ሚያዝያ ፲፮ (አሥራ ስድስት) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የክልሉ ወኪላችን የክልሉን ፖሊስ ኮሚሽን መረጃዎችን ዋቢ በማድረግ እና ፖሊሶች በየቀኑ የሚለዋወጡ የስልክ መረጃዎችን ተንተርሳ ባጠናቀረችው መረጃ፣ የአካባቢው ነዋሪዎች ከመልካም አስተዳደር እጦት፣ ከፍትህ መጓደል፣ ከመሬት ጋር በሚነሳ አምባጓሮ ፣ ድህነትና ስራ አጥነት ፣ ሙስናና ተዛማጅ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ በሚፈጠሩ አለመግባባቶች እንዲሁም ፖሊሶችና ወታደሮች በሚወስዱዋቸው እርምጃዎች ከሰኞ እስከ ሃሙስ በአሉት ቀናት ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በደቡብ ኦሞ ዞን አራት ህጻናት በጎርፍ ተወሰዱ
ሚያዝያ ፲፮ (አሥራ ስድስት) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡብ ኦሞ ዞን ዋና ከተማ ጅንካ አዋሳኝ በሆነው በካይሳ ቀበሌ ቅዳሜ ሚያዚያ 14/2009 ከሰዓት በኋላ ነፋስ ቀላቅሎ በጣለው ከባድ ዝናብ አቶ ታደሰ የተባሉ የቀበሌው ነዋሪ ሁለት ልጆች፣ የታናሽ ወንድማችው አንድ ልጅ፣ እንዲሁም የጎረቤታቸው አንድ ልጅ በአጠቃላይ አራት ህጻናት በጎርፍ መወሰዳቸውን የአካባቢው ምንጮች ገልጸዋል፡፡ የጎርፍ አደጋው የደረሰው የዞኑ ግብርና ቢሮ ከቀበሌው ...
Read More »አዲስ የተሾሙት አመራሮች በቡድን ተደራጀው በህዝብ ላይ ጉዳት እያደረሱ መሆናቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ
ሚያዝያ ፲፮ (አሥራ ስድስት) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቅርቡ እየተመደቡ ያሉ አመራሮች በቡድን ተደራጅተው በህብረተሰቡ ላይ ችግሮችን በመፍጠር ላይ መሆናቸውን የሚናገሩት የአዴት ከተማ ነዋሪ ወይዘሮ እማመይ አለባቸው፣ ከቀበሌ ሁለት አመራር ጀምሮ እስከ ከንቲባው ድረስ ህዝብን በማመስ ማስቸገር እንጅ ምንም አይነት ስራ ሲሰሩ አይታዩም ይላሉ። ከአሁን በፊት በብአዴን አባልነት ይሳተፉ እንደነበር የገለጹት ቅሬታ አቅራቢ ስርዓቱ ሙሰኝነት የተንሰራፋበት በመሆኑ በዚህ ...
Read More »ታዋቂው ጸሃፊ የፖለቲካ ሰውና የህግ ባለሙያ አቶ አሰፋ ጫቦ አረፉ
ሚያዝያ ፲፮ (አሥራ ስድስት) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አቶ አሰፋ ጫቦ ከአባታቸው አቶ ሰዴ ሃማ ከእናታቸው ወ/ሮ ማቱኬ አጆ በቀድሞው አጠራር በጋሞጎፋ ጠቅላይ ግዛት ውስጥ በጨንቻ ከተማ 1936 ዓ.ም ተወለዱ። እድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ በቤተክህነት ውስጥ ፊደል በመቁጠር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን እስከ ድቁና ማእረግ በመድረስ አገልግለዋል። የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በጨንቻ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸው ደግሞ ሻሸመኔ እና አዲስ አበባ ...
Read More »ሶስት የፖለቲካ ድርጅቶች ህዝባዊ ተቃውሞ እንዲባባስ አድርገዋል ተብለው ክስ ሊመሰረትባቸው መሆኑን ታወቀ
ኢሳት (ሚያዚያ 13 ፥ 2009) ሶስት የፖለቲካ ድርጅቶች ከአንድ አመት በፊት በኦሮሚያና በሌሎች ክልሎች ሲካሄድ የቆየው ህዝባዊ ተቃውሞ እንዲባባስ አድርገዋል ተብለው ክስ ሊመሰረትባቸው መሆኑን ታወቀ። ከቀናት በፊት በህዝባዊ ተቃውሞ ወቅት የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ሲመረምር የቆየው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን፣ ሶስት የፖለቲካ ድርጅቶች ተቃውሞ እንዲቀሰቅስና እንዲባባስ የተለያዩ አስተዋጽዖ አድርገዋል ሲል ለፓርላማ ባቀረበው ሪፖርት አመልክቷል። የኮሚሽኑን ሪፖርት ያቀረበው የህዝብ ተወካዮች ምክር ...
Read More »በጋምቤላ የእርሻ መሬት ጋር በተያያዘ ሲሰጥ በነበረው ብድር እጃቸው አለበት የተባሉ 25 የክልሉ ሃላፊዎችና ሰራተኞች ክስ ተመሰረተባቸው
ኢሳት (ሚያዚያ 13 ፥ 2009) መንግስት በጋምቤላ ክልል ሲሰጥ ከቆየው ሰፋፊ የእርሻ መሬት ጋር በተገናኘ በቢሊዮን ብር የሚቆጠር ኪሳራ እንደደረሰበት አስተዋጽዖ ነበራቸው የተባሉ 25 የክልሉ ሃላፊዎችና ሰራተኞች ክስ ተመሰረተባቸው። ተከሳሹ ከ28 በላይ ለሚሆኑ ባለሃብቶች ተገቢ ያልሆነ የኢንቨስትመንት ፍቃድና የመሬት ካርታ በመስጠት ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ በግል ባንካቸው ሂሳብ ማስቀመጣቸውን ከሳሽ አቃቤ ህግ በክሱ አመልክቷል። ሶስት የፖለቲካ ድርጅቶች ከአንድ አመት በፊት ...
Read More »የአቅም ችግር ታይቶባቸዋል የተባሉ የብዓዴን እና የኦህዴድ ከፍተኛ ባለስልጣናት በሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ ስልጠና ሊሰጣቸው ነው ተባለ
ኢሳት (ሚያዚያ 13 ፥ 2009) በጥልቅ ተሃድሶው የአቅም ችግር ታይቶባቸው የተባሉ የብዓዴን እና የኦህዴድ ከፍተኛ ባለስልጣናት በሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ ስልጠና ሊሰጣቸው መሆኑን ተነገረ። የመጀመሪያው ዙር ስልጠና ከብዓዴን የድርጅቱ የጽህፈት ቤት ሃላፊና አማራውን በመዝለፍ የሚታወቁት አቶ አለምነህ መኮንን ተከተዋል። የመጀመሪያው ዙር ስልጠና በመጭው ሰኞ ይጀምራል። በሁለተኛው ዙር ደግሞ የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በአቅም ችግር ስልጠና ይወስዳሉ ተብሏል። በሁለተኘው ዙር ...
Read More »በሰሜን ጎንደር የነጻነት ታጋዮች የሚፈጽሙት ጥቃት ቀጥሎአል
ሚያዝያ ፲፫ (አሥራ ሦስት) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአርበኞች ግንቦት7 አባላት የሆኑ ታጋዮች በደምቢያ ወረዳ ሰረባ መስኖ አጠገብ ሌሊት ላይ ጥቃት ፈጽመው፣ 2 ገልባጭ መኪኖችና አንድ እስካቫተር መኪና የተቃጠሉ ሲሆን፣ በታጋዮች እና ድርጅቱን በሚጠብቁት መካከል ለ30 ደቂቃ ያክል የተኩስ ልውውጥ መካሄዱንና አንድ ወታደር መገደሉን ድርጅቱ ለኢሳት በላከው መረጃ አስታውቋል። ኢሳት ወደ አካባቢው ነዋሪዎች ስልክ በመደወል በመኪኖች ላይ ከፍተኛ ...
Read More »በአለፉት 6 ወራት ብቻ 325 ሰዎች እስር ቤት ህይወታቸው አልፏል
ሚያዝያ ፲፫ (አሥራ ሦስት) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በ2009 ዓ.ም የስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ 325 በእስር ላይ የነበሩ ዜጎች ህይወታቸውን አጥተዋል። አሃዙ በቅሊንጦ እስር ቤት በእሳት የጋዩት እና በጥይት የተገደሉን እንዲሁም በብርሸለቆ እና በሰባት አሚት እስር ቤት በግፍ የተገደሉ እስረኞችን ያካተተ ነው። ይሁን እንጅ አሃዙ በየቀበሌው ያሉትን ጊዚያዊ እስር ቤቶችን መረጃ አላካተተም። ከ325 ሟች እስረኞች መካከል 49 ኙ ...
Read More »የአንድ ለአምስት አደረጃጀት ከሽፏል ተባለ
ሚያዝያ ፲፫ (አሥራ ሦስት) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቀድሞዋ ምስራቅ ጀርመንና በበርካታ የሶሻሊስት አገሮች ሲሰራበት የነበረው የመንግስት ሰራተኛውን በአንድ ለአምስት አደራጅቶ የመቆጣጠርና የመምራት አሰራር መክሸፉን አንድ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን ተናግረዋል። ሰሞኑን በባህር ዳር ከተማ አመራር አካዳሚ በተደረገ ስብሰባ ላይ የአካዳሚው ዳይሬክተር፣ የመንግስት ሠራተኛው የአንድ ለአምስትን ስብሰባን “መቼ ነው አላቆኝ የማየው?” በማለት በምሬት እስከ መግለጽ ደርሷል ብለዋል፡፡የዚህ ዓይነት ጥላቻ ...
Read More »