ኢሳት (ግንቦት 5 ፥ 2008) ከ70 ቢሊዮን ብር በላይ ተመድቦላቸው በስድስት አመት ጊዜ ውስጥ ወደስራ መግባት ያልቻሉ የስኳር ፋብሪካዎች በየወሩ ከ160 ሚሊዮን ብር በላይ ለደሞዝ ክፍያ ወጪን እያደረጉ እንደሆነ ተገለጠ። በጉዳዩ ዙሪያ ሪፖርት ያቀረበው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በበኩሉ የስኳር ኮርፖሬሽን የፋብሪካዎች ግንባታ ሳይጠናቀቅ የሰራተኛ ቅጥርን እንዳይፈጽም አሳስቧል። መንግስት ከተለያዩ አካላት ብድርን በማሰባሰብ የስኳር ፋብሪካዎቹን ለማቋቋም ጥረትን ቢያደርግም፣ ፋብሪካዎቹ ከፍተኛ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የደቡብ ሱዳን ነዋሪዎች ከኢትዮጵያ መንግስት ወታደሮች ጋር አለመግባባት ላይ ናቸው ተባለ
ኢሳት (ግንቦት 5 ፥ 2008) በቅርቡ ከጋምቤላ ክልል ታፍነው የተወሰዱ ህጻናትን ለማስለቀቅ በሚል ወደጎረቤት ደቡብ ሱዳን የገቡ የኢትዮጵያ ወታደሮች ከነዋሪዎች ጋር አለመግባባት ውስት መሆናቸውን የሃገሪቱ መገናኛ ብዙሃን አርብ ዘገቡ። ከጋምቤላ ክልል በቅርቡ ርቀት ላይ ከሚገኘው የፓቻላ ግዛት የሚኖሩት ነዋሪዎች ወታደሮች በእለት ከእለት እንቅስቃሴያቸው የጸጥታ ስጋትን አሳድረውባቸው እንደሚገኝም አስታውቀዋል። በፓቻላ አስተደደር አካባቢ ወሰጥ ሶስት ሺ የሚጠጉ የኢትዮጵያ ወታደሮች ሰፍረው እንደሚገኙ የተናገሩት ...
Read More »የኢትዮጵያ መንግስት በጎርፍ ከ 100 ሰዎች በላይ መሞታቸውን አስታወቀ
ኢሳት (ግንቦት 5 ፥ 2008) ሰሞኑን በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች በከፍተኛ ሁኔታ የዘነበውን ዝናብ ተከትሎ በተከሰተው የጎርፍ አደጋ፣ ከ100 በላይ ዜጎች በመሬት መደርመስና መሞታቸውንና በደራሽ ጎርፍ መወሰዳቸውን መንግስት አስታወቀ። በወቅታዊ ጎዳዮች ላይ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ የሰጡት የመንግስት ኮሚውኒኬሽን ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ፣ ከመጋቢት ወር ጀምሮ በተከሰተው በዚሁ ጎርፍ አያሌ ዜጎች ተጎድተዋል በማለት ተናግረዋል። አቶ ጌታቸው ማክሰኞ ዕለት ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት ጋዜጣዊ ...
Read More »በአዋሽ ወንዝ ሙላት ከሶስት ሺ ነዋሪዎች በላይ ተፈናቀሉ
ኢሳት (ግንቦት 5 ፥ 2008) በኢትዮጵያ በተለያዩ ክልሎች እየጣለ ያለው ከባድ ዝናብ ለአዋሽ ወንዝ መሙላት ምክንያት ሆኖ 300ሺ ነዋሪዎች ከቀያቸው ተፈናቀሉ። በክልሉ አሚባራ ወረዳ የደረሰው ይኸው የጎርፍ አደጋ በተለያዩ መሰረተ ልማቶች ላይም ከባድ ጉዳት ማድረሱን ከሃገር ቤት የተገኘው መረጃ አመልክቷል። የመከላከያ ሰራዊት አባላትና ሌሎች የነፍስ አድን ሰራተኞችም ነዋርዎችን ለከፋ አደጋ ለመታደግ ርብርብን እያደረጉ የሚገኝ ሲሆን የወንዙ ሙላት በቀጣዮቹ ቀናቶችም እየጨመረ ...
Read More »በዲላ ከተማ የመከላከያ ሰራዊት አባላት መንገድ ዘግተው ፈተሻ ሲያደርጉ ዋሉ
ግንቦት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጡት፣ የመከላከያ ስራዊት አባላትና የፌደራል ፖሊስ አባላት መንገዶችን ዘግተው ፍተሻ ሲያደርጉ እንዲሁም በመኪና ላይ ሆነው ቅኝት በማድረግና የሚጠርጥሩዋቸውን ወጣቶችም ይዘው ሲጠይቁ መዋላቸውን ተናግረዋል። ወታደራዊ ፍተሻውና ቅኝቱ፣ በመንግስት ታጣቂዎችና በአርበኞች ግንቦት 7 መካከል በአርባምንጭ አካባቢ የተፈጠረውን ጦርነት ተከትሎ የተካሄድ ሊሆን እንደሚችል ነዋሪዎች ተናግረዋል። ፍተሻውን እና ጥበቃውን በተመለከተ በአካባቢው ያሉ ባለስልጣናትን ...
Read More »በዶ/ር ቴዎድሮስ ሲመራ የነበረው ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ከግሎባል ፈንድ የተሰጠውን ገንዘብ ከስምምነት ውጪ መጠቀሙና ማጉደሉ ተገለጠ
ግንቦት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የጤና ጠበቃ ሚኒስቴርን መርተው ለውጤት እንዳበቁት በመግለጥ ፣ የአለም የጤና ድርጅት መሪ ለመሆን የቅስቅሳ ስራ የጀመሩት ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም፣ ኤች አይ ቪ ኤድስንና ሌሎች ተላላፊ በሽታዎችን ለመዋጋት በሚል ከግሎባል ፈንድ ለህዝብ የተሰጠውን ገንዘብ ከስምምነት ውጭ ለሌሎች አላማዎች መጠቀማቸውን የሚያመለክት የኦዲት ሪፖርት ቀርቦባችዋል። ግሎባል ፈንድ በአውሮፓውያን አቆጣጥር በ2010 ፣ 1 ቢሊዮን 3 ...
Read More »በካራሚሌ 4 ሴቶች በወታደሮች ተደፍረው ሆስፒታል ገቡ
ግንቦት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በምስራቅ ሃረርጌ ሰሞኑን የተነሳውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ ከምስራቅ እዝ የተላኩት ወታደሮች 5 ውጣት ሴቶችን አስገድደው መድፈራቸውንና ጉዳተኞችም ሆስፒታል መተኛታቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። አንድ የ 7ኛ ክፍል ተማሪ በ4 ወታደሮች በቡድን በመደፈሩዋ ለህይወት አስጊ በሆነ ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ ነዋሪዎች ገልጸዋል። በከተማው ያለው ወጥረትም እንዳለ መሆኑን የሚናገሩት ነዋሪዎች፣ በርካታ ስዎች ተይዘው ታስረዋል። በከተማዋ ...
Read More »በደንቢያ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ መምህራን አድማ አደረጉ
ግንቦት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መምህራኑ ዛሬ ከጠዋቱ 4 ሰአት ጀምሮ የስራ ማቆም አድማ ያደርጉ ሲሆን፣ መንግስትን የሚያውግዙ መፈክሮችን ሲያሰሙ እንደነበር ምንጮች ገልጸዋል። አድማውን ትከትሎ ትምህርት በመቁዋርጡ ተማሪዎች ወደ ቤታቸው እንዲሄዱ ተደርጎአል። ባድማው የተሳትፉ መምህራንን ለማነጋገር ሙከራ ብናደርግም፣ ከሰአት በሁዋላ ወደ ስብሰባ በመግባታቸው ሳይሳካልን ቀርቶአል። መምህራኑ መብታችን ሳይከብር ስራ አንጀምርም ማለታቸውን ተማሪዎች ለኢሳት ተናግረዋል።
Read More »በጄኒራል ክንፈ ዳኘው የሚመራው ሜቴክ የአባይ ግድብ ግንባታን በሶስተኛ ኩባንያ እያሰራ ነው
ግንቦት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከ77 ቢሊዮን ብር በላይ ገንዘብ ተከፍሎት ከ10 የስኳር ኮርፖሬሽን ፋብሪካዎች መካከል አንዱንም ማጠናቀቅ ያልቻለው የብረታብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ለአባይ ግድብ የኤሌክትሮ ሜካኒካል ስራውን ለመስራት ኮንትራት ቢወስድም፣ ሰራውን መስራት ባለመቻሉ የውጭ ኮንትራክተር ቀጥሮ እያሰራ ነው። የውጭ ኩባንያዎች በአማካሪ ስም ቢቀጠሩም ዋናውን ስራ የሚሰሩት እነሱ ናቸው። አዳማ የእርሻ መሳሪያዎች ማምረቻ ኢንዱስትሪ፣ አዳማ ጋርመንት ...
Read More »በዛንቢያ 41 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ተፈረደባቸው
ግንቦት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሊዋንጉዋ ማጀስትሬ ከፍተኛው ፍርድ ቤት በትናንትናው እለት በዋለው ችሎት በሕገወጥ መንገድ ወደ ዛንቢያ ገብተዋል ባላቸው 41 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ላይ የፍርድ ውሳኔ አሳልፏል። ፍርድ ቤቱ የአገሪቱን የሕገወጥ ስደተኞች ሕግ አንቀጽን በመጥቀስ እያንዳንዳቸው ስደተኞች 1 ሽህ 500 የዛንቢያ ክዋቻ እንዲከፍሉ ወይም የሶስት ወራት ጽኑ እስራት ይታሰሩ ዘንድ የፍርድ ብያኔውን ሰጥቷል። በሕገወጥ መንገድ ወደ ...
Read More »