(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 8/2011) ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች ችግር እንዳለባቸው በመግለጽ የተለያዩ የአሜሪካን አየር መንገዶች ውስጥ የሚሰሩ አብራሪዎች ስጋታቸውን የገለጹበት የድምጽ ቅጂ ይፋ ሆነ። በሌላ በኩል የትራምፕ አስተዳደር የአቪዬሽን ባለስልጣናት ችግሩ የቦይንግ ሳይሆን የአብራሪዎቹ በቂ ስልጠና አለማግኘት ነው የሚል መከራከሪያ ይዘው መምጣታቸው ውዝግብን ፈጥሯል። የቦይንግ ኩባንያን ስም ለመከላከል ጥፋትን መደበቅ አይገባም የሚል ተቃውሞ በአሜሪካን ፖለቲከኞች እየተነሳ ነው። ጉዳዩ ሁለቱን የአሜሪካ ተቀናቃኝ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
አቶ ጌታቸው አሰፋ በድጋሚ መጥሪያ እንዲሰጣቸው ትዕዛዝ ተላለፈ
(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 8/2011) ለቀድሞ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት መስሪያ ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው አሰፋ መጥሪያ እንዲሰጣቸው ፍርድ ቤት በድጋሚ ትዕዛዝ ሰጠ። ለዛሬ እንዲቀርቡ የተላለፈው የመጀመሪያው ትዕዛዝ ተፈጻሚ ያልሆነው መጥሪያው ከፍርድ ቤት ወጪ ሳይደረግ በመቅረቱ መሆኑን በዛሬው ችሎት ላይ ተገልጿል። የዋስትና መብት ጥያቄ ያቀረቡ ተከሳሾች በፍርድ ቤቱ ውድቅ ተደርጎባቸዋል። የአቶ ጌታቸው አሰፋን መጥሪያ በተመለከተ የተዛባ ዜና አሰራጭተዋል በተባሉ የሚዲያ ተቋማት ላይም ...
Read More »ተለማማጅ ሀኪሞችና የድህረ ምረቃ ተማሪዎች ዛቻና ማስፈራራት እየተደረገብን ነው አሉ
(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 8/2011)ከትላንት ጀምሮ ስራ ያቆሙ የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ተለማማጅ ሀኪሞችና የድህረ ምረቃ ተማሪዎች በአስተዳደር በኩል ዛቻና ማስፈራራት እየተደረገብን ነው ሲሉ ገለጹ። ጥያቄአችንን የጥቅም ብቻ በማስመሰል የሚዲያ ዘመቻ እንዲከፈትብን ተደርጓል ሲሉ ዛሬ መግለጫ ሰተዋል። በተቃውሞአቸውም እንደሚቀጥሉ ነው ያስታወቁት። በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅና የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ዳዊት ወንድማገኝ የህክምና ባለሙያዎቹን ክስ አስተባብለዋል። ከነገ ጀምሮ በስራ ገበታቸው ...
Read More »የህዝብ ተወካዮች የሁለት ኮሚሽኖች አመራሮችን ሹመት አጸደቀ
(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 8/2011)የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሁለት ኮሚሽኖችን አመራሮች ሹመት አጸደቀ። በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አቅራቢነት ለአመራሮቻቸው ሹመት የጸደቀላቸው ኮሚሽኖች የእርቅና ሰላም ኮሚሽንና የአስተዳደር ወሰንና ማንነት ኮሚሽን ናቸው። ካርዲናል ብርሃነየሱስና ወ/ሮ የትነበርሽ ንጉሴ የእርቅና ሰላም ኮሚሽን ኮሚሽነርና ምክትል ኮሚሽነር ሆነው ሲሾሙ፣ ዶ/ር ጣሰው ገብሬና ኡስታዝ አቡበክር አህመድ የአስተዳደር ወሰንና ማንነት ኮሚሽን ኮሚሽነርና ምክትል ሆናው መሾማቸውን የደረሰን መረጃ አምልክቷል። ሹመቶቹን የህዝባዊ ...
Read More »የሱዳን ወታደራዊ ምክር ቤትና ተቃዋሚዎች ስምምነት ላይ ደረሱ
(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 7/2011) የሱዳን ወታደራዊ ምክር ቤትና ተቃዋሚዎች የሶስት ዓመት የሽግግር ጊዜ ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተገለጸ። ከ30 ዓመታት የአልበሽር ዘመን በኋላ በወታደራዊ ምክር ቤት እየተመራች ሁለተኛ ወሯን የያዘችው ሱዳን ስልጣን በሲቪል አስተዳደር ስር እንዲሆን ከሃገር ውስጥና ከዓለም ዓቀፉ ማህብረሰብ ግፊት እየተደረገ ይገኛል። ሰሞኑን በካርቱም እየተካሄደ ባለውና ወታደራዊው ምክር ቤት ስልጣን እንዲያስረክብ በመጠየቅ ላይ ባለውና በወታደሮች መካከል በተፈጠረ ግጭት በትንሹ 10 ...
Read More »የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የህክምና ባለሙያዎች የስራ ማቆም አድማ መቱ
(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 7/2011) መንግስት ጥያቄአችንን ለመመለስ ዝግጁ አይደለም በሚል የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የህክምና ባለሙያዎች ከዛሬ የጀመረ የስራ ማቆም አድማ መምታታቸው ተገለጸ። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅና ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ዋና ዳይሬክተር አድማውን ህገወጥ ሲሉ ገልጸውታል። የድህረ ምረቃ ተማሪዎቹ እስከነገ ወደ ስራቸው የማይመለሱ ከሆነ ርምጃ እንደሚወሰድባቸው የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል አስተዳደር ውሳኔ ማስተላለፉ ታውቋል። የስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ድህረ ምረቃ ተማሪዎች ግን ጥያቄዎቻቸው ...
Read More »በአፋር አሳይታ አካባቢ መንገዶች ተዘግተው መዋላቸው ተገለጸ
(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 7/2011)በአፋር በነዋሪዎችና በመከላከያ ሰራዊት መካከል በተፈጠረ ግጭት የአሳይታ አካባቢ መንገዶች ተዘግተው መዋላቸው ተገለጸ። ግጭቱ የተፈጠረው በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የሚደርሱ ችግሮች ባልተፈቱበት ሁኔታ የመከላከያና የፌደራል ፖሊስ አባላት ለሌላ ዓላማ እንቅስቃሴ ማድረጋቸውን ተከትሎ ነው። የኢሳት ምንጮች ባደረሱን መረጃ ላይ እንደተመለከተው የመከላከያ ሰራዊቱ ከኮንትሮባንድ ንግድ ጋር የተያያዘ ዘመቻ ተሰጥቶት በመጓዝ ላይ እያለ ከህዝብ ተቃውሞ ገጥሞታል። በአፋር የክልሉም ሆነ የፌደራል መንግስቱ የህዝብን ...
Read More »በድሬደዋ ዩኒቨርስቲ ብሔር ተኮር የሆነ ጥቃት እየተፈጸመ ነው
(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 7/2011) በድሬደዋ ዩኒቨርስቲ ብሔር ተኮር የሆነ ጥቃት እየተፈጸመ መሆኑ ተገለጸ። አንዳንድ የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች እንደሚሉት በየጊዜው ከሚደርስባቸው ጥቃት ጋር በተያያዘ 700 የሚሆኑ ተማሪዎች ዩኒቨርስቲውን ለቀው ከወጡ ሁለት ወራት ተቆጥሯል። በግቢው የቀሩት ተማሪዎች ላይም በተፈጸመው ጥቃት በርካታ ተማሪዎች መጎዳታቸውን ተናግረዋል። ጥቃቱን ያደርሳሉ የተባሉት አንዳንድ ተማሪዎች ዶርም ውስጥ ገጀራን የመሳሰሉ መሳሪያዎች ቢገኙም አስተዳደሩ ግን እነዚህ ተማሪዎች ላይ ርምጃ ሊወስድ አልፈለገም ብለዋል። ...
Read More »ግሎባል አሊያንስ ለጌዲዮ ተፈናቃዮች የ31ሚሊዮን ብር ድጋፍ ሰጠ
(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 7/2011) ዓለም ዓቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያውያን መብት ግሎባል አሊያንስ ለጌዲዮ ተፈናቃዮች የ31ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ። ግሎባል አሊያንስ ዛሬ በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል የድጋፍ ገንዘቡን ለወርልድ ቪዥን ማስረከቡን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። ከኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የተሰበሰበውን ገንዘብ ያስረከበው የዓለም ዓቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያውያን መብት ፕሬዝዳንት አርቲስትና አክቲቪስት ታማኝ በየነ ነው። የጌዲዮ ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው ለመመለስና ለማቋቋም ለተዘጋጀው ፕሮጀክት የሚውለውን ገንዘብ የወርልድ ...
Read More »ዶክተር አምባቸው መኮንን የአመራር ለውጥ እንደሚደረግ ገለጹ
(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 5/2011)ለኢትዮጵያም ሆነ ለአማራ ክልል ተጨባጭ ለውጥ ያመጣል ተብሎ የታመነበት የአመራር ለውጥ እንደሚደረግ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር አምባቸው መኮንን ገለጹ፡፡ የማይመጥኑ አመራሮችን በአዳዲስ የመተካት ሥራው ወደፊትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ዶክተር አምባቸው መግለጻቸውን የአማራ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ በደረ-ገጹ አስታወቋል፡፡ በአማራ ክልል በወረዳ፣ ዞንና ክልል ደረጃ እስከ 70 በመቶ የሚደርስ የአመራር ለውጥ ከዚህ ቀደም ተደርጎ ነበር የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር አምባቸው መኮንን ...
Read More »