ግንቦት ፳፱ ( ሃያ ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የወልቃይት ማንነት ኮሚቴ አስተባባሪ የሆኑትና ከሕዝባዊ አመጹ ጋር በተያያዘ ራሳቸውን ለመከላከል በወሰዱት እርምጃ ተከሰው በጎንደር አንገረብ እስር ቤት የሚገኙት ኮሎኔል ደመቀ ዘውዴ ዛሬ ግንቦት በ29 ቀን 2009 ዓ.ም ጎንደር በከፍተኛ ጥበቃ ስር ሆነው ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቀርበዋል። የኮሎኔል ደመቀ ዘውዴን የፍርድ ቤት ቀጠሮ ምክንያት በማድረግ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የአቶ ሃይለማርያምና ባለቤታቸው የቤተክርስቲያን ጉብኝት ምዕመናን አስቆጣ
ግንቦት ፳፱ ( ሃያ ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኃ/ማርያም ደሳለኝ ከባለቤታቸው ከወ/ሮ ሮማን ተስፋዬና ከሌሎች ባለሳልጣናት ጋር በእስራኤል በሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አብያተ ክርስቲያናት ባደረጉት ጉብኝት የቤተክርስቲያኒቱን ስርዓት አለመጠበቃቸው በርካታ ምዕመናንን አስቆጣ። አቶ ኃ/ማርያምና ባለቤታቸው የሌላ እምነት ተከታይ ቢኾኑም አብያተ ክርስቲያናቱን መጎብኘት እንደሚችሉ በመጥቀስ ሆኖም በጉብኝታቸው ወቅት ”ከሀይማኖቱ አስተምህሮና ቀኖና ውጪ ከነጫማቸው መቅደስ ውስጥ መግባታቸው አምላክን ...
Read More »በአማራ ክልል ከፍተኛ የተምች ወረርሽኝ በመከሰቱ ስጋት ላይ እንደሆኑ አርሶ አደሮች ተናገሩ፡፡
ግንቦት ፳፱ ( ሃያ ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በምእራብ ጎጃምና አዊ አስተዳደሮች ከፍተኛ የተምች ወረርሽኝ የተከሰተ ሲሆን፣ ወረርሽኙ ከእለት ዕለት በመስፋፋት በሁሉም አካባቢዎች የበቀሉ እጽዋትን በማውደም ላይ መሆኑን አርሶአደሮች ተናግረዋል። ገዥው መንግስት ተገቢውን የመከላከያ መድሃኒት አላቀረበልንም በማለትም ወቀሳ እያቀረቡ ነው። በአንዳንድ ቀበሌዎች የቀረበው መድሃኒት የአገልግሎት ጊዜው ያለፈ ቢሆንም “ዝም ብላችሁ ተጠቀሙበት” የሚል ምላሽ በመስጠት ህብረተሰቡን ለጉዳት ...
Read More »የአርበኞች ግንቦት 7 ታጣቂዎች በወገራ ወረዳ ከ 60 በላይ እስረኞችን ማስለቀቃቸው ተገለጸ
ኢሳት (ግንቦት 29 ፥ 2009) በሰሜን ጎንደር ዞን ወገራ ወረዳ የሚገኝ ወህኒ ቤት በአርበኞች ግንቦት 7 ታጣቂዎች መሰበሩንና ከ60 በላይ እስረኞች መለቀቃቸው ተገለጸ። ወህኒ ቤቱን ለመስበር የተካሄደው ይኸው ጥቃት ሰዓታት እንደወሰደ የንቅናቄው የመስክ አመራሮች የገለጹ ሲሆን፣ አንድ የጥበቃ አባል ሲገደል፣ ሶስቱ መቁሰላቸው ተመልክቷል። የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ ታጣቂዎች በሰሜን ጎንደር ዞን በወገራ ወረዳ ችንፉዝ ሲላሪ ከተማ በሚገኝ ልዩ እስር ቤት ...
Read More »የፌዴራል መስሪያ ቤቶች ከ 20 ቢሊዮን ብር በላይ ከህግ አግባብ ውጭ ማባከናቸው ታወቀ
ኢሳት (ግንቦት 29 ፥ 2009) የጠቅላይ ኦዲት ጽ/ቤት በ158 የፌዴራል መስሪያ ቤቶች ወደ 20 ቢሊዮን ብር አካባቢ ከህግ አግባብ ውጭ መባከኑን አስታወቀ። የባለፈው አመት በጀት አጠቃቀም አስመልክቶ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰሞኑን ሪፖርት ያቀረበው ጽ/ቤቱ፣ በተገባደደው በጀት አመት የተመዘገባው የገንዘብ መባከን ከባለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር በሁለት እጅ እጥፍ መብለጡንም ገልጿል። አላስፈላጊ የተባሉ ወጪዎችን ከመጠን ያለፈ በጀት፣ ያልተሰበበሰቡ ግብሮችን፣ እንዲሁም የገባበት ...
Read More »በጋምቤላ ክልል በጎርፍ አደጋ የተፈናቀሉ ከሁለት ሺ በላይ ነዋሪዎች ዕርዳታ እንዳልደረሳቸው ተገለጸ
ኢሳት (ግንቦት 29 ፥ 2009) በቅርቡ በጋምቤላ ክልል ደርሶ በነበረ የጎርፍ አደጋ ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ ከሁለት ሺ በላይ ነዋሪዎች አሁንም ድረስ ዕርዳታን አየተጠባበቁ እንደሆነ ተገለጸ። በግንቦት ወር መጀመሪያ ላይ በክልሉ በሚገኙ አምስት ቀበሌዎች የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ 2ሺ 400 አካባቢ ሰዎች ተፈናቅለው እንደነበር የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ማክሰኞ አስታውቋል። ይሁንና ነዋሪዎቹ ከመኖሪያ ቀያቸው ከተፈናቀሉ አንድ ወር አካባቢ ቢሞላቸውም ...
Read More »አሜሪካ የተመድ የሰብዓዊ መብት ምክር ቤት ጸረ-እስራዔል አቋም ያራምዳል በማለት ከአባልነት ልትሰናበት ትችላለች ተባለ
ኢሳት (ግንቦት 29 ፥ 2009) አሜሪካ የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ምክር ቤት ጸረ-እስራዔል አቋምን ይዟል በማለት ከምክር ቤቱ አባልነት ልትሰናበት እንደምትችል ማክሰኞ አሳሰበች። የምክር ቤቱ 47ኛ አባል ሃገራት በአለም ዙሪያ ስላሉ የሰብዓዊ መብት ሁኔታዎች ላይ ለመምከር በስዊዘርላንድ መዲና ጄኔቭ የሁለት ሳምንት ጉባዔውን እንደጀመሩ ኢንዲፔንደንት ጋዜጣ ከስፍራው ዘግቧል። ሂውማን ራይትስ ዎች መካሄድ በጀመረው መድረክ የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ሁኔታ አጀንዳ ሆኖ እንዲቀርብ ...
Read More »በኦሮሚያ ክልል የመጀመሪያ ደረጃ የአማርኛና የኦሮምኛ ቋንቋ ስርዓተ ትምህርቶች ክህሎት ስለማያጎለብቱ ክለሳ ሊደረግባቸው ነው ተባለ
ኢሳት (ግንቦት 28 ፥ 2009) በኦሮሚያ ክልል ከአምስተኛ እስከ ስምንተኛ ክፍል ከአምስት አመት በላይ በሁለተኛ ቋንቋነት ሲያገለግሉ የነበሩ የተማሪዎች የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መጻህፍት ክለሳ እንዲደረግባቸው መወሰኑን የክልሉ የትምህር ቢሮ ገለጸ። በክልሉ ይሰጥ የነበረው የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት የተማሪዎችን የአማርኛ ቋንቋ ክህሎት በተገቢው ሁኔታ የማያጎለብትና የማያዳብር ሆኖ በመገኘቱ እንዲሻሻል መደረጉን ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል። ትምህርት ሚኒስቴር ከ5ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ላሉ ...
Read More »የፌዴራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት በዶ/ር መረራ ጉዲና፣ በኢሳትና ኦኤምኤን ላይ የቀረቡ ክሶች እንዲሻሻሉ ብይን ሰጠ
ኢሳት (ግንቦት 28 ፥ 2009) የፌዴራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት በዶ/ር መረራ ጉዲና እንዲሁም በኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን (ኢሳት) እና በኦሮሞ ሚዲያ ኔትዎርክ ላይ በአቃቤ ህግ የቀረቡ ክሶች እንዲሻሻሉ ብይን ሰጠ። ጠቅላይ አቃቤ ህግ የመሰረተባቸውን ክስ መሰረት በማድረግ ዶ/ር መረራ ጉዲና የቀረበባቸው ክስ እንዲሻሻል ጥያቄን አቅርበው የነበረ ሲሆን፣ ተከሳሹ ክሳቸው በተናጠል እንዲታይ መጠየቃቸው ይታወሳል። ይህንኑ ጉዳይ ሲከታተል የነበረው ፍርድ ቤቱ ከተከሳሹ ጋር ...
Read More »ስድስት የአረብ ሃገራት ከኳታር ጋር የነበራቸውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን አቋረጡ
ኢሳት (ግንቦት 28 ፥ 2009) ሳውድ አረቢያን ጨምሮ ስድስት የአረብ ሃገራት ኳታር አይሲስን ጨምሮ የተለያዩ ታጣቂዎችን ትደግፋለች በማለት ከሃገሪቱ ጋር ያላቸውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አቋረጡ። ሳውዲ አረቢያ፣ ግብፅ፣ የተባበሩት አረብ ኤመሬትስ፣ ባህሬን፣ የመን እና ሊቢያ ከኳታር ጋር ያላቸው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያቋረጡ ሃገራት ሲሆኑ፣ ሃገራቱ በሃገራቸው የሚገኙ የኳታር ዜጎች እንዲሁም ዲፕሎማቶች ሃገራቸውን በአስቸኳይ ለቀው እንዲወጡ መጠየቃቸውን ቢቢሲ ሰኞ ዘግቧል። ሳውዲ አረቢያ ከኳታር ...
Read More »