ኢሳት (ግንቦት 15 ፥ 2009) በኢትዮጵያ በተፈጸመው የሰብዓዊ መብት ረገጣዎች እጃቸው አለበት የሚባሉት እና በገዢው የህወሃት የአመራር ስልጣን ከፍተኛ ሃላፊነት ያላቸው ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የአለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተመረጡ። ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የኢትዮጵያ ጤና ጥበቃ ሚኒስትር በነበሩ ጊዜ የኮሌራ በሽታ እንዲደበቅ አድርገዋል በሚል በኒውዮርክ ታይምስና በዋሽንግተን ፖስት ጋዜጦች ዘገባዎች ሲቀርቡባቸው እንደነበር ይታወሳል። የአለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ለመሆን ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በሶማሌ ክልል ከ700 የሚበልጡ ሰዎች በአጣዳፊ ተቅማትና ትውከት በሽታ ህይወታቸው ማለፉን የአለም ጤና ድርጅት አስታወቀ
ኢሳት (ግንቦት 15 ፥ 2009) በኢትዮጵያ የሶማሌ ክልል ከ700 የሚበልጡ ሰዎች በአጣዳፊ ተቅማትና ትውከት በሽታ ህይወታቸው ማለፉን የአለም ጤና ድርጅት አስታወቀ። መንግስት በሽታው ኮሌራ አይደለም ቢልም የአለም ጤና ባለሙያዎች የአጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት በሽታው ኮሌራ ስለመሆኑ የላቦራቶሪ ውጤት መገኘቱን እንዳረጋገጡ ኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ባለፈው ሳምንት ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። ይሁንና የአለም ጤና ድርጅት የአጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት ክስተት ሲል በገለጸው ወረርሽኝ ባለፉት አራት ...
Read More »በጋምቤላ የወባ በሽታ ወረርሽኝ ተቀስቅሶ ከ500 በላይ የሚሆኑ ሰዎች መታመማቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ይፋ አደረገ
ኢሳት (ግንቦት 15 ፥ 2009) በጋምቤላ ክልል በማጃንግ ዞን ስር በሚገኙ አራት ቀበሌዎች የወባ በሽታ ወረርሽኝ መቀስቀሱን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ይፋ አደረገ። በማጃንግ ዞን በመንገሺ ወረዳ በመሰራጨት ላይ ባለው በዚሁ ወረርሽኝ እስከአሁን ድረስ ከ550 የሚበልጡ ሰዎች ለህመም መዳረጋቸውንና በሽታው ወደ አጎራባች ቀበሌዎች ይዛመታል የሚል ስጋት ማሳደሩን ድርጅቱ በክልሉ ያለውን የበሽታውን ስርጭት አስመልክቶ ባወጣው ሪፖርቱ አመልክቷል። በእስካሁኑ የበሽታው ስርጭት የሞተ ሰው ...
Read More »በአገሪቱ ያሉ የደህንነት ሰራተኞች ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው
ግንቦት ፲፭ ( አሥራ አምስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሚያዚያ ወር መጀመሪያ ላይ በአገሪቱ የሚገኙ ዋና ዋና የደህንት አባላት ድሬዳዋ ውስጥ ለ9 ቀናት የቆየ የማጣሪያና የመለያ ስብሰባ አካሂደዋል። በስብሰባው ላይ የህወሃት አባል ያልሆኑ የሌሎች ብሄር ተወላጆች፣ የትግራይ ተወላጅ የሆኑ የደህንነት አባላትን ለጠላት አጋልጠው በመስጠት ህይወታቸው እንዲያልፍ እያደረጉ ነው በሚል ከፍተኛ ወቀሳ ደርሶባቸዋል። የደህንነት አባላቱ ለስርዓቱ ታማኝ ያልሆኑ ...
Read More »ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የአለም የጤና ድርጅት መሪ ሆነው ተመረጡ
ግንቦት ፲፭ ( አሥራ አምስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአለም የጤና ድርጅትን በዳይሬክተርነት ለመምራት ለመጨረሻው ዙር ውድድር የቀረቡት ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም፣ ከኢትዮጵያ ዶ/ር ዴቪድ ናባሮ ከእንግሊዝ እንዲሁም ዶ/ር ሳኒያ ኒሽታር ከፓኪስታን የመጨረሻውን የምረጡኝ ዘመቻ ቅስቀሳ ካደሩ በሁዋላ ዶ/ር ቴዎድሮስ ተመርጠዋል። ሁሉም ተወዳዳሪዎች የ15 ደቂቃ ንግግሮችን ያደረጉ ሲሆን፣ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ቢመረጡ ሁሉም ዜጎች የጤና ሽፋን እንዲያገኙ እንዲሁም ...
Read More »ኢትዮጵያ “ በኤርትራ ላይ አዲስ ፖሊስ አውጥቻለሁ” ማለቷ ባዶ ማዘናጊያ ነው ሲሉ የኤርትራው መሪ ተናገሩ
ግንቦት ፲፭ ( አሥራ አምስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኤርትራው ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ ለአገር ውስጥ የሚዲያ አካላት እንደተናገሩት፣ ህወሃት በኤርትራ ላይ አዲስ ፖሊሲ ነድፌያለሁ ማለቱ ፣ በአገር ውስጥ የገባበትን የፖለቲካ አጣብቂኝ ተከትሎ ትኩረት ለማስቀየስ በሚል የሚለቀው ፕሮፓጋንዳ ነው። ይህ ትርጉም የለሽ ፕሮፓጋንዳ በኤርትራ ላይ የሚያመጣው ተጽኖ አይኖርም ሲሉም አቶ ኢሳያስ ተናግረዋል። ህወሃት የተከተለው የተሳሳተ ፖሊሲ በኤርትራና ...
Read More »በአውሮፓ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በስዊዘርላንድ ጄኔቭ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም እንዳይመረጡ ከፍተኛ ተቃውሞ አሰሙ
ግንቦት ፲፬ ( አሥራ አራት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጽ/ቤት ፊት ለፊት በተካሄደው ተቃውሞ ኢትዮጵያውያን ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የአለም የጤና ድርጅት ሆነው ለመጨረሻው ዙር ውድድር መቅረባቸውን በከፍተኛ ሁኔታ ተቃውመዋል። ዶ/ር ቴዎድሮስ እና እርሳቸው የሚወክሉትን የህወሃት /ኢህአዴግ አገዛዝ ፖሊሲዎችና በስልጣን ላይ በነበሩበት ጊዜ የሰሩዋቸውን ወንጀሎች እየጠቀሱ ውግዘታቸውን አሰምተዋል። ከለንደን ወደ ጀኔቫ በመሄድ ሰልፉን ሲያስተባብሩ ከነበሩት ...
Read More »የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጄንሲ የኦሮሚያ ቴሌቪዥንን ከሰሰ
ግንቦት ፲፬ ( አሥራ አራት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የክሱ ምክንያት ኤጄንሲው ከኦሮሚያ ክልል ወስዶት የነበረውን 200 ሺህ ካሬ ሜትር መሬት አስመልክቶ የኦሮሚያ ቴሌቪዥን በቅርቡ ያስተላለፈው ፕሮግራም ነው። ኢንሳ በቀን 09-09-2009 ለአቶ ለማ መገርሳ በጻፈው በዚሁ ደብዳቤ በ2002 ዓመተ ምህረት ለሥራ ኃላፊዎችና ለሠራተኞች መኖሪያ የሚሆን ካምፕ መሥሪያ መሬት የክልሉን መንግስት ጠይቆ በለገጣፎና በለገዳዲ መስተዳድር 200 ሺህ ሄክታር ...
Read More »በባህርዳር ዙሪያ ቦንብ መፈንዳቱን ተከትሎ ውጥረ ሰፍኖ ሰነበተ
ግንቦት ፲፬ ( አሥራ አራት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ቅዳሜ ምሽት በባህርዳር ዙሪያ ወረዳ ጭስ አባይ ከተማ ላይ የእጅ ቦንብ መወርወሩን ተከትሎ ባህርዳር እና አካባቢዋ እስከ ትናንት ድረስ ከፍተኛ ቁጥር ባላቸው ፌደራል ፖሊስ አባላት ተወረው እንደነበር የአይን እማኞች ገልጸዋል። ለልማት በሚል በሚወሰድ መሬት የካሳ ክፍያ ውዝግብ መነሳቱን የሚገልጹት ምንጮች፣ ማንነታቸው ያልተወቁ ሃይሎች፣ በአካባቢው ነዋሪ የሆነና የህወሃት/ኢህአዴግ ...
Read More »ኢህአዴግ በ3 ዙር 2 ሺ ካድሬዎችን ሊያሰለጥን ነው
ግንቦት ፲፬ ( አሥራ አራት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከፍተኛ ፖለቲካዊ ቀውስ ውስጥ በመግባቱ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ከፍተኛና መካከለኛ ካድሬዎችን የቀነሰው ኢህአዴግ ከአዲስ አበባና ድሬዳዋ መስተዳደርና ከ9 ክልሎችና የፌደራል መስሪያ ቤቶች የመለመላቸውን 500 የሚሆኑ ካድሬዎችን ግንቦት 14 ቀን 2009 ዓም አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ በተገኙበት የሚያስመርቅ ሲሆን፣ በስልጠና የቆዩት ካድሬዎች ስለጨበጡት ትምህርት ፈተና እንደሚፈተኑ እንደሁም በሚቀጥሉት ቀሪ 3 ...
Read More »