.የኢሳት አማርኛ ዜና

የድርቅ አደጋ እየተባባሰ በመሆኑ የተረጂዎች ቁጥር እያሻቀበ ነው ተባለ

ኢሳት (መጋቢት 20 ፥ 2009) በኢትዮጵያ አራት ክልሎች ተከስቶ ያለው የድርቅ አደጋ በመባባስ ላይ መሆኑን ተከትሎ የተረጂዎች ቁጥር ማሻቀቡን የብሄራዊ አደጋ ኮሚሽን ረቡዕ ገለጠ። የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና መንግስት በቅርቡ ለአስቸኳይ የምግብ ዕርዳታ የተጋለጡ ሰዎች ቁጥር 5.6 ሚሊዮን እንደሆነ መግለጻቸው ይታወሳል። ይሁንንና የድርቁ አደጋ በመባባስ ላይ በመሆኑ ምክንያት ቁጥሩ እየጨመረ በመሄድ ላይ መሆኑን ኮሚሽኑ ድርቁ እያደረሰ ያለውን ጉዳት አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ ...

Read More »

የኬንያ ፓርላማ ሴቶች ቁጥር ሁለት ሶስተኛ እንዲሆን የሚያደርግ መመሪያ ተግባራዊ ካላደረገ ፓርላማው ሊፈርስ (ሊዘጋ) እንደሚችል ተገለጸ

ኢሳት (መጋቢት 20 ፥ 2009) የኬንያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሃገሪቱ ፓርላማ በቀጣዮቹ ሁለት ወራቶች የሴቶች ቁጥር ሁለት ሶስተኛ እንዲሆን የሚያደርግ መመሪያ ተግባራዊ ካላደረገ ፓርላማው ሊፈርስ (ሊዘጋ) እንደሚችል ረቡዕ አሳሰበ። በሃገሪቱ ህግ መሰረት ከሁለት ሶስተኛ በላይ የሆኑ የህዝብ ተመራጮች ተመሳሳይ ጾታ እንዳይኖራቸው ቢደነግግም፣ ህጉ በኬንያ ፓርላማና በሌሎች መንግስታዊ ተቋማት ዘንድ ተፈጻሚ ሳይሆን መቅረቱን ዴይሊ ኔሽን ጋዜጣ ዘግቧል። ፓርላማው የሴቶች ቁጥር በህጉ ...

Read More »

ሼክ አላሙዲን የህዝብ የልማት ድርጅቶችን የገዙበትን ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ እዳ አልከፈሉም ተባለ

መጋቢት ፳ (ሃያ)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የመንግስትን ድርጅቶችን ወደ ግል በማዞር ሒደት አገዛዙ ለግል ባለሃብቶች ከሸጣቸው የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ውስጥ ከሶስት ቢሊየን ብር በላይ እንዳልተከፈለና አብዛኛውን እዳ የተሸከሙት ባለሀብቱ ሼክ ሙሃመድ ሁሴን አላሙዲን መሆናቸው ተገልጿል። መንግሥታዊው አዲስዘመን ጋዜጣ በረቡዕ መጋቢት 20 ቀን ዕትሙ እንደዘገበው ከመንግሥት ወደግል ከተዛወሩ 29 ድርጅቶች በጠቅላላው ከሶስት ቢሊየን ብር በላይ ክፍያ ያልተፈጸመበት ሲሆን፣ ከዚህ ...

Read More »

“የአባይ ግድብን በራስ አቅም እንገነባለን” የሚለው ቅስቀሳ ጥያቄ ውስጥ ገባ

መጋቢት ፳ (ሃያ)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፉት ስድስት ዓመታት ለግድቡ የቦንድ መዋጮ 12 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ቃል ተገብቶ የነበረ ቢሆንም፣ የቦንድ አሰባሳቢ ግብረሃይሉ ባስታወቀው መሰረት መሰብሰብ የተቻለው 9 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ብቻ ነው፡፡ ከዚህ ገንዘብ ውስጥ ከፍተኛውን ድርሻ እንዲያዋጣ የተገደደውም የመንግሥት ሠራተኛው ነው። ከእጅ ወደ አፍ በሆነ ወርሃዊ ገቢ የሚተዳደሩት የመንግሥት ሠራተኞች በየመ/ቤታቸው ሳይወዱ በግድ ባለፉት ...

Read More »

የፊላንዱ ቴንፐር ዩንቨርሲቲ ለጠቅላይ ሚንስትር ኃ/ማሪያም ደሳለኝ ሊሰጥ ያሰበውን የክብር ዶክትሬት እንደማይሰጥ አስታወቀ

መጋቢት ፳ (ሃያ)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዩንቨርሲቲው በድረገጹ ላይ ለጥፎት የነበረውን የጠቅላይ ሚንስትሩን ሽልማት ዜናም አንስቶታል። የዩንቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ከአቶ ኃማሪያም ደሳለኝ ጋር የሚያገናኝ ምንም ዓይነት ቀጠሮ አለመያዙንም ገልጸዋል። ዩንቨርሲቲው ለቀድሞው የቴንፐር ዩንቨርሲቲ ተማሪ አቶ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ የክብር ዶክትሬት መስጠት ማሰቡን ተከትሎ ኢትዮጵያዊያን ጋዜጠኞች ፣ በፊንላንድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አባላት እንዲሁም በመላው አለም የሚገኙ ታዋቂ ሰዎች ደብዳቤ በመጻፍ፣ ስልክ በመደወልና ...

Read More »

የአስቴር ስዩም እና የንግስት ይርጋ የፍርድ ቤት ሂደት ከሚገባው በላይ እየተጓተተ ነው

መጋቢት ፳ (ሃያ)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ያለምንም ማስረጃ በሽብር ወንጀል ተከሰው በቃሊቲ ማጎሪያ ቤት የሚገኙት፥ አስቴር ስዩም እና ንግስት ይርጋ፥ ትናንት መጋቢት 19 ቀን 2009 ዓ.ም በልደታ ፍርድ ቤት ቢቀርቡም አሁንም ሌላ ቀጠሮ ተሰጥቷቸው ወደ እስር ቤት ተመልሰዋል። አስቴር ስዩም እና ንግስት ይርጋ የቀረቡት አቶ ሄኖክ ከተባሉ የሕግ ጠበቃ ጋር ሲሆን፥ በንግስት ይርጋ የክስ መዝገብ አጠቃላይ የቀረቡት ስድስት ...

Read More »

በኢትዮጵያ የሚገኙ ቤተእስራዔላውያን ወደ እስራዔል ለማጓጓዝ የተገባው ቃል በድጋሚ መዘግየት አጋጠመው

ኢሳት (መጋቢት 19 ፥ 2009) በጎንደርና በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ ቤተ እስራዔላውያን ወደ እስራዔል ለማጓጓዝ የተገባው ቃል በድጋሚ መዘግየት እንዳጋጠመው ተገለጸ። ባለፈው አመት በኢትዮጵያ ጉብኝትን ያደረጉት የእስራዔሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቤንጃሚን ኔታኒያሁ ወደ 9ሺ አካባቢ ከሚጠጉት ቤተ እስራዔላዊያን መካከል የ1ሺ 3 መቶዎቹ ጉዞ በተያዘው አመት እንደሚጠናቀቅ የተቀሩትም በአምስት አመታት ውስጥ ተጠናቀው ወደ እስራዔል እንደሚገቡ ቃል መግባታቸው ይታወሳል። የቤተ-እስራዔላውያኑ ጉዞ ...

Read More »

የውጭ ንግድ ባለፉት ስድስት ወራት ከታቀደው ገቢ 1 ቢሊዮን ብር ጉድለት አስመዘገበ

ኢሳት (መጋቢት 19 ፥ 2009) የኢትዮጵያ ውጭ ንግድ ባለፉት ስድስት ወራቶች ብቻ ሊያስገኝ ከታቀደው ገቢ ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ ጉድለት አስመዘገበ። ሃገሪቱ በተያዘው በጀት አመት የመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት ከውጭ ንግድ ዘርፍ 4.2 ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት እቅድ የነበራት ቢሆንም፣ ሊገኝ የቻለው ግን 1.4 ቢሊዮን ዶላር አካባቢ መሆኑን የንግድ ሚኒስቴር አስታውቋል። ባለፉት ስድስት ወራቶች የውጭ ንግድ ገቢው ከታቀደው በታች  ማስመዝገቡ በኢኮኖሚ እንቅስቃሴውና ...

Read More »

በአራት ክልሎች በድርቅ የተጠቁት ህጻናትና በእርግዝና ላይ ያሉ ሴቶች ልዩ የምግብ እንክብካቤን የሚሹ መሆኑን ፋኦ (FAO) አስታወቀ

ኢሳት (መጋቢት 19 ፥ 2009) የአለም ምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ አራት ክልሎች በመባባስ ላይ ባለው አዲስ የድርቅ አደጋ በ192 ወረዳዎች በአንደኛ ደረጃ በመመደብ አፋጣኝ የምግብ አቅርቦት እንደሚፈልጉ አስታወቀ። በእነዚሁ ክልሎች የድርቁ አደጋ መልኩን እየቀየረ በመሄድ ላይ መሆኑን የገለጸው ድርጅቱ በአራቱ ክልሎች ስር በሚገኙ በርካታ ዞኖች ዕድሚያቸው ከአምስት አመት በታች የሆነ 198 ሺ ህጻናትና 120ሺ በእርግዝና ላይ ያሉ ሴቶች ልዩ የምግብ እንክብካቤን ...

Read More »

በቅርቡ በጎንደር በሚከበረው የከተሞች ቀን በክልሉ ያለውን ድባብ እንዲቀይር ብዓዴን ሃላፊነት ተሰጠው

  ኢሳት (መጋቢት 19 ፥ 2009) በሚመጣው ሚያዚያ ወር በጎንደር የሚከበረው የከተሞች ቀን የክልሉን ገጽታም ሆነ በአጠቃላይ በሃገሪቱ ውስጥ ያለውን ድባብ እንዲቀይር ለብዓዴን ሃላፊነት ተሰጠው። ምክትል ጠ/ሚ/ ደመቀ መኮንን ሂደቱን በበላይነት እንዲያስተባብሩ መሾማቸውም ታውቋል። ዝግጅቱ እንደ መስቀልና ጥምቀት በዓላት የፈዘዘ እንዳይሆን ሁሉም የብዓዴን አባላት የክልሉ መንግስት በሙሉ አቅማቸው እንዲንቀሳቀሱም ከፌዴራል መንግስት መመሪያ መተላለፉን መረዳት ተችሏል። ከሚያዚያ 21 ቀን 2009 ጀመሮ ...

Read More »