.የኢሳት አማርኛ ዜና

የኢትዮጵያ መንግስት ለደቡብ ሱዳን የተለያዩ ከባድ የጦር መሳሪያዎችን በሽያጭ በማቅረብ ላይ ነው ተባለ

ኢሳት (ኅዳር 22 ፥ 2009) የኢትዮጵያ መንግስት ለጎረቤት ደቡብ ሱዳን የተለያዩ ከባድ የጦር መሳሪያዎችን በሽያጭ በማቅረብ ላይ መሆኑን የሃገሪቱ አንድ የመገናኛ ብዙሃን ተቋም በብቸኝነት አግንቼዋለሁ ያለውን ሚስጢራዊ መረጃ ዋቢ በማድረግ አጋለጠ። መቀመጫውን በአዲስ አበባ ባደረገው የደቡብ ሱዳን ኤምባሲ ምክትል ወታደራዊ ተወካይ የሆኑት ሌተናል ኮሎኔል ሰለሞን ቶር ካንግ በሃገራቸው የመከላከያ ሚኒስትር አዛዥ ፓል ዋሎንግ አዋንግ የጦር መሳሪያዎቹን ወደ ጁባ እንዲጓጓዙ የ55ሺ ...

Read More »

ባለፉት 10 ወራት ብቻ ወደ 90ሺ የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን በስደት የመን መግባታቸውን ተመድ ገለጸ

ኢሳት (ኅዳር 22 ፥ 2009) ባለፉት 10 ወራቶች ብቻ ወደ 90ሺ የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን በስደት የመን መግባታቸውን የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኮሚሽን አስታወቀ። ጦርነት ዕልባት ወዳላገኘባት የመን የሚሰደዱ ኢትዮጵያውያን ስጋት እንዳደረሰባት የገለጸው ድርጅቱ ባለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ከ70ሺ የሚበልጡ ኢትዮጵያውያን ወደ ሃገሪቱ ገብተው እንደነበር አውስቷል። በየመን ያለው የዕርስ በዕርስ ጦርነት ባላገኘበት ወቅት በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በመሰደድ ላይ መሆናቸውን የገለጸው ድርጅቱ ባለፉት 10 ...

Read More »

ወደ አፍሪካ ህብረት አባልነት ለመመለስ ያቀረብኩት ጥያቄ በኮሚሽኑ ሊቀመንበር ተጓቷል ስትል ሞሮኮ ክስ አቀረበች

ኢሳት (ኅዳር 22 ፥ 2009) ሞሮኮ ተሰናባቿ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ንኮሳዛና ድላሚኒ ዙማ ሃገሪቱ ዳግም ወደ አባልነት ለመመለስ የያዘችውን ሂደት አጓተዋል ስትል ይፋዊ ቅሬታን አቀረበች። የቀድሞ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት አባል ሞሮኮ ሃገሪቱ ግዛቴ ናት ለምትላትው የሰሃራዊ ሪፐብሊክ ዕውቅና መሰጠቱን ተከትሎ ከ32 አመት በኋላ ከአህጉራዊ ድርጅት አባልነት እራሷን ማግለሏ ይታወሳል። ይሁንና የሞሮኮ ባለስልጣናት በሰሃራዊ ሪፐብሊክ ያላቸውን አቋም ሳይለወጡ ዳግም ወደ ...

Read More »

የዶክተር መረራ ጉዲና መታሰር አለማቀፍ ትኩረት እያገኘ ነው

ኅዳር ፳፪ (ሃያ ሁለት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበርና የመድረክ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት ዶ/ር መረራ ጉዲና በአውሮፓ ሕብረት ፓርላማ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ በተጋባዥነት  እንግድነት ንግግር አድርገው ወደ አገራቸው ሲመለሱ በህወሃት ኢህአዴግ ኮማንድ ፖስት በቁጥጥር ስር ውለዋል። የዶ/ር መረራ ጉዲናን መታሰር አስመልክቶ አምነስቲ ኢንተርናሽናል መግለጫ አውጥቷል። የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የምስራቅ አፍሪካ እና ታላላቅ ሃይቆች ምክትል ዳሬክተር ...

Read More »

በፌደራል ፖሊስ ዋና መስሪያ ቤት ቦንብ ተገኝቷል በሚል ሰበብ በርካታ ፖሊሶች ታሰሩ

ኅዳር ፳፪ (ሃያ ሁለት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከሶስት ቀናት በፊት ሜክሲኮ አደባባይ በሚገኘው በፌደራል ፖሊስ ዋናው ጽ/ቤት ወንጀል ምርመራ ክፍል ውስጥ ቦንብ ተገኝቷል በሚል ሰበብ በርካታ የኦሮሞና አማራ ተወላጅ ፖሊሶች ታሰረዋል። ምንጮች እንደገለጹት ቦንቡ ሆን ተብሎ ፖሊሶችን ለማጥመድ ተብሎ በህወሃት የፌደራል ፖሊስ አባላትና የደህንነት ሰዎች የተቀነባባረ ነው። በወንጀል ምርምራ ክፍል ውስጥ የጦር መሳሪያ እንደማይገባ የሚገልጹት ምንጮች፣ ድርጊቱ አገዛዙን ...

Read More »

በፍኖተሰላም በህገወጥ መንገድ የተገደሉ እስረኞችን ቀብር ያጋለጡ አባት ታሰሩ

ኅዳር ፳፪ (ሃያ ሁለት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በምዕራብ ጎጃም ዞን በፍኖሰላም ከተማ ተፈጥሮ የነበረውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ ከታሰሩት መካከል የ2 እስረኞች አስከሬን በድብቅ በሌሊት በቁስቋም ቤተክርስቲያን ሲቀበር የተመለከቱት ሊቀ ጳጳስ መካነ ሰላም፣ ድርጊቱን በመቃወማቸውና ድርጊቱንም ለህዝብ በመንገራቸው መታሰራቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ሊቀ ጳጳሱ ለቁስቋም ቤተክርስቲያን ንግስ ከደብረሊባኖስ ገዳም ወደ ፍኖተሰላም መሄዳቸውን የገለጹት ምንጮች፣  በቅዳሴ ሰአት ፖሊሶች ሁለት ...

Read More »

በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የምስራቅ አፍሪካ ስደተኞች በባሕር ወደ የመን እየፈለሱ ነው

ኅዳር ፳፪ (ሃያ ሁለት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የምስራቅ አፍሪካ አገራት ስደተኞች ሕይወታቸውን ለአደጋ አጋልጠው የተሻለ ኑሮ ፍለጋ በእርስበርስ ጦርነት ወደምትታመሰው የመን በብዛት እየገቡ  ነው። አስተማማኝ ባልሆኑ ጀልባዎች ተጭነው የመን የገቡ ኢትዮጵያዊያን እና ሶማሊያዊያን ስደተኞች በያዝነው ዓመት ብቻ ከመቶ ሽህ መብለጡን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አሳውቋል። እስካሁን ድረስ ቁጥራቸው ከ90 ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊያን እና ከ17 ሽህ በላይ ሶማሊያዊያን ዜጎች ከሞት ...

Read More »

ዶ/ር መረራ ጉዲና ከአውሮፓ አዲስ አበባ ሲገቡ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ታወቀ

ኢሳት (ህዳር 21 ፥ 2009) የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ ፕሬዚደንት ዶ/ር መረራ ጉዲና ከአውሮፓ አዲስ አበባ ሲገቡ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ታወቀ። የአይን ምስክሮች እንደገለጹት ዶ/ር መረራ ጉዲና በቁጥጥር ስር የዋሉት በምን እንደሆነ የታወቀ ነገር ባይኖርም፣ የህወሃት መገናኛ ብዙሃን ዶር መረራ እንዲታሰሩ ሰሞኑን በቅስቀሳ ላይ እንደነበሩ ታውቋል። በአውሮፓ ህብረት ግብዣ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ይዞታ ላይ ምስክርነት ለመስጠት ከፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋና ከአትሌት ፈይሳ ...

Read More »

ጥንታዊው የገዳ ስርዓት በዩኔስኮ ቅርስነት ተመዘገበ

ኅዳር ፳፩ (ሃያ አንድ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት የሳይንስ እና የባህል ተቋም ዩኔስኮ በመዲናችን አዲስ አበባ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኤኮኖሚክስ አዳራሽ ባደረገው 11ኛው መደበኛ ስብሰባው ላይ ጥንታዊውን የገዳ ስርዓትን በዓለም በማይዳሰሱ ቅርስነት መዘግቦታል። የገዳ ስርዓት በኢትዮጵያ የኦሮሞ ብሔረሰብ አባላት ዘንድ ባሕላዊ አስተዳደራዊ ስርዓት ሆኖ  ለዘመናት እውቀትን ከትውልድ ወደ ትውልድ በማሸጋገር ያገለገለ ጥንታዊ አስተዳደራዊ መዋቅር መሆኑ ...

Read More »

በህወሃት/ ኢህአዴግ ኩባንያዎች ምርቶች ላይ የተጀመረው ማዕቀብ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

ኅዳር ፳፩ (ሃያ አንድ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ህወሃት/ ኢህአዴግ በሃገሪቱ ዜጎች ላይ በሚያካሂደው ግድያና ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ረገጣ ምክንያት የፓርቲውን ምርቶች አለመጠቀምና በሃብቶቹም ላለመገልገል የወሰነው የአማራ ክልል ነዋሪ ህዝብ፣ ይህን አቋሙን አጠናክሮ በመቀጠሉ በፓርቲው የግል ኢኮኖሚ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እያደረሰ ነው። በአማራ ክልል ዋና ዋና የንግድ መነኻሪያ ከተሞች ህብረተሰቡ የህወሃት/ ኢህአዴግ ኩባንያዎች ምርቶች የሆኑትን ዳሽን ቢራ፣ራያ ቢራ ፣መሰቦ ...

Read More »