.የኢሳት አማርኛ ዜና

ሰባት የስኳር ፋብሪካዎችን ለመገንባት ተነድፎ የነበረው እቅድ ባለመሳካቱ ከፍተኛ ኪሳራ አስከተለ

ኢሳት (ግንቦት 3 ፥ 2008) መንግስት ከ70 ቢሊዮን ብር በላይ ብድርን በማሰባሰብ ሰባት የስኳር ፋብሪካዎችን ለመገንባት የነደፈው እቅድ ለስደስት አመት ያህል ጊዜ ወደ ተግባር ባለመለወጡ ከፍተኛ ኪሳራ ማስከተሉ ተገለጠ። የስኳር ፋብሪካዎቹን ግንባታ እንዲቆጣጠር ሃላፊነት የተሰጠው የስኳር ኮሮፖሬሽን በበኩሉ ለእቅዱ አለመሳካት ብረታብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽንን ተጠያቂ ማድረጉ ታዉቋል። ሰባቱ የስኳር ፋብሪካዎችን ለመገንባት መንግስት ከአባዳሪ አባላት ወደ ሁለት ቢሊዮን ዶላር አካባቢ የወሰደ ሲሆን ...

Read More »

አትላስ አፍሪካ ኢንዱስትሪስ ሊሚትድ የተባለ ኩባንያ 2.4 ሚሊዮን ብር ያለአግባብ በኢትዮጵያ መንግስት ተወስዶብኛል አለ

ኢሳት (ግንቦት 3 ፥ 2008) መቀመጫውን በብሪታኒያ ያደረገና በቅርቡ በኢንቨስትመንት ስራ ላይ ለመሰማራት ወደ ኢትዮጵያ የገባ አንድ አለም አቀፍ ኩባንያ በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ካለው የባንክ ሂሳብ (አካውንት) ውስጥ 2.4 ሚሊዮን ዶላር በመንግስት ተወስዶብኛል ሲል ሃሙስ ቅሬታን አቀረበ። አትላስ አፍሪካን ኢንዱስትሪስ ሊሚትድ የተሰኘው ይኸው ኩባንያ በመንግስት ተወስዶብኛል ያለውን ገንዘብ ለማስመለስ ህጋዊ፣ ዲፕሎማሲያዊ፣ እንዲሁም ፖለቲካዊ አማራጮችን እየተመለከተ እንደሆነም ይፋ አድርጓል። ይኸው በቅርቡ ...

Read More »

76 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በማላዊ ተያዙ

ኢሳት (ግንቦት 3 ፥ 2008) ከሁለት ቀን በፊት ከ30 በላይ ስደተኛ ኢትዮጵያውያንን በቁጥጥር ስር ያዋለው የማላዊ መንግስት ተጨማሪ 76 ኢትዮጵያውያንን ረቡዕ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገለጠ። ከእነዚሁ ስደተኞች መካከል 33ቱ በእቃ መጫኛ (ኮንቴይነር) ተሽከርካሪ ውስጥ ተደብቀው ከማላዊ ለመውጣት በጉዞ ላይ ኣያሉ ሊያዙ መቻላቸውን የማላዊ ፖሊስ አስታውቋል። በስደተኛ ኢትዮጵያውያን ቁጥር መበራከት ስታጋቸውን በመግለጽ ላይ ያሉት የሃገሪቱ የኢሚግሬሽን ባለስልጣናት በዕቃ መጫኛ ተሽከርካሪው ውስጥ ...

Read More »

በኢትዮጵያ የተሰከሰተው ድርቅ በህጻናት ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ እያደረሰ ነው ተባለ

ኢሳት (ግንቦት 3 ፥ 2008) በኢትዮጵያ በተከሰተው ከፍተኛ የዝናብ እጥረት የህጻናትን ህይወት ለአደጋ እያጋለጠ መገኘቱን   ዩኒሴፍ አስታወቀ።የተባበሩት መንግስታት የህጻናት መርጃ ድርጀት UNICEF ይህንን ያስታወቀው በሳምንቱ መጀመሪያ በድረ ገጹ ላይ ባቀረበው ዘገባ ሲሆን፣ህጻናቱም ሆነ ቤተሰቦቻቸው ችግሩን ለመቋቋም ቀዬያቸውን ጥለው ለመሰደድ መገደዳቸውንም አስፍሯል። ባለፈው ዓመት ዝናብ በወቅቱ ባለመዝነቡ ምክንያት የውሃ እጥረት እና የአዝመራ መውደም እንዳስከተለ፣ ይህም የህጻናት ምግብ አቅርቦት በእርዳታ ላይ የተመሰረተ ...

Read More »

 በባሌ ዞን  የጎርፍ  አደጋ በሰውና ንብረት ላይ ጉዳት አደረሰ

ኢሳት (ግንቦት 3 ፥ 2008) ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል በባሌ ዞን ለተከታታይ ቀናት የዘነበውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ በተከሰተው ጎርፍ፣ ቁጥሩ  ያልታወቀ የሰው ህይወት ማለፉና ከአንድ ሺ በላይ የሚሆኑ የቀንድ ከብቶች በጎርፉ መወሰዳቸው ተገለጸ ።  በኦሮሚያ ክልል በባሌ ዞን የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ቢሮ ሃላፊ የሆኑት አቶ ኣብርሃም ሃይሌ APA ለተሰኘው የዜና አውታር  ማክሰኞ እንደገለጹት፣ ጎርፉ ቁጥራቸው እስካሁን ያልታወቀ የሰዎችን ህይወት አጥፍቷል፣ በ559 ...

Read More »

በአርባምንጭ የነጭ ሳር ፓርክ አካባቢ በተደረገው ጦርነት ከ20 ያላነሱ የመንግስት ታጣቂዎች ተገደሉ

ግንቦት ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአካባቢው ታማኝ ምንጮች እንደገለጹት ታጣቂዎቹ ባደረሱት ድንገተኛ ጥቃት 20 የመንግስት ወታደሮች ሲገደሉ፣ በርካቶች ደግሞ ቆስለዋል። ከተገደሉት መካከል የአካባቢው ወታደራዊ አዛዥም ይገኝበታል። የተኩስ ልውውጡ ለረጅም ሰአታት የቀዬ መሆኑን የሚናገሩት ምንጮች፣ በከፍተኛ ሁኔታ የተጎዱ የመንግስት ታጣቂዎች ወደ ህክምና ተወስደዋል። የመንግስት የጸረ ሽብር ግብረሃይል ዛሬ ባወጣው መግለጫ፣ ከኤርትራ የተንቀሳቀሱ ሃይሎች በሞያሌ በኩል ወደ አርባምንጭ ጫካ ...

Read More »

ከ12 ቢሊዮን ብር በላይ ያልተወራረደና የተበላሸ ሂሳብ ያለው ንግድ ባንክ ከ700 ሚሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ ወጪ ማውጣቱ ታወቀ

ግንቦት ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ለኢሳት የደረሰው የባንኩ የውስጥ ኦዲት ሪፖርት እንደሚያሳየው በበጀት አመት እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2013 እና 2014 ባንኩ ያላወራረደው 11 በሊዮን ብር እንዲሁም የተበላሸ ገንዘቡ 1 ቢሊዮን ብር ቢደርስም፣ የባንኩ ባለስልጣናት ከተመደበላቸው መደበኛ በጀት ውጭ 729 ሚሊዮን ብር አውጥተዋል። “ሙስናን በመዋጋት አገራችንን ከዘላለማዊ ከእዳ እንታደግ “ በሚል የባንኩ ሰራተኞች የውስጥ እንቅስቃሴ የጀመሩ ሲሆን፣ ከመንግስት ...

Read More »

በመከላከያ አዛዦች የሚመራው ሜቴክ አገሪቱን ለከፍተኛ እዳ እየዘፈቃት ነው ተባለ

ግንቦት ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በህወሃቱ ጄኔራል ክንፈ ዳኘው የሚመራውና በአንድ ወቅት አቶ መለስ ዜናዊ “የኢትዮጵያን የኢንዱስትሪ እድገት አቅጣጫ የሚቀይስ ተቋም” ብለው ያሞካሹት በመከላከያ ስር የሚገኘው የብረታብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ( ሜቴክ) በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገነቡ ፕሮጀክቶች መጓተት እንዲሁም በማህበራዊ አገልግሎት ዘርፍ ለሚታዩ ችግሮች ዋና ተጠያቂ መሆኑን የመንግስት ባለስልጣናት መናገር ጀምረዋል። ይሁን እንጅ የሜቴክ አመራሮችን ደፍሮ የሚጠይቃቸው በመጥፋቱ፣ አገሪቱ ...

Read More »

መንግስት ቤቶችን ስርቶ ለማስረከብ የገባውን ቃል ማክበር ሳይችል ቀረ

ግንቦት ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከ160 ሺ በላይ ህዝብ በየወሩ እየቆጠበ ከዛሬ ነገ ቤት አገኛለሁ በሚል እየተጠባበቀ የሚገኘውን 40 በ60 ተብሎ የሚታወቀው የቤቶች ፕሮጀክት ትክክለኛ የማስተላለፊያ ጊዜ መቼ እንደሆነ የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስትሩ አቶ መኩሪያ ሀይሌ አለመናገራቸው ቆጣቢዎችን አስቆጥቷል። በ2005 ዓም መጨረሻ በ40 በ60 የቤቶች ልማት መርሀግብር በመመዝገብ መንግስት በ18 ወራት ቤት ሰርቶ እንደሚያስረክብ የገባውን ቃል በማመን፣ ...

Read More »

በሺ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ወደ የመን እየጎረፉ ነው ተባለ

ኢሳት (ግንቦት 2 ፥ 2008) ባለፈው የፈረንጆች ወር ብቻ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ጦርነት እልባት ወደ አላገኘበት የመን በስደት መግባታቸውን አንድ አለም አቀፍ ተቋም ገለጠ ። በአፍሪካ ቀንድና የመን የስደተኞችን እንቅስቃሴ የሚከታተለው አህጉራዊ የስደተኞች ተቋም (ማይግሬሽን ሴክረታሪያት ) በመጋቢት ወር ብቻ አብዛኞቹ ኢትዮጵያዊያን የሆኑ 10 ሺ 400 ስደተኞች ወደ የመን በመግባት የፖለቲካ ጥገኝነት ማቅረባቸውን አመልክቷል። ከዚህ ከፍተኛ ቁጥር መካከልም ቁጥራቸው አነስተኛ ...

Read More »