.የኢሳት አማርኛ ዜና

የአርበኛ ጎቤ መለኬ የእህት ልጅ ታፍኖ ተወሰደ

ግንቦት ፬ ( አራት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት የአርበኛ ጎቤ የእህት ልጅ የሆነው ወጣት ዳዊት አንጋው ትናንትና ነው በወያኔ ታጣቂዎች ታፍኖ የተወሰደው። ታጣቂዎቹ ወጣት ዳዊትን አፍነው የወሰዱበትም ምክንያት ያልተናገሩ ሲሆን፤ በጎንደር ሁለተኛ ፖሊስ ጣቢያ እንደታሰረ ማረጋገጣቸውን ምንጮቹ ጠቅሰዋል። አርበኛ ጎቤ መልኬ ያለፈውን ሕዝባዊ አመጽ ተከትሎ እጅግ በርካታ ሀብትና ንብረቱን ትቶ የሀገሩን ነጻነት ለማስከበር ከወያኔ ...

Read More »

በዶክተር ቴዎድሮስ አድኃኖም ላይ እየተካሄደ ያለው የተቃውሞ ዘመቻ ዓለማቀፍ የመገናኛ ብዙሀን ሽፋን እያገኘ ነው።

ግንቦት ፬ ( አራት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሎስ አንጀለስ ሴንቲኔል፣አፍሪካን ኒውስና በርካታ የውጪ ሚዲያዎች ፣ ኢትዮጵያን በመወከል የዓለም የጤና ድርጅት ዳይሬክተር ለመሆን የሚወዳደሩት ዶክተር ቴዎድሮስ አድኃኖም በኢትዮጵያውያን ዘንድ የተቀናጀና ተከታታይ የተቃውሞ ዘመቻ እየተካሄደባቸው እንደሆነ አስነብበዋል። ዶክተር ቴዎድሮስ አድኃኖምን በማስተዋወቁ ረገድ ከአንዳንድ አካላት ድርጅቱን ለመምራት ብቃት እንዳላቸው ቢገለጽም፣ በበርካታ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ብቁ አይደሉም የሚል ተቃውሞ እንደገጠማቸው ተገልጿል። ...

Read More »

በሽብርተኝነት ተጠርጥረው የተከሠሱት እነ ሉሉ መሰለ የመከላከያ ምስክሮቻቸውን አሰሙ::

ግንቦት ፬ ( አራት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በተመሰረተባቸው የሽብርተኝነት ክስ በፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት እንዲከላከሉ እንዲከላከሉ የተበየነባቸውን የሰማያዊ ፓርቲ አባልና የ2007 ዓ.ም ሀገራዊምርጫ የአርባ ምንጭ አካባቢ የክልል ምክር ቤት ተወዳዳሪ አቶ ሉሉ መሰለን ጨምሮ 7 ተከሳሾች የመከላከያ ምስክሮቻቸውን አሰምተዋል፡፡ አቶ ሉሉ መሰለ የቀረበባቸው ክስ፣በአርባ ምንጭ ከተማ የሚገኙ ወጣቶችን በአርበኞች ግንቦት ሰባት አባልነት በመመልመል ወደ ኤርትራ ይልካል ...

Read More »

በአማራ ክልል ሙስና ፈጽመዋል የተባሉ 211 ግለሰቦች በፅኑ እስራትና በገንዘብ መቀጣታቸው ተገለጸ።

ግንቦት ፬ ( አራት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የክልል የስነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ እውነቴ አለነ ፤ ግለሰቦቹ የተቀጡት ባለፉት ዘጠኝ ወራት በተደረገ ጠንካራ የክትትልናየቁጥጥር ስራ ጥፋተኛ ሆነው በመገኘታቸው ነው በማለት ለመንግስት መገናኛ ብዙሀን ገልጸዋል። ከተከሳሾቹ መካከል 182ቱ ወንድና 29ኙ ሴቶች ሲሆኑ፤በተመሰረተባቸው በስልጣን ያለ አግባብ በመጠቀም፣ በግዢና ጨረታ ሙስና፣ በተጭበረበረ ሰነድበመገልገል፣ በግብር መሰወርና በመሰል የወንጀል ...

Read More »

ህወኃት በሁመራ ከተማ የአማራ እና የትግራይ ተወላጅ ሽማግሌዎችን በመመልመልና “እርቅ እናውርድ!” በሚል መሪ ሀሳብ ሕዝባዊ ስብሰባ ሊያደርግ መሆኑን የከተማው ነዋሪዎች ለኢሳት ገለጹ።

ግንቦት ፬ ( አራት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ህወኃት ይህን ለማድረግ የተዘጋጀው ከልቡ እርቅና ፍቅርን ፈልጎ ሳይሆን በእርቅ ስም ፖለቲካ ቁማር ለመጨዋት በመኾኑ ሕዝቡ ሁኔታውን በጥንቃቄ እንዲከታተልና ህወኃት በቀደደለት ቦይ እንዳይሄድ የነዋሪዎቹ ውቀኪሎች ተናግረዋል። እንዲሁም ጠገዴን ከሁለት በመክፈል ጠገዴ ና ፀገዴ ብሎ የለዬውና በድንበር ጉዳይ ህዙቡን ሲያጋጭ የቆዬው ህወኃት በአሁኑ ሰዓት የሁለቱን አካባቢ እርቅ አውራጅ ሽማግሌዎች ባህርዳር ...

Read More »

የብሪታኒያ መንግስት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እንዲለቀቁ ግፊት እየተደረገበት ነው

ኢሳት (ግንቦት 3 ፥ 2009) የብሪታኒያ መንግስት ባለስልጣናት በሃገሪቱ በሶማሊያ ጉዳይ ላይ በሚመከረው አለም አቀፍ ጉባዔ ላይ እየተሳተፉ ከሚገኙ የኢትዮጵያ መሪዎች ጋር በአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ጉዳይ ዙሪያ እንዲመክሩ የሃገሪቱ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋም ሃሙስ ጥሪ አቀረበ። በለንደን ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው በዚሁ ጉባዔ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ተሳታፊ ሲሆኑ ከብሪታኒያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና ጠቅላይ ሚኒስትሯ ቴሬሳ ሜይ ጋር ውይይትን ...

Read More »

ለአለም ጤና ድርጅት ቀጣዩ ዋና ዳይሬክተር ለመሆን እየተወዳደሩ ባሉት በዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ላይ በርካታ ተቃውሞዎች እየቀረበባቸው ነው

ኢሳት (ግንቦት 3 ፥ 2009) ለአለም ጤና ድርጅት ቀጣዩ ዋና ዳይሬክተር ለመሆን ከመጨረሻዎቹ ሶስቱ ተፎካካሪዎች አንዱ የሆኑት ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ከበርካታ ኢትዮጵያ ዘንድ እየቀረበባቸው ያለው ተቃውሞ ተጠናክሮ መቀጠሉን ግሎባል ኢንፎርሜሽን ኔትዎርክ የተሰኘ ጋዜጣ ዘገበ። የአለም ጤና ድርጅቱ አባል ሃገራት በቅርቡ ቀጣዩን የድርጅቱ ሃላፊ ለመምረጥ በዝግጅት ላይ እያሉ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የማህበራዊ ድረ-ገጾችን በመጠቀም የተቃውሞ ቅስቀሳን እያካሄዱ እንደሚገኝ ጋዜጣው አስነብቧል። ዶ/ር ...

Read More »

የኬንያ ሳምቡራ ግዛት ሃላፊዎች በኢትዮጵያ በጀመሩት ጉብኝት ታቃውሞ ተቀሰቀሰ

ኢሳት (ግንቦት 3 ፥ 2009) የኬንያ የሳምቡራ ግዛት ሃላፌዎች ረቡዕ በኢትዮጵያ የጀመሩት የስራ ጉብኝት በግዛቲቱ የበላይ አስተዳዳሪዎች ዘንድ የህዝብ ሃብትን ማባከን ነው በሚል ተቃውሞ ቀሰቀሰ። በሰሜን ማዕከላዊ ኬንያ ስር የሚገኘው የግዛቲቱ የልዑካን ቡድን ዘጠን አባላት በኢትዮጵያ ለሚያደርጉት የስምንት ቀን ቆይታ ከ58 ሺ ዶላር በላይ (ስድስት ሚሊዮን የኬንያ ሽልንግ) በጀት መያዛቸውን ዘ-ስታር የተሰኘ የኬንያ ጋዜጣ ዘግቧል። ከተለያዩ የግዛቲቱ የስራ ሃላፊነት የተመረጡ ...

Read More »

የአቶ ፈቃደ ሸዋ ቀና የቀብር ስነስርዓት ቅዳሜ ግንቦት 5 ፥ 2009 ዓም አደልፊ በሚገኘው የጆርጅ ዋሽንግተን የመቃብር ቦታ እንደሚፈጸም ተገለጸ

አቶ ኢሳት (ግንቦት 3 ፥ 2009) የታዋቂው ምሁርና የፖለቲካ ሰው የአቶ ፈቃደ ሸዋ ቀና የቀብር ስነስርዓት ቅዳሜ ግንቦት 5 ፥ 2009 ዓም አደልፊ በሚገኘው የጆርጅ ዋሽንግተን የመቃብር ቦታ እንደሚፈጸም ተገለጸ። የስነስርዓቱ አስተባባሪ ኮሜቴው ለኢሳት በላከው መግለጫ የአቶ ፈቃደ ሸዋቀና የቀብር ስነስርዓት የሚጀምረው በዋሽንግተን መንበረ-ፀባዖት ቅድስት ማሪያም  ቤተክርስቲያን ጠዋት ላይ በሚካሄደው ጸሎተ ፍትሃት ይሆናል። ከጠዋቱ 9 ሰዓት እስከ 11 ሰዓት AM ...

Read More »

ከኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥንና ሬዲዮ  የተሰጠ መግለጫ

ኢሳት (ግንቦት ፥ 2009) የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥንና ሬዲዮ (ኢሳት) በሃገር ቤትና በአካባቢው ሲያስተላልፍ የነበረው የሳተላይት ስርጭት እንደተለመደው በአገዛዙ ጭንቀትና ስጋት ምክንያት በህወሃት ኢህአዴግ የሚመራው መንግስት ከፍተኛ ወጪ በማውጣት ስርጭቱ እንዲቋረጥ አድርጎ ህዝቡ መረጃ እንዳያገኝ ተፅዕኖ በመፍጠር ላይ ይገኛል። በኢሳት ምክንያት እንቅልፍ ያጣው የህወሃት /ኢህአዴግ አገዛዝ አሁን ደግሞ እንደተለመደው የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም የሳተላይት ስርጭቱ እክል እንዲገጥመው አድርጓል። ይሁን እንጂ የኢሳት አመራር ...

Read More »