ሰኔ ፲፬( አሥራ አራት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የክልሉ የወንጀል መከላከል ኃላፊ ስራውን በፈቃዱ ለቋል በአማራ ክልል ህዝብ ዘንድ በከፍተኛ ደረጃ የሚጠሉትና የህወሃት ቀኝ እጅ ተድርገው የሚቆጠሩት የአቶ ዓለምነው መኮንን የግል አጃቢ የሆነው አንዋር ሙሃመድ የተባለው ግለሰብ፣ ባህርዳርቀበሌ 04 በሚገኘው ግሪንላንድ ሆቴል ውስጥ በጥይት ተመትቶ ተገድሎ ከተገኘ በሁዋላ፣ የብአዴን ካድሬዎችና የአቶ ዓለምነው የቅርብ ወዳጆች ሽብር ውስጥ መግባታቸውን ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በኦህዴድ ውስጥ የእርስ በርስ መጠላለፍና መወነጃጀል ተፈጥሯል
በኦህዴድ ውስጥ ያሉ የህወሓት ታማኞች ጓዶቻቸውን እያሳደዱና እያሰሩ ነው። ሰኔ ፲፬( አሥራ አራት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኦህዴድ ውሰጥ ያሉ ታማኝ የህወሓት አገልጋዮቸ አንፃራዊ በሆነ መንገድ የራስ መተማመንንበማዳበር ላይ ያሉትን የኦህዴድ አመራር አባላትን ማደን ጀምረዋል። የህወኃት ተላላኪዎቹ-ጓደኞቻቸውን ኦህዴድ ውስጥ ሆነው ህገመንግሥቱን በኃይል ለማፍረስ ተንቀሳቅሰዋል ሲሉ ከሰዋቸዋል። ባለፉት 2 ቀናት የምስራቅ ሸዋና የአርሲ 3 የዞን አመራሮች የታሰሩ ሲሆን፤ አምስት ...
Read More »የደደቢት ተጨዋቾች በክፍያ ምክንያት ከክለቡ ጋር ውዝግብ ውስጥ ገብተዋል። የባህር ዳር ስፓርት ደጋፊዎች ተቃውሞ አሰሙ።
ሰኔ ፲፬( አሥራ አራት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከቅርብ አመታት ወዲህ በኢትዮዽያ ፕሪምየር ሊግ ዋነኛ ተፎካካሪ እየሆነ የመጣውና ለየሊጉን ዋንጫ እስከማንሳት የደረሰው የትግራዩ ደደቢት እግር ኳስ ክለብበዘንድሮ አመት የውድድር ዘመን ለተጨዋቾቹ ደሞዝ ባለመክፈሉ በክለቡ ውስጥ ውዝግብ ተፈጥሯል። ክለቡ የአምስት ወር ደሞዝ አልከፈለንም በማለት የቡድኑ ወሳኝ ተጨዋቾች የሆኑት አይናለም ኃይሌ ፣ አስራት መገርሳ ፣ ሳምሶን ጥላሁን ፣ አክሊሉ አየነው ...
Read More »ከ470 ብር ሺህ በላይ አጭበርብራ የታሰረች ግለሰብ በትዕዛዝ ተፈትታ ደህንነት ሥራ ላይ ተመደበች
ሰኔ ፲፬( አሥራ አራት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአማራ ክልል ፓሊስ ኮሚሽን በመረጃ ሠራተኝነት ስትሰራ የነበረችው እና “ቦታ አሰጣችኋለሁ” በማለት ከባህር ዳር ነጋዴወችና ከተለያዩ ግለሰቦች ከ470.00ሺህ ብር በላይ ገንዘብ በመቀበል ክስ ተምስርቶባት ታስራ የነበረች ሴት በትዕዛዝ ተፈትታ አሁንም በደህንነትና ስለላ ሥራ መሰማራቷ ተጠቆመ። በፈጸመችው የማጭበርበር ወንጀል ተይዛ በሙስና ተከሳ ከ 5 ወር በላይ በእስር ያሳለፈችው የትግራይ ተወላጇ ሰላም ...
Read More »የፌዴራል አቃቤ ህግ ዶ/ር መረራ ያቀረቡትን የክስ መቃወሚያ ባለመቀበል ለፍ/ቤት አቤቱታ አቀረበ
ኢሳት (ሰኔ 13 ፥ 2009) የኢትዮጵያ አቃቢያን ሕግ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና ያቀረቡትን የክስ መቃወሚያ እንደማይቀበሉት ለፍርድ ቤት አቤቱታ አቀረቡ። የፌደራል አቃቤ ሕጎች ማክሰኞ ሰኔ 13/ 2009 ለፍርድ ቤት ባቀረቡት የተቃውሞ አቤቱታ ዶ/ር መረራ ጉዲና ክሳቸው ከኢሳትና ኦኤምኤን ተለይቶ የሽብር ክሳቸው በሌላ መታየቱን እንደማይቀበሉ ገልፀዋል። ዶ/ር መረራ ጉዲና በአቃቤ ሕግ የቀረበውን በርካታ ክሶች ከሽብርተኛ ጋር የሚያገናኛቸው ነገር ...
Read More »ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት 80 ዓመታት ከግማሽ በላይ የቡና ምርቷን ልታጣ እንደምትችል አንድ ጥናት አመለከተ
ኢሳት (ሰኔ 13 ፥ 2009) በዓለም አቀፍ ደረጃ እየተከሰተ ባለው የአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ በቀጣዬቹ 80 ዓመታት ኢትዮጵያ ከ60 በመቶ በላይ የቡና ምርቷን ልታጣ እንደምትችል አንድ ጥናት አመለከተ። ኔቸር ፕላንትስ የተሰኘ የሳይንስ መፅሄት ላይ የወጣው አዲስ ጥናት እንዳመለከተው የኢትዮጵያ ገበሬዎች ከፍተኛ ወደሆኑ መልከአምድሮች ምርታቸውን ካላበቀሉ 60 በመቶ የቡና ምርት ሊጠፋ ይችላል። በጥናቱ እንደተገለፀው የአካባቢ የአየር ንብረት ተፅዕኖ የሙቀት መጨመር አነስተኛ ...
Read More »ከአውስኮድ ክለብ ጋር ባህርዳር ላይ የእግር ኳስ ግጥሚያ ማድረግ የነበረበት የመቀሌ ቡድን በጸጥታ ምክንያት ጨዋታውን ሰረዘ
ኢሳት (ሰኔ 13 ፥ 2009) ከአማራ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት /አውስ ኮድ / ክለብ ጋር የእግር ኳስ ውድድር ለማካሄድ ባህር ዳር መግባት የነበረበት የመቀሌው ከነማ ቡድን በጸጥታ ስጋት ምክንያት ጨዋታውን መሰረዙ ተሰማ ። የመቀሌው እግር ኳስ ክለብ ከአማራ ስፖርት ኮሚሽንና ከክልሉ መንግስት የጸጥታ ዋስትና እንዲሰጠው ጠይቆ የጽሁፍ ደብዳቤ ባለማግኘቱ በጸጥታ ስጋት ጨዋታውን መሰረዙ ታውቋል። በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደራል ህግና ...
Read More »በአዲስ አበባ ተግባራዊ ይሆናል ተብሎ የሚጠበቀው የቀን ገቢ ግምት አሰራር አድሎአዊ እንደነበረ ተገለጸ
ኢሳት (ሰኔ 13 ፥ 2009) የአዲስ አበባ አስተዳደር የገቢዎች ኤጀንሲ በግንቦት 30 ቀን 2009 አ ም እንዳጠናቀቀ ይፋ ያደረገው የቀን ገቢ ግምት የስነ-ምግባር ችግር ያለበት በሙስና በዘመድ አዝማድና የፖለቲካ አባልነት ምክንያት አድሎአዊ አሠራር የተከተለ መሆኑን የንግዱ ማህበረሰብ አባላት ገለጹ። ይህ የተገለጸው የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባላስልጣና የአዲስ አበባ ከተማ ታክስ ፕሮግራም ዘርፍ በቀን ገቢ መረጃ አሰባሰብ ሂደት ላይ ከነጋዴ ተወካዮችና የነዋሪዎች ...
Read More »የተምች ወረርሽን በ6 የኢትዮጵያ ክልሎች ተከሰተ
ኢሳት (ሰኔ 13 ፥ 2009) በኢትዮጵያ በተከሰተው ድርቅ የተረጂዎች ቁትር ከ5.6 ሚሊዮን ወደ 7.8 ሚሊዮን በተሻገረበት ወቅት በ6 የሀገሪቱ ክልሎች የተምች ወረርሽን መከሰቱ ተገለፀ። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እንዳስታወቀው በ35 ዞን 233 ወረዳዎች ችግሩ ተከስቷል። የተባበሩት መንግስታት የሠብዓዊ ዕርዳት ማስተባበሪያ ቢሮ ወረርሽኙን በቅድሚያ የተከሰተው በደቡብ ክልል ሻላ ዞን የኪ ወረዳ ቢሆንም አሁን በ6 ክልሎች ተጨማሪ 232 ወረዳዎችን አጥቅቷል። ወረዳዎቹ የችግሩ ...
Read More »በባህርዳር ማረሚያ ቤት በርካታ ወታደራዊ አዛዦች መታሰራቸውን ምንጮች ገለጹ
ሰኔ ፲፫( አሥራ ሦስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቅርቡ የተደረገውን ህዝባዊ የለውጥ እንቅስቃሴ ተከትሎ በመከላከያ ውስጥ በተደረገው የ “ ጥልቅ ተሃድሶ ግምገማ” ሰበብ ከ50 ያላነሱ እስከ ኮሎኔልነት የሚደርስ ወታደራዊ ማእረግ ያላቸውና ተራ ወታደሮችና ለስርዓቱም ታማኞች አይደሉም በሚል ታስረው እንደሚገኙ የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። እስረኞቹ ጃዊ ውስጥ በሚገኝ የመከላከያ ካምፕ ውስጥ ለወራት ታስረው ከቆዩ በሁዋላ፣ በአማራነታቸው ብቻ ተገምግመው መታሰራቸውን ...
Read More »