.የኢሳት አማርኛ ዜና

የብአዴን የክፍለ ከተማ አመራሮች ተቃውሞአቸውን አሰሙ

ነሃሴ  ፲፩ ( አሥራ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ነሃሴ 11 ቀን 2008 ዓም በአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ስም በባህርዳር ከተማ የሚገኙ የክፍለ ከተማ አመራሮች ስብሰባ የተጠሩ ቢሆንም፣ በስብሰባው ላይ የተገኙት የህውሃት አመራሮች ሆነው መገኘታቸው ውዝግብ አስነስቷል። ሰብሳቢው “ በወልቃይት ላይ የሚነሳው የአማራነት ጥያቄ ወቅቱን ያልጠበቀ መሆኑንና ጉዳዩን ሊመለከቱት የሚገባቸው የአካባቢው ነዋሪዎችና የክልል አንድ አመራሮች ...

Read More »

በምስራቅ ሸዋ ሆራ ፈጀሶ የተባለ ወጣት አንድ የአጋዚ ወታደር ገድሎ ሌላ አንድ የፌደራል ፖሊስ ካቆሰለ በሁዋላ ተገደለ።

ነሃሴ  ፲፩ ( አሥራ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከሌሊቱ 10 ሰአት ላይ ወታደሮቹ  “የጦር መሳሪያ አለህና አውጣ” ብለው  የቤቱን በር በሃይል ሰብረው ሲገቡ፣ ወጣት ሆራ እጄንማ አልሰጥም ብሎ አንዱን ግንባሩ ላይ በሽጉጥ መትቶ ሲገድለው፣ ሌላውን ደግሞ ሆዱ አካባቢ መትቶ ጥሎታል። የአጋዚው ወታደር ወዲያኑ ህይወቱ ሲያልፍ፣ የፖሊስ አባሉ ደግሞ ሆስፒታል ገብቷል። በዚህ የተበሳጩት ወታደሮች ወጣቱን ከገደሉት በሁዋላ በአስከሬኑ ...

Read More »

በጋምቤላ  የኦሮሞ ተወላጅ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች  ለምን ዘመራችሁ በሚል መታሰራቸው ታወቀ

ነሃሴ  ፲፩ ( አሥራ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኦሮምያ በመካሄድ ላይ ካለው ህዝባዊ ተቃውሞ ጋር በተያያዘ 21 የኦሮሞ ተወላጅ የፕሮቴስታንት ሃይማኖት ተከታዮች ሃምሌ 30 ቀን 2008 ዓም መታሰራቸውን ኢሳት ዘግቦ ነበር።  አማኞቹ ከጥምቀት ቦታ እየዘመሩ ወደ ቤተክርስቲያናቸው እየሄዱ ሳለ፣ የክልሉ ልዩ ሃይል አባላት ዝማሬው የተቃውሞ መስሎአቸው ሁሉንም ካገቱ በሁዋላ እየደበደቡ አስረዋቸዋል። ምእመናኑ ሲዘምሩ የነበረው የምስጋና የአምልኮ መዝሙር ...

Read More »

በኢትዮጵዊያን ላይ የሚፈጸመውን ግድያ የሚያወግዙ የተቃውሞ ሰልፎች እየተደረጉ ነው

ነሃሴ  ፲፩ ( አሥራ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአውሮፓና አሜሪካ የተለያዩ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የህወሃት ኢህዴግን የጅምላ ግድያና እስራት በማውገዝ ሰላማዊ ሰልፎች እያደረጉ ነው። በፈረንሳይ ዋና ከተማ ፓሪስ በተደረገ የሰላማዊ ሰልፍ ያልታጠቁ ሰላማዊ ዜጎች ላይ መተኮስ ወንጀል ነው፣ በደም የወጣ ስልጣን አይቆምም፣ ዘረኛ መንግስት ዘረኛ ነው፣ የመሬት ወረራው ይቁም፣ የሚሉ መፈክሮችን ተሰምተዋል። በደቡብ ኮሪያ የሚኖሩ ...

Read More »

የደብረ ማርቆስ ከተማ ነዋሪዎች የስራ ማቆም አድማ መጀመራቸውን አስታወቁ

ኢሳት (ነሃሴ 10 ፥ 2008) በሳምንቱ መገባደጃ ቅዳሜ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍን ያካሄዱ የደብረ ማርቆስ ከተማ ነዋሪዎች ማክሰኞ ከሰዓት በኋላ ጀምሮ የስራ ማቆም አድማ ማድረግ መጀመራቸውን ነዋሪዎች ለኢሳት አስታወቁ። የከተማዋ ነዋሪዎች ማከሰኞ ጠዋት ከዞንና ከከተማው አስተዳደር ሃላፊዎች ጋር ምክክርን በማካሄድ ለእስር የተዳረጉ የከተማዋ ነዋሪዎች በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጥያቄ ማቅረባቸው ታውቋል። ነዋሪዎቹ ያቀረቡት ጥያቄ ምላሽን እስኪያገኝ ድረስ የስራ ማቆም አድማ እንደሚጀምሩ ለሃላፊዎቹ በውይይቱ ...

Read More »

ኢትዮጵያ የእርሻ ምርቷ ክፉኛ ጉዳት እንደሚደርስባት ተመድ አስታወቀ

ኢሳት (ነሃሴ 10 ፥ 2008) በተያዘው አመት የዝናብ እጥረት ምክንያት ለድርቅ አደጋ የተጋለጠችው ኢትዮጵያ፣ ዳግም በሚከሰት የቅዝቃዜ የአየር ንብረት ለውጥ የእርሻ ምርቷ ክፉኛ ጉዳት እንደሚደርስባት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አሳሰበ። ሃገሪቱን ከጥቅምት ወር ጀምሮ ይመታታል ተብሎ የሚጠበቀው ይኸው ቀዝቃዛ የአየር ንብረት ለውጥ የእርሻ ምርት እንዲቀንስ በማድረግ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ለምግብ ድጋፍ ይዳርጋል ሲል ድርጅቱ ማክሰኞ ባወጣው ማሳሰቢያ አመልክቷል። ጉዳዩ እጅግ አሳሳቢ ...

Read More »

በግብፅ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ከ150 በላይ ስደተኞች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ኢሳት (ነሃሴ 10 ፥ 2008) በግብጽ የሜዲትራኒያን ባህር ግዛት ወደ ተለያዩ የአውሮፓ ሃገራት በህገወጥ መንገድ ሲጓዙ ነበሩ የተባሉ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ከ150 በላይ የተለያዩ የአፍሪካ ሃገራት ስደተኞች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የግብፅ የባህር ሃይል ባለስልጣናት አስታወቁ። በሃገሪቱ በኩል ወደ አውሮፓ ለመሰደድ የሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ድርጊቱ አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱን ዴይሊ ኒውስ ኢጂፕት የተሰኘ ጋዜጣ ባለስልጣናትን ግቢ በማድረግ ዘግቧል። በቁጥጥር ስር የዋሉትን ...

Read More »

በጎንደር ከተማ ከቤት ላለመውጣት የተጀመረው አድማ ለሶስተኛ ቀን ቀጥሎ ዋለ

ኢሳት (ነሃሴ 10 ፥ 2008) በጎንደር ከተማ ከቤት ላለመውጣት የተጀመረው አድማ ለሶስተኛ ቀን ማክሰኞ መቀጠሉንና ሁሉም የመንግስትና የግል ድርጅቶች ተዘግተው እንደሚገኙ የከተማዋ ነዋሪዎች ለኢሳት አስታወቁ። ለተለያዩ አስቸኳይ ጉዳዮች ከቤት የሚወጡ ነዋሪዎች ጥቁር ልብስን በመልበስ ብቻ የተወሰኑ እንቅስቃሴዎችን እንደሚያደርጉ እነዚሁ ለደህንነታቸው ሲሉ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ ነዋሪዎች ከዜና ክፍላችን ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ገልጸዋል። በቅርቡ በጎንደርና እና በባህርዳር ከተሞች የተፈጸመ ግድያ በመቃወም ከቤት ...

Read More »

በጎንደር የስራ ማቆም አድማው ለሶስተኛ ቀናት ቀጥሎአል

ነሃሴ  ፲ ( አሥር) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ተመሳሳይ ተቃውሞች በሌሎች ከተሞችም ይደረጋሉ በጎንደር በአደባባይ ሲደረግ የነበረው ተቃውሞ ወደ ስራ ማቆም እና ከቤት ያለመውጣት አድማ ከተቀየረ በሁዋላ ፣ ሁሉንም የከተማዋ ነዋሪዎች በአንድነት ያሳተፈ የስራ ማቆም እና ከቤት ያለመውጣት አድማ ውጤታማ በሆነ መልኩ እየተካሄደ ነው። ካለፉት ሶስት ቀናት ጀምሮ የንግድ ድርጅቶች አልተከፈቱም፣ ታክሲዎች አውቶቡሶች እና ሌሎች ተሽከርካሪዎች ስራ አቁመዋል። ...

Read More »

በጋምቤላ 20 የኦሮሞ ተወላጆች የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች ታሰሩ

ነሃሴ  ፲ ( አሥር) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኦሮምያ በመካሄድ ላይ ካለው ህዝባዊ ተቃውሞ ጋር በተያያዘ 20 የኦሮሞ ተወላጅ የፕሮቴስታንት ሃይማኖት ተከታዮች አምልኮ ከሚያደርጉት ቤተክርስቲያን ተይዘው ወደ እስር ቤት ተወስደዋል። በእጃቸው ላይ ከመጽሃፍ ቅዱስ በስተቀር ሌላ ምንም ነገር ያልያዙት አማኞች፣ ኦሮሞ ስለሆኑ ብቻ መታሰራቸውን ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የቤተክርስቲያን ምንጮች ገልጸዋል። ሰዎቹ ለአንድ ሳምንት ያክል በጋምቤላ እስር ቤት ሲቆዩ ፍርድ ...

Read More »