መጋቢት ፲፬ (አሥራ አራት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት ያለምንም ተለዋጭ ቤትና ቦታ ከመኖሪያቸው እንዲፈናቀሉ የተደረጉት፣ በቀበሌ 14 አካባቢ የሚኖሩ ዜጎች ለከፍተኛ ችግር ተዳርገዋል። ትናንት ባሉዋን ሲደበድቡባት ጩኸት ያሰማች ነፍሰጡር ሴት ፣ በፖሊሶች በደረሰባት ድብደባ ከፉኛ ተጎድታ ሆስፒታል ገብታለች። አንድ ህጻንም በነበረው ግርግር ተረጋግጣ ህይወታ ማለፉ ታውቋል። አብዛኞቹ ወጣቶች ጫካ በመግባት ከድብደባ አምልጠዋል። ሁኔታው አስከፊ መሆኑን የሚናገሩት ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የገጠሩ ህዝብ የኢህአዴግን ጥሪ መቀበል አቁሟል ሲሉ የወረዳ አመራሮች ተናገሩ
መጋቢት ፲፫ (አሥራ ሦስት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢህአዴግ በከተማው ህዝብ ሳይሆን በአርሶ አደሩ ድጋፍ እንደሚተማመን በተደጋጋሚ ይገ ልጸል። ምንም እንኳ አሁንም ከ6 ሚሊዮን ያላነሰ አርሶአደር በረሃብ መጠቃቱ እንዲሁም ከ7 ሚሊዮን ያላነሰ አርሶአደር በምግብ ለስራ መርሃ ግብር ታቅፎ በውጭ እርዳታ እየኖረ ቢሆንም፣ ኢህአዴግ የግብርና ምርቱ በየጊዜው እየጨመረ መምጣቱን ይናገራል። አርሶአደሩም መሰረታዊ የሚባሉት የምግብ፣ የጤና፣ የትምህርት ፍላጎቱ እየተሟሉለት መሆኑን ግንባሩ ...
Read More »ህዝብ ባደረሰው ጫና _የወረዳ 10 አስተዳደር ያወጣውን ማስታወቂያ ካደ
መጋቢት ፲፫ (አሥራ ሦስት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቂርቆስ ክፍለከተማ ወረዳ 10 ከቤት መፈናቀል ጋር በተያያዘ ወረዳው ያወጣውን ማስታወቂያ ለመገንጠልና በዱሪዬዎች የተለጠፈ ነው በሚል ሰበብ በመካድ ለማስተባበል መሞከሩን ነዋሪዎች ተናገሩ። በአካባቢው የሚገኙ ነዋሪዎች እስከ ግንቦት 30 ቀን 2009 ዓም ቤታቸውን ለቀው እንዲወጡ በስብሰባ ላይ የተነገራቸው መሆኑን ኢሳት ዘግቦ የነበረ ሲሆን፣ መጋቢት12 ደግሞ “መንግስት መሬቱን ለቻይናና ቱርክ ባለሃብቶች ማስረከብ ስላለበት ...
Read More »በአሜሪካ በተዘጋጀ የአፍሪካ የንግድ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ የተጋበዙ አፍሪካውያን የመግቢያ ቪዛ ተከለከሉ
መጋቢት 13: 2009) ኢትዮጵያን ጨምሮ ከተለያዩ የአፍሪካ ሃገራት በአሜሪካ በተዘጋጀ የአፍሪካ የንግድ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ የተጋበዙ እንግዶች የአሜሪካ የመግቢያ ቪዛ መከልከላቸውን የጉባዔው አዘጋጆች አስታወቁ። በካሊፎርኒያ ግዛት በሚገኘ የደቡብ ካለፎርኒያ ዩኒቨርስቲ የተዘጋጀው የንግድ ጉባዔ በአፍሪካ ጉዳይ ላይ ለመምከር ቢዘጋጅም አንድም የአፍሪካ ተወካይ በቪዛ ችግር ሊገኝ አለመቻሉን ዘጋርዲያን ጋዜጣ አዘጋጆቹን ዋቢ በማድረግ ዘግቧል። ለሶስት ቀናት የተዘጋጀው የንግድ ጉባዔ የአፍሪካና የአሜሪካንን የቢዝነስ ትስስር ...
Read More »በአዲስ አበባ የውሃ እጥረት ተባብሶ መቀጠሉ ተነገረ
መጋቢት 13: 2009) በአዲስ አባባ በርካታ አካባቢዎች የውሃ እጥረት ችግር ተባብሶ መቀጠሉን ነዋሪዎች አስታወቁ። የከተማዋ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ለከተማዋ የውሃ አቅርቦት የሚያገለግሉ ጉድጓዶች በመድረቃቸው ምክንያት የውሃ እጥረቱ መከሰቱን በቅርቡ መግለፁ ይታወሳል። ባለስልጣኑ የውሃ እጥረቱ ጊዜያዊ መፍትሄ እንዲያገኝ ተደርጓል ሲል ከቀናት በፊት መግለጫን ቢሰጥም ነዋሪዎችና የተቋማት ባለቤቶች ችግሩ ዕልባት አለማግኘቱን ይገልጻሉ። ለአመታት የቆየው የመዲናይቱ የውሃ እንዲሁም የመብራት እጥረት በዕለት ከእለት ኑሯቸው ...
Read More »በአዲስ አበባ የነዳጅ እጥረት ተከሰተ
መጋቢት 13: 2009) በአዲስ አበባ ለሁለተኛ ሳምንት ጊዜ የቀጠለው የነዳጅ እጥረት በነዋሪዎች ላይ ማህበራዊ ተፅዕኖ ማሳደሩን የከተማዋ ነዋሪዎች ገልጹ። በተለይ የህዝብ ትራንስፖርት ተጠቅመው የተለያዩ ጉዳዮች የሚያከናውኑ ነዋሪዎች የነዳጅ እጥረቱ ለሁለተኛ ሳምንት በመቀጠሉ ምክንያት ለዘርፉ ብዙ ችግር መዳረጋቸውን አስታወቀዋል። በመዲናይቱ የሚገኙ የተሽከርካሪ ባለሃብቶች በበኩላቸው ነዳጅ ለማግኘት በነዳጅ ማደያ አካባቢዎች ለማደር መገደዳቸውን ጭምር ለመገናኛ ብዙሃን አስረድተዋል። ለመንግስት ስራና ለግል ጉዳዩች ለመንቀሳቀስ የህዝብ ...
Read More »ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ መንገደኞች የያዙትን ገንዘብና ጌጣጌጥ ጭምር እንዲያስመዘግቡ አዲስ መመሪያ ተግባራዊ ሆነ
መጋቢት 13: 2009) የውጭ ምንዛሪ ዝውውርን ለመቆጣጠር ሲባል ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ መንገደኞች የያዙትን ገንዘብና ጌጣጌጥ ጭምር እንዲያስመዘግቡ አዲስ መመሪያ ተግባራዊ ሆነ። ከዚህ በፊት ከተለያዩ ሃገራት የአየር ትራንስፖርት ተጠቅመው ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ መንገደኞች 24 ሰዓት እስካልሞላቸው ድረስ የያዙትን ገንዘብም ሆነ ጌጣጌጥ ማስመዝገብ እንደማይጠበቅባቸው ታውቋል። ይሁንና በአዲሱ መመሪያ መሰረት ማንኛውም ተጓዥ ወደ ኢትዮጵያ እንደገባ በእጁ የሚገኙ ገንዘቦችን እንዲሁም ጌጣጌጦችን እንዲያስመዘግብ መደረጉን የኢትዮጵያ ...
Read More »በሶማሌ ክልል የተበከለ ውሃን የተጠቀሙ ነዋሪዎች ለሞትና ህመም ተዳረጉ
መጋቢት 13: 2009) በኢትዮጵያ የሶማሌ ክልል አፍዴር ዞን ስር በምትገኘው የሃርገሌ ከተማ አካባቢ ከሚገኝ ግድብ የተበከለ ውሃን ከተጠቀሙ ነዋሪዎች መካከል በትንሹ ስድስቱ ሞተው በርካታ ለህመም መዳረጋቸውን አንድ ግብረ ሰናይ ድርጅት አስታወቀ። በክልሉ በመባባስ ላይ ያለው የድርቅ አደጋ ጋር በተያያዘ ሰዎች በመሞት ላይ መሆናቸውን የገለጸው የካቶሊክ ዕርዳታ ድርጅት፣ ህይወታቸውን ለመታደግ ሲሉ ከግድቡ የተገኘን ውሃ የሚጠቀሙ ሰዎች ለሞትና ለበሽታ መዳረጋቸውን በጉዳዩ ዙሪያ ...
Read More »አርበኞች ግንቦት 7 በተለያዩ አካባቢዎች የጀመረው የሽምቅ ጥቃት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለጸ
መጋቢት 13: 2009) አርበኞች ግንቦት ሰባት ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ሰሞኑን በሰሜንና ደቡብ ጎንደር በሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎች የጀመረው የሽምቅ ጥቃት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለጸ። ከመጋቢት ወር መጀመሪያ ጀምሮ የንቅናቄው ሰራዊት አባላት በማክሰኝት፣ በደጎማ፣ በደንቀዝን ፣ በበለሳ፣ በአዲስ ወረዳ፣ በደምቢያ እንዲሁም በጯሂት በህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ ስርዓት ተቋማት ላይ የተቀናጀ የሽምቅ ጥቃት ማድረሳቸውን ባወጣው መግለጫ አመልክቷል። በሰሜንና ደቡብ ጎንደር በተካሄዱ የንቅናቄው የሽምቅ ጥቃት መንግስት ቀይ ...
Read More »ትግላችን ከሌሎች ብሄሮች ጋር በመተባበር ኢትዮጵያን ማዳን ነው ሲሉ የቤኒሻንጉል ህዝብ ንቅናቄ የፖለቲካ ሃላፊ ገለጹ
ኢሳት (መጋቢት 12: 2009) የቤኒሻንጉል ህዝብ ንቅናቄ (ቤህኒን) የሚካሄደው የነጻነት ትግል ሃገራዊና ከሌሎች ብሄሮች ጋር በመተባበር ኢትዮጵያን የማዳን መሆኑን የድርጅቱ የፖለቲካ ሃላፊ ገለጹ። የቤህኒን የፖለቲካ ሃላፊ አልሃጂ አፈንዲ ጠሓ በተለይ ለኢሳት እንደገለጹት በህወሃት/ኢሀዴግ የሚመራውን አገዛዝ ለማስወገድ የሚካሄደው የነጻነት ትግል ተጠናክሮ ቀጥሏል። ድርጁቱ በሃገር ውስጥ የሚካሄደው የትጥቅ ትግል በህወሃት/ኢህአዴግ ላይ ያነጣጠረ እንጂ በመሰረተ ልማቶች ላይ ጉዳት የማድረስ አላማ እንደሌለውም ገልጸዋል። በቅርቡ ...
Read More »