መጋቢት ፳፯ (ሃያ ሰባት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- እንደ ግንባሩ መግለጫ በምስራቅ ኢትዮጵያ ኦጋዴን አካባቢ በጥቂት ቀናት ውስጥ እየተዛመተ በመጣው የኮሌራ ተላላፊ በሽታ ምክንያት ከመቶ በላይ ዜጎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። በተለይ የዶሎ፣ ቆራሄ፣ ኖጎቦ፣ ጃራር እና አፍዴር ወረዳዎች ክፉኛ ተጠቅተዋል። ከኮሌራው ወረሽኝ በሽታው በተጨማሪ በቀጠናው እየተስፋፋ የመጣው መጠነ ሰፊ የድርቅ አደጋ በነዋሪዎቹ ላይ ከፍተኛ ሰባአዊ ቀውስ እያስከተለ ቢሆንም ዓለምአቀፉ ማህበረሰብ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በኢትዮጵያ በምግብ አለመመጣጠን ችግር የተነሳ በየዓመቱ ዕድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ 53 በመቶ ሕጻናት እንደሚሞቱ ተነገረ፡፡
መጋቢት ፳፯ (ሃያ ሰባት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- 23 በመቶ የሚደርሱ እናቶች የደም ማነስ ችግር እንዳለባቸውና ይህም ችግር በወሊድ ወቅት እስከሞት ለሚደርስ አደጋ እየዳረጋቸው መሆኑ ተሰምቷል፡፡ ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ በምግብ አለመጣጠን ሳቢያ ገና በእናታቸው ማህጸን እያሉ ጀምሮ በህጻናት ላይ የጤና ችግሮች ሊከሰት እንደሚችል ይናገራል፡፡ ከጤና ችግሮቹ መካከል የሕጻናት ሞት፣ በተደጋጋሚ በበሽታ መጠቃት እና ከታመሙ በሁዋላ በቶሎ ማገገም ...
Read More »ከየካቲት መጨረሻ አንስቶ እየተካሄደ ያለውና በርካታ ሀገሮችን ያካተተው የአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ከተጠበቀው በላይ በስኬት እየቀጠለ እንደሚገኝ ከየስፋራዎቹ የደረሱ ሪፖርቶች አመለከቱ።
መጋቢት ፳፯ (ሃያ ሰባት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በንቅናቄው ከፍተኛ አመራር በአቶ ኤፍሬም ማዴቦ የተመራው ይህ የገቢ ማሰባሰብ ፕሮግራም እስካሁን በሜልበርን ፣በኒውዝላንድ ፣በኦክላንድ በክራይስት ቸርች ፣ በዊሊንግተን፣ በአውስትራሊያ በፐርዝ፣ በብሪዝበን፣ በሜልቦርን ፣ በኮሪያ ሴኡል እና ብጃፓን ቶኪዮ በከፍተኛ ስኬትና ድምቀት ተከናወኗል። ከኤርትራ በርሃ በቀጥታ ወደ አውስትራልያ የመጡት የዕለቱ የክብር እንግዳ አቶ ኤፍሬም ማዴቦ ፕግራሞቹ በተዘጋጁባችወ አዳራሾች ሲገኙ ለስብሰባው የታደመው ...
Read More »በሶሪያ የተፈጸመውን የኬሚካል ጦር መሳርያ ጥቃት ተከትሎ የተመድ ጸጥታ ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ ጠራ
ኢሳት ( መጋቢት 27 ፥ 2009) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታ ምክር ቤት በሶሪያ መንግስት ተፈጽሟል የተባለን የኬሚካል ጦር መሳሪያ ጥቃትን ተከትሎ ረቡዕ አስቸኳይ ስብሰባ ጠራ። አሜሪካንን ጨምሮ የምዕራባውያን ሃገራት 20 ህጻናትን ጨምሮ ለ72 ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነው የኬሚካል ጦር መሳሪያ ጥቃት የባሽር አልአሳድ መንግስት ተጠያቂ መሆኑን ገልጸዋል። የሶሪያ የጦር አውሮፕላኖች ማክሰኞ በሰሜናዊ የሃገሪቱ ክፍል ፈጽመውታል የተባለው ጥቃት በተጎጂዎች ላይ ከፍተኛ ...
Read More »በሶማሌ ክልል በሚገኙ 37 ወረዳዎች የኮሌራ ወረርሽኝ መከሰቱን ተመድ ይፋ አደረገ
ኢሳት ( መጋቢት 27 ፥ 2009) በኢትዮጵያ የሶማሌ ክልል ድርቅ ጉዳት እያደረሰባቸው ካሉ 43 ወረዳዎች መካከል በ37ቱ የኮሌራ ወረርሽን መከሰቱን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ይፋ አደረገ። የበሽታውን ስርጭት ለመቆጣጠር ሲባል ከተለያዩ የሃገሪቱ ክልሎች የተውጣጡ ወደ 300 አካባቢ የጤና ባለሙያዎች ወደ ወረዳዎች እንዲሰማሩ የተደረገ ሲሆን፣ ችግሩ ለተጎጂዎች ተጨማሪ ስጋት ማሳደሩ ታውቋል። በክልሉ አጋጥሞ ያለው የምግብና የውሃ እጥረት ለውሃ ወለድ በሽታዎች መዛመት ምክንያት ...
Read More »የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በቂሊንጦ የደርሰውን የእሳት ቃጠሎ ያስነሱት እስረኞች ናቸው ሲል ለፓርላማ ገለጸ
ኢሳት ( መጋቢት 27 ፥ 2009) የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ባለፈው አመት በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ደርሶ የነበረው የእሳት ቃጠሎ አደጋ ያስነሱት በወንጀል ተጠርጥረው የፍርድ ሂደትን የሚጠባበቁ እስረኞች ናቸው ሲል ለፓርላማ ገለጸ። በአጀንዳው ዙሪያ ያካሄደው ጥናት አስመልክቶ ለፓርላማው ሪፖርቱን ረቡዕ ያቀረበው መንግስታዊው ኮሚሽን ከዚሁ በፊት ከሳሽ አቃቤ ህግ እስረኞቹን ተጠያቂ ያደረገበት ሂደት በተመሳሳይ ሁኔታ አቅርቧል። ባለፈው አመት ነሃሴ ወር በእስር ቤቱ ...
Read More »ሱዳንና ኢትዮጵያ በፖለቲካና ወታደራዊ ዘርፎች ትስስር ለመመስረት የሚያስችል አዲስ ስምምነት መድረሳቸው ተነገረ
ኢሳት ( መጋቢት 27 ፥ 2009) የሱዳኑ ፕሬዚደንት ኦማር ሃሰን አልበሽር ሃገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር በፖለቲካና በወታደራዊ ዘርፎች ትስስር ለመመስረት የሚያስችል አዲስ ስምምነት መደረሱን አስታወቁ። ለሶስት ቀን ጉብኝት ማክሰኞ አዲስ አበባ የገቡት ፕሬዚደንት አል-በሽር የኢትዮጵያ ደህንነት እና ፀጥታ ከሱዳን ተለይቶ አይታይም ሲሉ ለጋዜጠኞች መግለጻቸውን ሱዳን ትሪቢዮን ጋዜጣ ዘግቧል። ካለፈው አመት ጀምሮ ለሶስተኛ ጊዜ የሁለትዮሽ ስምምነት የደረሱት ሁለቱ ሃገሮች የፖሊስ የደህንነትና የሰራዊት ...
Read More »በኢትዮጵያ የምግብ ዋጋ ንረት ወደ 8.7 በመቶ ከፍ ማለቱ ተገለጸ
ኢሳት ( መጋቢት 27 ፥ 2009) አዲስ አበባ ከተማን ጨምሮ በተለያዩ ክልሎች በማሻቀብ ላይ ያለን የምግብ ዋጋ ንረት ተከትሎ የመጋቢት ወር የዋጋ ግሽበት ከሰባት በመቶ ወደ 8.5 በመቶ ከፍ ማለቱን የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ አስታወቀ። የወተት ተዋጽዖን ጨምሮ በስጋና በመሰረታዊ የምግብ ሸቀጣሸቀጦች ላይ ከፍተኛ ጭማሪ መመዝገቡን የገለጸው ኤጀንሲው በተለይ የምግብ ዋጋ ባለፈው ወር ከነበረበት የ7.8 ወደ 9.6 በመቶ ሊያድግ መቻሉን መንግስታዊ ...
Read More »በዋልድባ ገዳም አቅራቢያ በአማራና በትግራይ ሚሊሺያዎች መካከል የተጀመረው ግጭት መቀጠሉ ተገለጸ
ኢሳት ( መጋቢት 27 ፥ 2009) በዋልድባ ገዳም አቅራቢያ በአማራና በትግራይ ሚሊሺያዎች መካከል ትናንት የተጀመረው ግጭት መቀጠሉን የአካባቢው ምንጮች ለኢሳት ገለጹ። ለንግስ አምበርታት ገዳም የነበሩ ምዕመናን በግጭቱ ከጉዟቸው መገታታቸው ታውቋል። በዋልድባ አምበርታት ገዳም መጋቢት 27 ፥ 2009 በሚከበረው የመድሃኒያለም ክብረ በዓል ላይ ለመገኘት ይጓዙ የነበሩ የአማራ ክልል ሚሊሺያዎች ትጥቃቸው እንዲፈቱ በመጠየቃቸው ማክሰኞ ዕለት በተጀመረው ግጭት ከሁለቱ ወገን 6 ሚሊሺያዎች ተገድለዋል። ...
Read More »በአዲስ አበባ የሚገኙ አብያተ-ክርስቲያናት ለአባይ ግድብ እያንዳንዳቸው 50ሺህ ብር፣ ካህናትም የአንድ ወር ደሞዛቸው እንዲያዋጡ በድጋሚ ታዘዙ
ኢሳት ( መጋቢት 27 ፥ 2009) ለአባይ ግድብ ግንባታ በአዲስ አበባ የሚገኙ አብያተ-ክርስቲያናት እያንዳንዳቸው 50ሺህ ብር እንዲያዋጡ በድጋሚ ታዘዙ። በአብያተ-ክርስቲያናቱ የሚያገለግሉ ካህናትም የአንድ ወር ደሞዛቸውን ለግድቡ ግንባታ እንዲሰጡ ተወስኗል። በጠቅላይ ቤተክህነት የሚገኙ የእሳት ምንጮች እንደገለጹት በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ 90 ያህል አብያተ-ክርስቲያናት እያንዳንዳቸው የሚያዋጡት 50ሺህ ብር እንዲሁም የካህናቱ የአንድ ወር ደሞዝ በጠቅላይ ቤተ-ክህነት በኩል ለህዳሴው ግድብ ብሄራዊ ምክር ቤት ገቢ ...
Read More »