.የኢሳት አማርኛ ዜና

በኢትዮጵያ በተከሰተው ረሃብ ሰብዓዊ ቀውስ ሊፈጠር ይችላል የሚል ስጋት እንዳለው ወርልድ ቪዥን ገለጸ

መጋቢት ፳፩ (ሃያ አንድ)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የበልግ ዝናብ ወቅቱን ጠብቆ አለመጣሉን ተከትሎ በተፈጠረ ከፍተኛ ድርቅ ምክንያት በምስራቅ እና ደቡብ ምስራቅ ኢትዮጵያ አካባቢዎች የሚኖሩ አርብቶ አደሮች ለከፋ ረሃብ መጋለጣቸውን ወርልድ ቪዥን አስታውቋል። የአየር ትንበያዎች በመጪዎቹ ወራቶች ካሁኑ በከፋ ሁኔታ የዝናብ እጥረቱ ተባባሶ እንደሚቀጥልና ከቀድሞው 45 በመቶ ከመቶ በታች የሆነ ዝናብ ሊዘንብ እንደሚችል ያመለክታሉ። ከምስራቅ እና ደቡብ ምስራቅ ኢትዮጵያ ...

Read More »

ረሃብና ጦርነትን የሸሹ በሽዎች የሚቆጠሩ ሶማሊያዊያን ዜጎች ወደ ኢትዮጵያ እየፈለሱ ነው።

መጋቢት ፳፩ (ሃያ አንድ)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ብዙ ኪሎሜትሮችን በእግር በመጓዝ ሕጻናትን የያዙ እናቶች፣ ነፍሰጡሮች እና አቅመ ደካማ ሶማሊያዊያን አገራቸውን እና መኖሪያ ቀያቸውን በመተው ኢትዮጵያ ውስጥ ወደሚገኘው ዳሎ አዶ መጠለያ ጣቢያ እየጎረፉ ነው። ሶማሊያውያን በርሃብ የተጎዱ ልጆቻቸውን ማጥባት የተሳናቸው ሲሆን፣ አገራቸውን ጥለው ወደ ኢትዮጵያ የተሰደዱት ረሃብ እና ጦርነትን ሸሽተው መሆኑን ተናግረዋል።

Read More »

በኢትዮጵያ የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በአራት ወር እንዲራዘም ተደረገ

ኢሳት (መጋቢት 21 ፥ 2009) በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ተቀስቅሶ የነበረው ህዝባዊ ተቃውሞ በቁጥጥር ስር ሊውል ባለመቻሉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ለተጨማሪ አራት ወራት እንዲራዘም ተወሰነ። የአዋጁን አፈጻጸም ለመቆጣጠር የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት ሃሙስ ለፓርላማ ባቀረበው ሪፖርት ክልሎች በሚዋሰኑባቸው አካባቢዎች የሚነሱ ችግሮችን ለመጠቀም የሚፈልጉ እና ጸረ-ሰላም ሲል የገለጻቸው አካላት እየተንቀሳቀሱ ነው ሲል አስታውቋል። በበራሪ ወረቀቶች የተለያዩ ፅሁፎች አሁንም ድረስ በመበተን ላይ እንደሚገኙ ኮማንድ ...

Read More »

ከቆሼ አደጋ የተረፉ ነዋሪዎች ህጋዊ አይደላችሁም ተብለው ከጊዜያዊ መጠለያ እንዲወጡ መደረጋቸውን አስታወቁ

ኢሳት (መጋቢት 21 ፥ 2009) በቅርቡ በአዲስ አበባ ከተማ ቆሼ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በደረሰ አደጋ የተረፉና በጊዜያዊ መጠለያ እንዲቆዩ የተደረጉ ነዋሪዎች ህጋዊ ነዋሪዎች አይደላችሁም ተብለው ከመጠለያ እንዲወጡ መደረጋቸውን አስታወቁ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በበኩሉ በጊዜያዊ መጠለያ እንዲገቡ የተደርጉ ሰዎች በአደጋው ተጎጂ እንደነበሩና እንዳልነበሩ የመለየት ስራ እየተካሄደ መሆኑን ሃሙስ ገልጿል። ይሁንና በጊዜያዊ መጠለያው የሚገኙ በርካታ ሰዎች ከአደጋው ተርፈው በመጠለያ እንዲገቡ ቢደረግም ...

Read More »

የኢህአዴግ መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ያራዘመው ህዝባዊ ተቃውሞው ሊቀጣጠል ይችላል የሚል ስጋት ስላደረበት እንደሆነ ተገለጸ

ኢሳት (መጋቢት 21 ፥ 2009) መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲራዘም የወሰነው ህዝባዊ ተቃውሞ ሊቀጥል ይችላል የሚል ስጋት ስላደረበትና ተግባራዊ የተደረገ ማሻሻያ ባለመኖሩ እንደሆነ ዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ የተለያዩ አካላትን ዋቢ በማድረግ ሃሙስ ዘግቧል። የዩኒቨርስቲ መምህር የሆኑትና ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በፊትና በአዋጁ መውጣት ወቅት ለእስር ተዳርገው የነበራት አቶ ስዩም ተሾመ ህዝቡ ተቃውሞን የሚገልፅበት መንገድ ባለመኖሩ አዋጅ ከተነሳ ህዝባዊ ተቃውሞ ሊቀጥል እንደሚችል ከጋዜጣው ...

Read More »

አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ለኢትዮጵያውያን በሚሰጠው የቪዛ ቁጥር ላይ የተጣለ ገደብ አለኖሩን አስታወቀ

ኢሳት (መጋቢት 21 ፥ 2009) በኢትዮጵያ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ለኢትዮጵያውያን በሚሰጠው የቪዛ ቁጥር ላይ የተጣለ ገደብ አለኖሩን አስታወቀ። የአሜሪካው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ማሻሻያ አድርገው ያቀረቡትንና በፍርድ ቤት ዳግም ውድቅ የተደረገባቸውን የኢሚግሬሽን መመሪያ ተከትሎ በተለያዩ መንገዶች ለኢትዮጵያ በሚሰጥ የቪዛ ኮታ ላይ ቅነሳ እንደተደረገ ተደርጎ መረጃ በመሰራጨት ላይ መሆኑን ኤምባሲው ባወጣው መግለጫ አመልክቷል። ይኸው ኢትዮጵያን በተመለከተ እየተነገረ ያለውና በመሰራጨት ላይ የሚገኘው ...

Read More »

በሳውዲ በህገወጥ የሚኖሩ ሶስት ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች በ90 ቀናት ከአገር እንዲወጡ ተጠየቁ

ኢሳት (መጋቢት 21 ፥ 2009) የሳውዲ አረቢያ መንግስት ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው ከሶስት ሚሊዮን በላይ ሰዎች በቀጣዮቹ 90 ቀናቶች ውስጥ ከሃገሪቱ እንዲወጡ አሳሰበ። ይኸው የ90 ቀን ገደብ ረቡዕ የተጀመረው ሲሆን፣ ዕርምጃው በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን የሚመለከት እንደሆነ ተመልክቷል። መንግስት በበኩሉ የሳውዲ አረቢያ ውሳኔ የሚመለከታቸው በርካታ ኢትዮጵያውያን መኖራቸውን ገልጾ፣ ኢትዮጵያውያኑ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ከሃገሪቱ እንዲወጡ ጠይቋል። የሳውዲ አረቢያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የሃገር ...

Read More »

በኢትዮጵያ የሚታየው ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ትኩረት ካልተሰጣቸው አሁን እየታዩ ያሉ ችግሮች ሊፈቱ እንደማይችል ተገለጸ

ኢሳት (መጋቢት 20 ፥ 2009) ከኢትዮጵያ እየጨመረ የመጣን የስደተኞች ቁጥር ለመግታት በሃገሪቱ ያሉ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ትኩረት ሊሰጣቸው እንደሚገባ በግጭቶች ዙሪያ የሚሰራ አንድ አለም አቀፍ ተቋም አሳሰበ። ወደ አንድ መቶ ሚሊዮን አካባቢ የሚጠጋ ህዝብ ያላት ኢትዮጵያ ከጥቂት አመታት ወዲህ ጀምሮ ለአለም ስደተኞች ቁጥር መበራከት ምንጭ እየሆነች መምጣቷን አርምድ ኮንፍሊክትስ የተሰኘውና በአለም ባሉ ግጭቶች ዙሪያ የሚሰራው ተቋም የኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይን አስመልክቶ ...

Read More »

የገበያ ማዕከል ለመገንባት ከ10 አመት በፊት ከ580 ሚሊዮን ብር በላይ በዝግ ሂሳብ ያስቀመጡ ነጋዴዎች ጉዳዩ ሳይፈጸምላቸው በመቅረቱ ቅሬታ አቀረቡ

ኢሳት (መጋቢት 20 ፥ 2009) በአዲስ አበባ ከተማ የገበያ ማዕከላት ለመገንባት የሚያስችል መሬት እንደሚሰጣቸው ቃል ተገብቶላቸው ከ580 ሚሊዮን ብር በላይ በዝግ ሂሳብ ያስቀመጡ ከ10ሺ በላይ ነጋዴዎች ቃል የተገባልን ሳይፈጸም 10 አመታት አስቆጠረ ሲሉ ቅሬታን አቀረቡ። በአስሩም ክፍለ ከተሞች የገበያ ማዕከላት ለመገንባት በከተማው አስተዳደር ቃል ተገብቶላቸው እንደነበር የሚናገሩት ቅሬታ አቅራቢዎቹ በዝግ ሂሳብ ያስቀመጡት 583 ሚሊዮን ብር በባንክ ከገባ 10 አመት እንደሞላው ...

Read More »

አፍሪካ ህብረት ጽ/ቤት አካባቢ የሚኖሩ ዜጎች በሶስት ቀን ጊዜ መኖሪያ ቤታቸውን ልቀቁ ተባሉ

ኢሳት (መጋቢት 20 ፥ 2009) በአዲስ አበባ ከተማ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የአፍሪካ ህብረት አካባቢ የሚኖሩ ከአንድ ሺ በላይ ነዋሪዎች ያለምንም ቅድመ ዝግጅት በሶስት ቀን ውስጥ ልቀቁ ተብለናል ሲሉ ቅሬታን አቀረቡ። በክፍለ ከተማው ወረዳ 11 በተለምዶ ፈለገ ዮርዳኖስ ተብሎ በሚጠራ ስፍራ የአፍሪካንና ቻይና የጋራ አለም አቀፍ ዘርፈ ብዙ ተቋማትና ባለአምስት ኮከብ ሆቴሎችን ለመገንባት እቅድ መያዙ ታውቋል። ለዚሁ ግንባታ ሲባል 1ሺ 516 ...

Read More »