትዮጵያ ወህኔ ቤቶች ምን አይነት ሰቆቃ በእስረኞቹ ላይ ሲደርስ እንደበር በዝርዝር ያሰፈረው ጋዜጣው፣  በኬንያ ያሉት ስደተኞች በኢትዮጵያ ውስጥ ታስረው በነበሩበት ጊዜ፣ በማዕከላዊና በሌሎች ተመሳሳይ እስር ቤቶች የሚገኙ መርማሪዎች፣ እስረኞቹን በኤለክትሪክ ወንበር እንደሚያቃጥሉ፣ እስኪቆስሉ ከገረፉ ...

Read More »

የኢትዮጵያ መንግስት የስኳር ፋብሪካዎች ግንባታ ሊያጠናቀቅ ባለመቻሉ ለውጭ ገበያ ለማቅረብ ያሰበው እንዳልተሳካ ተገለጸ

ኢሳት (ሚያዚያ 12 ፥ 2008) በተያዘው አመት ስኳርን ለውጭ ገበያ ለማቅረብ እቅድ ይዞ የነበረው መንግስት የስኳር ፋብሪካዎች ግንባታ ሊጠናቀቅ ባለመቻሉ እቅዱ ለሁለተኛ ጊዜ መስተጓጎሉን የስኳር ኮርፖሬሽን ገለጠ። መንግስት በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብን በመመደብ አራት የስኳር ፋብሪካዎችን  ስራ ለማስጀመር ጥረት ቢያደርግም ፋብሪካዎቹ መጠናቀቅ እንዳልቻሉ ታውቋል። በሃገሪቱ በመባባስ ላይ ያለው የድርቅ አደጋ በነባር የስኳር ፋብሪካዎች ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደሩንና ስኳርን ከውጭ ሃገር ለማስገባት ...

Read More »