.የኢሳት አማርኛ ዜና

በደንቢያ ወረዳ የሚታየውን ተቃውሞ ተከትሎ አንድ ቤተክርስቲያን በወታደሮች ተቃጠለ

መጋቢት ፳፰ (ሃያ ስምንት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት በሰሜን ጎንደር ዞን በደንቢያ ወረዳ ጩሃይት ከተማ መጋቢት 26 ቀን 2009 ዓም ጀሪ ደበርጋ ጊዮርጊስ የተባለ ቤተክርስቲያን በአካባቢው በሰፈሩ ወታደሮች ተቃጥሏል። ህዝቡ በድርጊቱ በመቆጣት ተቃውሞውን ሲያሰማ ወታደሮች ድርጊቱን የፈጸሙት የአርበኞች ግንቦት 7 አባላት ናቸው በማለት ህዝቡን ለማሳመን ቢሞክሩም ፣ ነዋሪዎች ግን አልተቀበሉትም። ወታደሮቹ ድርጊቱን የፈጸሙት በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ ...

Read More »

በወሎ ለእርዳታ የመጣ እህል መዘረፉን ነዋሪዎች ተናገሩ በሙስና እና በአስተዳደር ችግር የተማረሩት ዜጎች መንግስት አለ ወይ ሲሉ ይጠይቃሉ።

መጋቢት ፳፰ (ሃያ ስምንት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ሳምንት በወሎ በተደረገው ስብሰባ ለእርዳታ የተላከ እህል፣ ዘይት፣ ክክ እና ሌሎችም ነገሮች እየተዘረፉ መሆኑን የሚናገሩት አቶ አለባቸው አረጋ፣ ሰራተኞች በሞቱ ሰዎች ሳይቀር እየፈረሙ ገንዘብ ይወስዳሉ ይላሉ። ነዋሪዎቹ 100 ኩንታል የእርዳታ ስንዴ በባለስልጣናት መዘረፉንም ይገልጻሉ ። ልማት የለም የሚሉት አቶ አለባቸው፣ ስኳር እና ዘይት ካየን 5 ወራት አልፎናል ብለዋል። መሬት በአምቻ ...

Read More »

በመላው አገሪቱ በሚገኙ ወረዳዎች መብራት የለም በሚባልበት ደረጃ ላይ መደረሱን መረጃዎች አመለከቱ

መጋቢት ፳፰ (ሃያ ስምንት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የውሃ፣ መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስቴር የተወካዮች ምክር ቤት አባላት፣ ከህዝብ ያሰባሰቡትን መረጃ አጠናክረው የላኩትን መረጃ በማድረግ በጻፈው ደብዳቤ በመላ አገሪቱ የሚታየው የመብራት መቆራረጥ ህዝቡን ተስፋ አስቆርጦታል። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ጽ/ቤት ፣ በፓርላማ አባላት አማካኝነት ከህዝብ ያሰባሰባቸውን 66 ገጽ ጥያቄዎችን ለውሃ፣ መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስቴር የላከ ሲሆን፣ ጥያቄዎቹ በአብዛኛው በመብራት መቆራረጥ፣ ...

Read More »

በአፋር የመንግስት ሰራተኞች ያለፈቃዳቸው ለብሄር ብሄርሰቦች በአል በሚል ግማሽ ደሞዛቸው ተወሰደባቸው

መጋቢት ፳፰ (ሃያ ስምንት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የመንግስት ሰራተኞች ለኢሳት እንደገለጹት ለበአሉ በሚል ደሞዛቸው ያለፈቃዳቸው መቆረጡን ካወቁ በሁዋላ፣ አቤቱታ ማሰማታቸውን ተከትሎ በአዋሽ አርባ ዞን የጤና ባለሙያዎችን ማክሰኞ መጋቢት 26 ቀን 2009 ዓም በመስብሰብ ለማወያየት ቢሞክሩም ፣ ሰራተኞች ግን ድርጊቱን በመቃወም አልተቀበሉትም። በዚህ የተበሳጩት ባለስልጣናት እናንተ ፈቃደኞች ሆናችሁም አልሆናችም ደሞዛችሁ ይቆረጣል በማለት የእብሪት መልስ ሰጥተዋል። ዛሬ መጋቢት 28 ደግሞ ...

Read More »

በሶማሌ ክልል በልዩ ሃይል የተፈጸመው ግድያና የሰብዓዊ መብት ጥሰት ትኩረት አለመሰጠቱ ተገለጸ

ኢሳት (መጋቢት 28 ፥ 2009) በኢትዮጵያ የሶማሌ ክልል ባለፈው አመት በልዩ ሃይሎች የተፈጸሙ የነዋሪዎች ግድያና የሰብዓዊ መብት ጥሰት በሃገሪቱ ባለስልጣናት ዘንድ ትኩረት አለመሰጠቱ ስጋት እንዳሳደረበት ሂዩማን ራይትስ ዎች ሃሙስ አስታወቀ። በክልሉ የተቋቋሙ ልዩ ሃይሎች በሰኔ ወር 2008 አም በምስራቃዊ የክልሉ ግዛት ስር በምትገኘው ያዳማክ ዱባድ መንደር በፈጸሙት ጥቃት 21 ነዋሪዎች ተገድለው በርካቶች ድብደባና እንግልት እንደተፈጸመባቸው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋም በጉዳዩ ...

Read More »

በአማራና በትግራይ ሚሊሺያዎች መካከል የተካሄደው ግጭት አዲስ ውጥረት ማንገሱን አንድ አለም አቀፍ ተቋም አስታወቀ

ኢሳት (መጋቢት 28 ፥ 2009) በዋልድባ ገዳም አካባቢ በአማራና በትግራይ ሚሊሺያዎች መካከል ለሁለት ቀን የተካሄደው ግጭት በስፍራው አዲስ ውጥረት ማንገሱን አንድ አለም አቀፍ ተቋም ሃሙስ አስታውቋል። ይኸው በመከላከያና ደህንነት ዙሪያ የሚሰራውና መቀመጫውን በብሪታኒያ ያደረገው ጄን የተሰኘ ተቋም ለሁለት ቀን በዘለቀው የሁለቱ ወገኖች ግጭት በትንሹ ስድስት ሰዎች መሞታቸውን የተለያዩ መረጃዎችን ዋቢ በማድረግ በጉዳዩ ዙሪያ ባወጣው ሪፖርት አመልክቷል። የአይን እማኞች በዋድባ እምበርታት ...

Read More »

በበለጸጉ ሃገራት ለኢትዮጵያ ሊሰጥ የነበረ የ100 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ተቃውሞ ገጠመው

ኢሳት (መጋቢት 28 ፥ 2009) አሜሪካንን ጨምሮ የተለያዩ የበለጸጉ ሃገራት ለኢትዮጵያ አረንጓዴ ልማትና ድርቅ ጋር በተያየዘ ሊሰጥ የነበረ የ100 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ እንዳይሰጥ ተቃወሙ። ግሪን ክላይሜት ፈንድ (Green Climate Fund) የተሰኘና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ስር የሚገኝ የአካባቢ ልማት ፕሮጄክት በደቡብ ኮሪያ ሰንግዶ ከተማ እያካሄደ ባለው ጉባዔ ለኢትዮጵያ ሊሰጥ በታሰበው የገንዘብ ድጋፍ ረቡዕ ምክክር መጀመሩን ክላይሜት ሆም የተሰኘ የአካባቢ የመገናኛ አውታር ...

Read More »

በጎንደር ፍሎሪዳ ሆቴል የደረሰውን የቦምብ ፍንዳታ ተከትሎ የብሪታኒያ መንግስት ዜጎቹ የጉዞ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ጠየቀ

ኢሳት (መጋቢት 28 ፥ 2009) በሳምንቱ መገባደጃ ቅዳሜ በጎንደር ከተማ በሚገኘው የፍሎሪዳ አለም አቀፍ ሆቴል ላይ የደረሰውን የቦንብ ፍንዳታ ተከትሎ የብሪታኒያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዜጎቹ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ሃሙስ አሳሰበ። የከተማዋ ነዋሪዎች በሆቴሉ ላይ በደረሰው ጥቃት በትንሹ ሶስት ሰዎች መጎዳታቸውንና ድርጊቱ በከተማው አዲስ ውጥረት ማንገሱን ለኢሳት መግለጻቸው ይታወሳል። መንግስት ሰለቦንቡ አደጋ እስካሁን ድረስ የገለጸው ነገር ባይኖርም የብሪታኒያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ...

Read More »

በሰሜን ጎንደር ዞን በደንቢያ የሚገኘው የቻይና ኩባንያ በድርጅቱ ላይ የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ ከአካባቢው ለቆ ወጣ

መጋቢት ፳፯ (ሃያ ሰባት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በዚያው በደንቢያ የሚሊሺያ ሃላፊው ህዝቤን መሳሪያ አላስገፍፍም በማለት ራሱን አጥፍቷል። ለኢሳት የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት የአርሶአደሩን መሬት ያለበቂ ካሳ በመንጠቅ እንዲሁም በሰራተኞች ላይ በደል በማድረስ በሚታወቀው ጎርጎራ አካባቢ በሚገኘው የቻይና ካምፕ ላይ መጋቢት 25 እና 26 በተፈጸመው ጥቃት 3 ሰዎች መገደላቸውን እና በበርካታ ተሽከርካሪዎች ላይ ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ ፣ የመንገድ ስራ ድርጅቱ ...

Read More »

በቀድሞው የምርጫ ቦርድ ምክትል ሃላፊ የሚመራው የሰብአዊ መብት ድርጅት በቂሊንጦ የደረሰው የእሳት አደጋ ሆን ተብሎ በእስረኞች የተነሳ ነው አለ

መጋቢት ፳፯ (ሃያ ሰባት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ራሱን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ብሎ የሚጠራው እና በህወሃት አባሉ በቀድሞው የምርጫ ቦርድ ምክትል ሊ/መንበር ዶ/ር አዲሱ ገ/እግዚአብሄር የሚመራው ድርጅት በዛሬው ዕለት ለፓርላማው ፍትህ እና አስተዳደር ጉዳዮች ቆሚ ኮሚቴ ባቀረበው ሪፖርት፣ የእሳት አደጋው እንዲነሳ ያደረጉት በከፍተኛ ወንጀል ተጠርጥረው የፍርድ ሂደቱን የሚጠባበቁ እስረኞች ናቸው በማለት የፖሊሲን መረጃ አጠናክሯል። የኮሚሽኑ ኮምሽነር ዶ/ር አዲሱ ...

Read More »