ኢሳት (ሃምሌ 28 ፥ 2008) በመገንባት ላይ ያለው የአባይ ግድብ በታችኛው ተፋሰስ ሃገራት ላይ የሚያመጣው ተፅዕኖ የለም ሲል የቆየው የኢትዮጵያ መንግስት ግድቡ ተፅዕኖ እንደሚኖረው ከተረጋገጠ የማስተካከያ እርምጃን እንደሚወስድ ለግብፅ መንግስት ማረጋገጫ ሰጠ። የውሃ ሃብት ሚንስትሩ አቶ ሞቱማ መካሳ ሃገራቸው ግድቡ በተለይ በግብፅና ሱዳን ላይ የሚያመጣው ተፅዕኖ መኖሩ በባለሙያዎች ከተረጋገጠ ተፅዕኖውን ለመቀነስ ኢትዮጵያ ዝግጁ መሆኗን ለግብጹ አክባር አልዩም ጋዜጣ በሰጡት ቃለምልልስ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የተመድ ሰራተኞች ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል በሚደረገው ህዝባዊ ተቃውሞ ጋር በተገናኘ የጥንቃቄ እርምጃ እንዲወስዱ ተጠየቀ
ኢሳት (ሃምሌ 28 ፥ 2008) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰራተኞች በሚቀጥሉት ቀናት በኢትዮጵያ በተለይም በኦሮሚያ ክልል ሰላማዊ ሰልፍ በሚካሄድባቸው ቦታዎች የጥንቃቄ እርምጃ እንዲወስዱ በተባበሩት መንግስታት የጸጥታና ደህንነት ክፍል ባለስልጣን ገለጹ። ማርኮ ስሞልነር የተባሉ የተባበሩት መንግስታት የደህንነትና የጸጥታ ክፍል ባለስልጣን ባሰራጩት የኢሜይል መልዕክት፣ በሚቀጥለው ቅዳሜና እሁድ በኦሮሚያ ክልል በሁሉም የዞንና የወረዳ ከተሞች ሰላማዊ ሰልፎች ሊደረጉ ስለሚችሉ፣ የተመድ ሰራተኞች የጥንቃቄ እርምጃ እንዲወስዱ ጠይቀዋል። ...
Read More »አዲስ አበባን ጨምሮ በኦሮምያ፣ ባህርዳርና ደብረታቦር የሚደረገውን የተቃውሞ ሰልፍ የተሳካ ለማድረግ ዝግጅቶች እየተካሄዱ ነው
ሐምሌ ፳፰ ( ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፊታችን ቅዳሜ በዋና ከተማዋ አዲስ አበባን ጨምሮ በመላው ኦሮምያ፣ በባህርዳር ከተማ እና በደብረታቦር ከተማ የተለያዩ የመብት ጥያቄዎችን የሚያቀነቅኑ የተቃውሞ ሰልፎች ይደረጋሉ። በእነዚህ ሰልፎች ላይ የህወሃት አገዛዝ እንዲያበቃ ጥሪ ይቀርባል። ሰልፉ በኦሮምያ የደረሰውን ጭፍጨፋ እንዲሁም የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ምንነት የኮሚቴ አባላት መታሰራቸውን ያወግዛል። በኦሮምያና በባህርዳር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የሰልፉን ቀን በጉጉት እየጠበቁት ...
Read More »አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ አገሪቱ ከባድ የህልውና አደጋ ከፊቷ ተደቅኗል አሉ ሌሎች ወገኖች ግን አደጋው ለኢህአዴግ ህልውና እንጅ ለኢትዮጵያ አይደለም ይላሉ
ሐምሌ ፳፰ ( ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በባህርዳር ሲካሄድ በሰነበተው የዲያስፖራ በአል ላይ የተገኙት ሃይለማርያም ደሳለኝ፣ ኢትዮጵያ ከባድ የህልውና አደጋ እንደተደቀነባት ተናግረዋል። የጠባብነትና የትምክህትነት አደጋ ከፊታችን እንዳለ ዛሬ ሳይሆን አስቀድመን አውቀናል ያሉት አቶ ሃይለማርያም፣ ይህ ደግሞ አገራችንን ወደ ማትመለስበት የብሄር ግጭት አደጋና የእርስ በርስ ጦርነት ይከታታል ሲሉ ገልጸዋል። ሁላችንም ይህን ጠባብነትና ትምክት ተረባርበን ካላስቆምነው እስከዛሬ የተጓዝንበትን ሁሉ ...
Read More »በእስራኤል የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት ድጋፋቸውን ገለጹ የሚፈጸመውን ግድያም አወገዙ
ሐምሌ ፳፰ ( ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በእስራኤል የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ቤተ እስረኤላውያን የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት ጥያቄን ደግፈው፣ ከዚሁ ጋር በተያያዘ የታሰሩት ሁሉ እንዲለቀቁ ጠይቀዋል። በኦሮምያ የሚፈጸመውን ግድያ አውግዘዋል። የታሰሩት ሁሉ እንዲፈቱ ጠይቀዋል። ኢትዮጵያውያኑ ወደ ኪዳነምረት ቤተክርስቲያን በማምራት ገዢው ፓርቲ የሚጠቀምበትን ሰንደቅ አላማ በማውረድ ኮከብ የሌለውን ሰንደቃላማ ሰቅለዋል። ድርጊቱን በተመለከተ ከአዘጋጆቹ አንዱ የሆነው አቶ ማስተዋል ጥላሁን ድርጊቱን ...
Read More »በወልቃይት ጠገዴ ጥያቄ ዙሪያ የአመራር ክፍፍል መኖሩን አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ገለጹ
ሐምሌ ፳፯ ( ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ጠ/ሚኒስትሩ በባህርዳር በመካሄድ ላይ ባለው የዲያስፖራ ውይይት ላይ ፣ የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ጥያቄ ህዝባዊነት የሌለውና በ አመራሮች የሃሳብ ልዩነት የመጣ መሆኑን በመግለጽ መፍትሄውም አመራሩን ማስተካከል ነው ብለዋል። ጠ/ሚኒስትሩ የትኛው አመራር ምን አይነት አቋም እያራመደ እንደሆነ ከመገልጽ ቢቆጠቡም፣ ከዚህ በፊት በተወሰኑ ከፍተኛ የብአዴን አመራሮችና በህወሃት አመራሮች መካከል ልዩነት መፈጠሩ ሲነገር ...
Read More »በአወዳይ ከፍተኛ የሰብአዊ ቀውስ አጋጥሟል ተባለ
ሐምሌ ፳፯ ( ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኦሮምያ ክልል ምስራቅ ሃረርጌ ዞን አወዳይ ከተማ ባለፈው እሁድ ተነስቶ የነበረውን ተቃውሞ ተከትሎ ከ11 ሰዎች በላይ ከተገደሉ በሁዋላ፣ አካባቢውን የተቆጣጠሩት የመከላከያ ሰራዊት አባላትና የፌደራል ፖሊሶች ማንኛውም ሰው ከቤቱ እንዳይወጣ እገዳ በመጣላቸው፣ ህጻናትና እናቶችን ጨምሮ ህዝቡ ከፍተኛ ስቃይ ውስጥ መግባቱ ታውቋል። ወኪላችን እንደገለጸው አብዛኛው ህዝብ ከቤት አትወጣም በመባሉ የሚበላው አጥቶ ...
Read More »በኦሮሚያ በዴሳ ከተማ ሁለት ሰዎች በመንግስት ጸጥታ ሃይሎች ተገደሉ
ኢሳት (ሃምሌ 26 ፥ 2008) በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ሃረርጌ ዞን ስር በምትገኘው የበዴሳ ከተማ ማክሰኞ ተጨማሪ ሁለት ሰዎች በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ተገደሉ። በከተማዋ ሰኞ የተገደሉት ሁለት ሰዎችን ማክሰኞ ለመቅበር በተካሄደ ስነ-ስርዓት ላይ የጸጥታ ሃይሎች ተኩስ በመክፈት ተጨማሪ ሁለት ሰዎች እንዲሞቱ ማድረጋቸውን እማኞች ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ አስረድተዋል። የአራቱ ሟቾችን ስም በመጥቀስ ስለድርጊቱ እማኝነታቸውን የሰጡት የበዴሳ ከተማ ነዋሪዎች በከተማዋ ከፍተኛ የጸጥታ ...
Read More »የትግራይ ተወላጆች በሰሜን አሜሪካ ማህበር በዶ/ር አዲስ አለም ባሌማ ላይ የቀረበው ተቃውሞ በሻዕቢያና በትምክህተኞች ትብብር የተፈጸመ ነው ሲል መግለጫ አወጣ
ኢሳት (ሃምሌ 26 ፥ 2008) ባለፈው እሁድ ዋሽንግተን ዲሲ ሲደርሱ ከፍተኛ ተቃውሞ የቀረበባቸው የትግራይ ክልል ምክትል ፕሬዚደንትን በተመለከተ የትግራይ ተወላጆች በሰሜን አሜሪካ ማህበር መግለጫ አወጣ። ማህበሩ ባወጣው በዚህ መግለጫ ሻዕቢያና ትምክህተኞችን በመተባበሩ የፈጸሙት ተግባር ነው ሲሉ በትግራይ ክልል ም/ፕሬዚደንት ላይ የደረሰውን ተቃውሞ አውግዟል። ረቡዕ ሃምሌ 27, 2008 በሚጀምረው የትግራይ ተወላጆች በሰሜን አሜሪካ በዓል ላይ ለመገኘት እሁድ ሃምሌ 24, 2008 ...
Read More »በሱዳንና ግብፅ ድንበር 600 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በቁጥጥር ስር ዋሉ
ኢሳት (ሃምሌ 26 ፥ 2008) የሱዳን መንግስት የጸጥታ ሃይሎች ሃገሪቱ ከሊቢያ እና ከግብፅ ጋር በምትዋሰንበት ድንበር አካባቢ 600 ኢትዮጵያውያን ስደተኖችን በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን ሰኞ አስታወቁ። ሃገሪቱ በሰኔ ወር ህገወጥ የተባሉ ስደተኞችን ለመቆጣጠር ልዩ የጸጥታ ሃይሏን በድንበር አካባቢ ያሰፈረች ሲሆን፣ በርካታ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በዚሁ ዘመቻ እየተያዙ መሆኑን ሱዳን ትሪቢዩን ጋዜጣ ወታደራዊ ሃላፊዎችን ዋቢ በማድረግ ዘግቧል። የሱዳን የድንበር ልዩ የጸጥታ ሃይሎች ተወካይ ...
Read More »