.የኢሳት አማርኛ ዜና

የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅት አባላትንና ዜጎችን ማሰሩ ቀጥሎአል

ነሃሴ  ፲፰ ( አሥራ  ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በምእራብ ጉጂ ዞን ገላና ወረዳ የሰማያዊ ፓርቲ አስተባባሪ የሆኑት አቶ አራርሶ ጌዶ ትናንት ማክሰኞ በርቲ ቀበሌ ውስጥ ተይዘው ታስረዋል። በአዲስ አበባ 4ኛ ፖሊስ ጣቢያ ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ 56 ወጣቶች ታስረው ከፍተኛ ደብደባ የደረሰባቸው ሲሆን ፣ ምግብ ከቀመሱ በርካታ ቀናትን ያስቆጠሩ በመሆኑ ህይወታቸው አደጋ ላይ ወድቋል። ብዙዎቹ በጠጠር እና እሾህ ...

Read More »

በኢትዮጵያ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በጎርፍ ምክንያት ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቀሉ

ነሃሴ  ፲፰ ( አሥራ  ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ካለፈው መጋቢት ወር ጀምሮ ከመጠን በላይ በሚጥለው ዝናብ በተፈጠረ የጎርፍ መጥለቅለቅ ሳቢያ ከ600 ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊያን ከትውልድ ቀያቸው ተፈናቅለዋል። የጎርፍ አደጋው እስከ ቀጣይ ዓመት ታህሳስ ወር ድረስ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታውቋል።በኢትዮጵያ ዝናቡ ወቅቱን ጠብቆ አለመጣሉን ተከትሎ ካለፈው ዓመት ጀምሮ ባለፉት አስር ዓመታት ውስጥ ተከስቶ የማያውቅ አስከፊ የርሃብ ...

Read More »

በባህር ዳር ከቤት ያለመውጣት አድማ ለሶስተኛ ቀን በተሳካ ሁኔታ ተካሄደ

ኢሳት (ነሃሴ 17 ፥ 2008) የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር እሁድ በነዋሪው የተጀመረው ከቤት ያለመውጣት አድማ እንዲያበቃ ቅስቀሳንና ዛቻን ቢያደርግም አድማው ማክሰኞ ለሶስተኛ ቀን መቀጠሉን ነዋሪዎች ለኢሳት አስታወቁ። ከተማዋ ማክሰኞች ምሽት ድረስ ሙሉ ለሙሉ ከማኛውም እንቅስቃሴ ውጭ ሆና መዋሏን የተናገሩት እማኞች የባህር ዳር ከተማ ንግድ ኢንዱስትሪና ገበያ ልማት መምሪያ የንግድ ተቋማት ስራቸውን እንደሚጀምሩ ማሳሰቢያዎችን ቢያሰራጭም ነዋሪው እምቢተኛ መሆኑን አስረድተዋል። ለሶስት ቀን ...

Read More »

ግብፅ በአባይ ግድብ ዙሪያ የነበረ ስጋቷ እየቀነሰላት እንደመጣ አስታወቀች

ኢሳት (ነሃሴ 17 ፥ 2008) በመገባንት ላይ ባለው የአባይ ግድብ ዙሪያ ላለፉት አራት አመታት ተቃውሞን ስታቀርብ የቆየችው ግብፅ በመካሄድ ላይ ያሉ ድርድሮች ስጋቷን እየቀነሰላት እንደመጣ አስታወቀች። በድርድሩ ዙሪያ ዝርዝር መረጃን ከመስጠት የተቆጠቡት የግብፅ ፕሬዚደንት አብደል ፈታህ አል-ሲሲ ሃገራቸው ከአሁን በሁዋላ የምትፈራው ነገር እንደሌለ ለግብፅ መገናኛ ብዙሃን ይፋ አድርገዋል። ሁለቱ ሃገራት ግድቡ በገለልተኛ አካል ጥናት እንዲካሄድበት እያደረጉ ያለው ድርድር ለሁሉም ወገኖች ...

Read More »

በአማራ ክልል የሚደረገው የስራ ማቆምና ከቤት ያለመውጣት አድማ አድማሱን እያሰፋ ነው

ነሃሴ  ፲፯ ( አሥራ  ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባህርዳርን ለሶስት ቀናት ጸጥ ረጭ ያደረገው የስራ መቆም እና ከቤት ያለመውጣት አድማ ወደ ደባርቅ፣ ቆላ ድባ፣ ጯሂትና ጎርጎራ ከተሞች ተሸጋግሮ በጸጥታ ሃይሎችና በነዋሪዎች ላይ ጉዳት እንዲደርስ ምክንያት ሆኗል። በገበያው ውስጥ ምንም እንቅስቃሴ ባለመኖሩ የገበያው ዋና ዋና በሮች ተዘግተው በገበያው ጠባቂዎች ይጠበቃሉ፡፡በተለይ ከአስራ አንድ ሰዓት በኋላ  ግርግር የሚበዛባቸው የገበያው በሮችና ...

Read More »

ህዝቡ እንደ ሃማስ የከተማ የትጥቅ ትግል ሊጀመር ይችላል ሲል ኢህአዴግ ስጋቱን ገለጸ

ነሃሴ  ፲፯ ( አሥራ  ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢህአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣናት ባደረጉት ስብሰባ ላይ ፣ አሁን በሚታየው አካሄድ የአማራ እና የኦሮምያ ክልል ነዋሪዎች ተቃውሟቸውን  እያጠናከሩ ከመጡ  እንደ ሃማስ መሳሪያ አንግተው ሰፈር ለሰፈር ከመንግስት ጋር የሚታኮሱ ሃይሎች እንደሚፈጠሩ፣ ጥያቄያቸውም ከሰፈር ነፃነት ጥያቄ ወደ አገራቀፍ አጀንዳ ሊያቀየር  ይችላል ሲል የኢህአዴግ የፖለቲካ ደህነነት ክፍል ግምገማውን አቅርቧል። ብአዴን፣ የጎንደር ህዝብ አመፅ ...

Read More »

ፈይሳ ሌሊሳ በሪዮ ኦሎምፒክ ያሳየው የተቃውሞ ምልክት በአገር ውስጥና በውጪ አሁንም መነጋገሪያነቱ ቀጥሏል

ነሃሴ  ፲፯ ( አሥራ  ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በታላቁ የሪዮ ኦሎምፒክ የማራቶን ውድድር ላይ ሁለተኛ በመውጣት የብር ሜዳሊያ ተሸላሚ የሆነው አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ በመላው ዓለም ባሉ የመገናኛ ብዙሃን ከፍተኛውን የዜና ሽፋን አግኝቷል። የአትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ሕዝባዊ ወገንተኝነቱን ማሳየቱን ተከትሎ በተለይ በአገሩ ኢትዮጵያ ውስጥ የሕዝቡ መነጋገሪያ ዋና ጉዳይ ሆኗል። ገዥው ህወሃት/ኢህአዴግ በኢትዮጵያዊያን ላይ የሚያደርሰውን የጅምላ ግድያ፣ እስራትና ማፈናቀል ...

Read More »

የፈንታሌ ወረዳ ነዋሪዎች በድርቅ ክፉኛ ተጠቅተዋል

ነሃሴ  ፲፯ ( አሥራ  ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የቤት እንስሳትም እየሞቱ ነው በምስራቅ ሸዋ ዞን የፈንታሌ ወረዳ ነዋሪዎች በአካባቢያቸው ባጋጠማቸው ድርቅ ሳቢያ ለከፍተኛ ስቃይ መዳረጋቸውን አስታወቁ። በፈንታሌ ሃሮ ሁባ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አርሶ አደር አቶ ቦራ ሮቡ ኢቱ ሁኔታውን ሲያስረዱ ”በድርቅ በተጠቃው ቀበሌ ውስጥ ነዋሪ የሆንነው ሁሉ ልጆቻችንን መመገብ አለመቻላችን ያናድደናል። የከብቶቻችን ሁኔታው አሳሳቢ ነው። የቤት እንስሳቶች ...

Read More »

በደባርቅ ለሶስት ቀን የሚቆይ ከቤት ያለመውጣት አድማ መጀመሩን ተከትሎ ግጭት ተቀሰቀሰ

ኢሳት (ነሃሴ 17 ፥ 2008) የደባርቅ ከተማ ነዋሪዎች ለሶስት ቀን የሚቆይ ከቤት ያለመውጣት አድማ ማክሰኞች መጀመራቸውን ተከትሎ የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ነዋሪዎች የወሰዱትን ዕርምጃ ለማስቆም ያደረጉት ጥረት ግጭትን ቀሰቀሰ። የስራ ማቆም አድማ ያካተተውን ተቃውሞ የተቀላቀሉ የደባርቅ ከተማ ሆስፒታል የህክምና ስራተኞች በቅጥር ግቢው ውስጥ በጸጥታ ሃይሎች ድብደባ እንደተፈጸመባቸው እማኞች ከዜና ክፍላችን ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ አስረድተዋል። በጎንደር ባህር ዳር ከተማ የተፈጸመ ግድያን ለማውገዝና ...

Read More »

በፌዴራልና ክልል ከተሞች መንግስታዊ አገልግሎቶች እየተስተጓጎሉ እንደሆነ ተነገረ

ኢሳት (ነሃሴ 17 ፥ 2008) በኢትዮጵያ በተለያዩ ቦታዎች ላይ በተቀጣጠለው ህዝባዊ እምቢተኝነት ምክንያት አዲስ አበባን ጨምሮ በፌዴራልና ክልሎች መደበኛ መንግስታዊ አገልግሎቶች በመስተጓጎላቸው የህዝቡን ምሬት እያባባሱ እንደሆነ ተገለጸ። አዲስ አበባን ጨምሮ በፌዴራልና የልል መንግስታዊ ተቋማት በመዘዋወር መረጃውን ያደረሱን የኢሳት ምንጮች፣ በመንግስታዊ ተቋማት ጉዳይ ለማስፈጸም የሚሄዱ ነዋሪዎች አገልግሎት ማግኘት የማይችሉበት ሁኔታ በመፈጠሩ በስርዓቱ ላይ መማረራቸውን ገልጸዋል። በተለይም በአንዳንድ የኦሮሚያ እና አማራ አካባቢዎች ...

Read More »