.የኢሳት አማርኛ ዜና

በሰቆጣ የመንግስት ባለስልጣናት በሸደይ በአል ላይ ሳይገኙ ቀሩ

ነሃሴ  ፲፮ ( አሥራ  ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሰቆጣ ከተማ በእያመቱ የሚከበረውን የሸደይ በአል ለማክበር የፌደራል እና የክልል መንግስታት ከፍተኛ ባለስልጣናት ይገኛሉ ተብሎ ቢጠበቅም፣ ሳይገኙ ቀርተዋል። በአሉ በእያመቱ በደመቀ ሁኔታ ይከበራል። ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት በበአሉ ላይ እየተገኙ ንግግር የማድረግ ልማድ ቢኖራቸውም፣ በዘንድሮው በአል ላይ ግን አልተገኙም። ባለስልጣናቱ በበአሉ ላይ ለመገኘት ለምን እንዳልፈለጉ ባይታወቅም አንዳንድ ወገኖች በተለያዩ የአገሪቱ ...

Read More »

የአሜሪካ መንግስት ዜጎቹ በኢትዮጵያ ውስጥ በሚያደርጉት እንቅስቃሴ የጥንቃቄ እርምጃዎችን እንዲወስዱ አሳሰበ

ኢሳት (ነሃሴ 13 ፥ 20108) በኦሮሚያና አማራ ክልሎች እየተካሄዱ ያሉ ህዝባዊ ተቃውሞዎች ወደ መዲናይቱ አዲስ አበባ ሊዛመቱ ይችላሉ በሚል የአሜሪካ መንግስት ዜጎች በእንቅስቃሴያቸው ላይ የጥንቃቄ እርምጃዎችን እንዲወስዱ አርብ አሳሰበ። በሃገሪቱ እየተካሄዱ ባሉ ተቃውሞዎች ዙሪያ መግለጫን ያወጣው የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በሁለቱ ክልሎች በመካሄድ ላይ ያለው ተቃውሞ ወደ ሌሎች ክልሎችና አዲስ አበባ ሊዛመት እንደሚችል ማሳሰቢያ መውጣቱን ሮይተርስ ዘግቧል። መቀመጫውን በአዲስ አበባ ...

Read More »

የአዲስ አበባ ህዝባዊ እምቢተኝነት አስተባባሪ ኮሚቴ እሁድ የሚካሄደውን የተቃውሞ ሰልፍ አስመልክቶ መግለጫ አወጣ

ኢሳት (ነሃሴ 13 ፥ 20108) የአዲስ አበባ ህዝባዊ እምቢተኝነት አስተባባሪ ኮሚቴ በቀጣይ እሁድ በአብዮት አደባባይ ለሚካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ ህዝቡ በነቂስ እንዲወጣ ጥሪ አቀረበ። ኮሚቴው ነሃሴ 13 ቀን 2008 ዓም ባወጣው መግለጫ፣ ሃገራችን ኢትዮጵያ ከጫፍ እስከ ጫፍ እየተቀጣጠለ ባለ ህዝባዊ እምቢተኝነት ውስጥ እንደምትገኝ፣ በተለይም በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች በተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ  ከ700 በላይ ወገኖቻችን መገደላቸው፣ በ10ሺዎች ለእስር እንግልትና መሰወር መዳረጋቸውን ገልጸዋል። የአዲስ ...

Read More »

በህወሃት/ኢህአዴግ ባለቤትነት የሚተዳደረው ፋና በግል ድርጅት ስም የንግድ ቴሌቪዥን ፈቃድ ተሰጠው

ኢሳት (ነሃሴ 13 ፥ 20108) የህወሃት የግል ንብረት የሆነው ሬዲዮ ፋና በግል ድርጅት ስም የመጀመሪያን የንግድ ቴሌቪዥን ስርጭት ፈቃድ ተሰጠው። የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ባለስልጣን የቴልቪዥን ፍቃድ የመስጠት ስልጣን የተሰጠው ቢሆንም፣ እስካሁን ድረስ ለማንም የግል ድርጅት ፍቃድ ሳይሰጥ ቆይቷል። ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ባለፉት ጊዚያቶች ይፋ እንዳደረገው ከሆነ፣ የግል ንግድ ቴሌቪዥን ስርጭት ለመጀመር ጥያቄ ያቀረቡት የህወሃት ኢህአዴግ ኩባንያዎች የሆኑት ሬዲዮ ፋና፣ ዋልታ ኢንፎርሜሽን ...

Read More »

የኢትዮጵያ መንግስት ተመድ በአማራና ኦሮሚያ ለተፈጸሙት ግድያዎች የማጣራት ጥያቄ ይፋዊ የእምቢተኝነት ምላሽ ሰጠ

ኢሳት (ነሃሴ 13 ፥ 20108) የኢትዮጵያ መንግስት ተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች የተፈጸሙ ግድያዎች በገለልተኛ አካል እንዲጣራ ለቀረበለት ጥያቄ ተባባሪ እንደማይሆን ይፋዊ የጽሁፉ ምላሽን ሰጠ። በክልሎቹ እየተካሄዱ ያሉ ህዝባዊ ተቃውሞዎችን “ህገወጥና በሽብርተኛ ቡድኖች” የሚካሄዱ ናቸው ሲል በምላሹ ያሰፈረው መንግስት ከተቃውሞው ጋር በተገኛኘ የሞቱ ሰዎችን ጉዳት የደረሰባቸውን አካላት ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ጋር በመተባበር የራሱን ማጣራት እንደሚያካሄድ አስታውቋል። የተባበሩት መንግስታት ...

Read More »

የእብናት ነዋሪዎች ስብሰባ ረግጠው ወጡ

ነሃሴ  ፲፫ ( አሥራ  ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሰሜን ጎንደር ዞን በእብናት ወረዳ የሚገኙ ነዋሪዎች የወረዳው ባለስልጣናት የጠሩትን ስብሰባ ረግጠው ወጥተዋል። ባለስልጣናቱ በስፍራው ለተገኙ የንስሃ አባቶች በእየቤቱ እየዞሩ መንፈሳዊ ልጆቻቸውን እንዲመክሩ፣ የእስልምና አባቶችም ተመሳሳይ ሚናቸውን እንዲወጡ ቅስቀሳ ሲጀምሩ፣ ህዝቡ “እናንተ ጥያቄያችንን በሰላማዊ መንገድ ባቀረብን ወታደር አምጥታችሁ አስገደላችሁን ፣ ከኢህ በሁዋላ ከእናንተ ጋር የሚያገናኘን ነገር የለም” በሚል በአንድ ...

Read More »

በደብረዘይት የህወሃት የአየር ሃይል አባላት ወደ ትግራይ ተላኩ

ነሃሴ  ፲፫ ( አሥራ  ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአየር ሃይል ምንጮች እንደገለጹት ከኢታማዦች ሹሙ በተሰጠ ትእዛዝ መሰረት የህወሃት አባላት የሆኑ የአየር ሃይል አባላት ተንቤን በሚከበረው የአሸንዳ በአል ላይ እንዲገኙ በሚል ሰበብ ወደ ትግራይ እንዲሄዱ ታዘዋል። ነሃሴ 9 ቀን 2008 ዓም የተጻፈውን ደብዳቤ ተንተርሶ የአየር ሃይል አባላቱ ወደ ትግራይ የተጓዙ ሲሆን፣ ስለወቅቱ ሁኔታ መመሪያ ይሰጣቸዋል ተብሎ ይጠበቃል። የአሸንዳ በአል ...

Read More »

ዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ በሃይል እጥረት ሳቢያ ለማምረት አለመቻሉን ለደንበኞቹ ገልጸ፡፡

ነሃሴ  ፲፫ ( አሥራ  ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመላው አማራ የህውሃት/ኢህአዴግን ምርት ላለመጠቀም በተማማለው ህዝብና ነጋዴ ምክንያት ተጠቃሚ ያጣው  የሞሰቦ ስሚንቶ ምርት ወደ ገበያ ለማስገባት አገዛዙ  የዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካን በኃይል በመቆራረጥ ምርቱን ለደንበኞቹ ለማቅረብ እንዳይችል ማድረጉን ምንጮች ገለጹ:፡ የክልሉ ነጋዴዎች በአማራው ህዝብ ላይ የሚደረሰውን ግፍና ግድያ ለመቃወም የመሰቦ ስሜንቶ ምርትን ላለመጠቀም የወሰኑ ሲሆን፣ ድርጊቱ ያበሳጨው ህወሃት መራሹ መንግስት ...

Read More »

ተመድ በኢትዮጵያ የተፈጸመውን ግድያ የማጣራት ጥያቄ የልማት ኣጋሮች እንዲደግፉት ሂውማን ራይትስ ዎች ጠየቀ

ኢሳት (ነሃሴ 12 ፥ 2008) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በኢትዮጵያ የተፈጸሙ ግድያዎች በገለልተኛ አካል እንዲጣራ ያቀረበውን ጥሪ የሃገሪቱ የልማት አጋሮች እንዲደግፉት ሂውማን ራይትስ ዎች ጠየቀ። የሃገሪቱ የልማት አጋሮች የድርሻቸውን ተጽዕኖ ማሳደር ይኖርባቸው ሲል የገለጸው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ ድርጊቱ መንግስት ያለተጠያቂነት ሰላማዊ ሰልፈኞችን መግደል እንደማይችል ጠንካራ መልዕክትን የሚያስተላልፍ ነው ሲሉ አስታውቋል። የልማት አጋሮች የሚወስዱት እርምጃ ለመንግስት ከሚያስተላልፈው መልዕክት ...

Read More »

ኢትዮጵያ በቢጫ ወባ በሽታ ስርጭት ሰለባ ልትሆን እንደምትችል ተነገረ

ኢሳት (ነሃሴ 12 ፥ 2008) ኢትዮጵያን ጨምሮ የወባ በሽታ ተጋላጭ የሆኑ የአፍሪካ ሃገራት በአንጎላና ዴሞክራቲክ ሪፕሊክ ኮንጎ እየተስፋፋ ባለው የቢጫ ወባ በሽታ ስርጭት ሰለባ ሊሆኑ እንደሚችሉ የአለም ጤና ድርጅት ረቡዕ አሳሰበ። ካለፈው ወር ጀምሮ በሁለቱ ሃገራት ከ400 በላይ ሰዎች በበሽታው ስርጭት የሞቱ ሲሆን፣ ከስድስት ሺ የሚበልጡ ተጨማሪ ሰዎች በበሽታው መያዛቸውን ሲ ኤን ኤን የቴሌቪዥን ጣቢያ ዘግቧል። በወባ ትንኝ አማካኝነት የሚተላለፈው ...

Read More »