(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 22/2009) ከጊኒ ህዝብ በዘረፉት ሀብት በአሜሪካ ተቀማጥለው ሲኖሩ የነበሩት አንድ የጊኒ የቀድሞ ከፍተኛ ባለስልጣን በአሜሪካ ፍርድ ቤት እስራት ተበየነባቸው። ወንጀል ሆኖ የቀረበባቸው ክስ ስልጣናቸውን ያለአግባብ በመጠቀም ዘርፈዋል በተባለው ሐብት ነው። አሜሪካ የሌቦች መደበቂያ እንደማትሆንም የአሜሪካ ባለስልጣናት አረጋግጠዋል። ከኢትዮጵያ ሀብት የዘረፉ የመንግስት ባለስልጣናት በዘመዶቻቸውና በራሳቸው ስም ወደ አሜሪካ ያሸሹትን ገንዘብ ለማስመለስ ኢትዮጵያውያን ለሚያደርጉት ጥረት በጊኒው ባላስልጣን ላይ አሜሪካ የወሰደቸው ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በባህርዳር የባለስልጣናት ንብረት እንደሆኑ የሚታመኑ ሆቴሎች ልዩ ጥበቃ እየተደረገላቸው ነው
(ኢሳት ዜና –ነሐሴ 22/2009)በባህርዳር የባልስልጣናት ንብረት እንደሆኑ የሚታመኑ ሆቴሎች የተለየ ጥበቃ እንደተጀመረላቸው ተገለጸ። የህውሃትና ብአዴን ባለስልጣናት በጀርባ በባለቤትነት የያዝዋቸው ሆቴሎች ጥቃት ሊደርስባቸው ይችላል በሚል በፌደራልና በልዩ ሃይል እየተጠበቁ መሆኑን ከደረሰን መረጃ ለማወቅ ተችሏል። የአቶ አዲሱ ለገስ ፓፒረስ፣ የአቶ በረከት ስምዖን ራይ ናይል እንዲሁም የአቶ አያሌው ጎበዜ ጋሳ ሆቴሎች ጥበቃ እየተደረገላቸው ከሚገኙ ሆቴሎች የሚጠቀሱ ናቸው። በሌላ በኩል በባህርዳር አንድ የደህንነት አባል ...
Read More »በኦሮሚያና ሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ ላይ ለአንድ ሰዓት የዘለቀ ውጊያ መደረጉ ተገለጸ
(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 22/2009) በኦሮሚያና ሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ ላይ ለአንድ ሰዓት የዘለቀ ውጊያ መደረጉ ተገለጸ። በሶማሌ ልዩ ሃይልና በኦሮሞ አርሶአደሮች መካከል በተደረገው ውጊያ ሶስት ሰዎች መቁሰላቸው የታወቀ ሲሆን አንደኛው የደረሰበት ጉዳት ከፍተኛ በመሆኑ ወደ አዳማ ሆስፒታል መወሰዱን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። ውጊያው መኢሶን በተባለች ከተማ አቅራቢያ ባሉ ሁለት ቀበሌዎች መካሄዱ ተገለጿል። በሌላ በኩል ባለፈው ሳምንት የተሳካ የአድማ ጥሪ ያደረጉት የኦሮሞ ወጣቶች በቀጣይ ...
Read More »በአሜሪካዋ ቴክሳስ ሀርቬይ አውሎ ንፋስ 30 ሺ ሰዎችን ከቀያቸው ሲያፈናቀል ከ450 ሺ በላይ የሚሆኑትን ደግሞ እርዳታ እንዲጠብቁ ማድረጉ ታወቀ
(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 22/2009) በአሜሪካዋ ቴክሳስ ግዛት የባህር ዳርቻዎች በተቀሰቀሰው ሀርቬይ አውሎ ንፋስ 30 ሺ ሰዎች ከቀያቸው ሲያፈናቀሉ ከ450 ሺ በላይ የሚሆኑትን ደግሞ እርዳታ በመጠባበቅ ላይ መሆናቸው ታወቀ። እስካሁንም በቴክሳስና በአካባቢዋ ሀርቬይ አውሎ ንፋስ ስላደረሰው ጉዳት አጠቃላይ መረጃ መስጠት ባይቻልም የግዛቲቱ አስተዳደር ግን በአካባቢው ወደ 400 ሺ የሚጠጉ ዜጎች ከኤሌክትሪክ አገልግሎት ውጪ ሆነዋል። ከአደጋው ጋር በተያያዘም 2 ሰዎች ሕይወታቸውን ማጣታቸው ታውቋል። ...
Read More »የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሕግ ውጪ የሰጠውን የሕንጻ ግንባታ የቢሮ እቃዎች የማሟላት ስራ ያለ ጨረታ ለአቶ ተክለብርሃን አምባዬ ባለቤት ሰጠ
(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 22/2009) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሸናፊውን ኩባንያ በመከልከል ለተክለብርሃን አምባዬ ኮንስትራክሽን ከሕግ ውጪ የሰጠውን የሕንጻ ግንባታ በተጠናቀቀበት በአሁኑ ወቅት የቢሮ እቃዎቹን የማሟላቱን ስራ ያለ ጨረታ ለአቶ ተክለብርሃን አምባዬ ባለቤት መሰጠቱ ታወቀ። የኮንስትራክሽን እቃዎቹን እንዲያቀርቡ ተመርጠው የነበሩት በቅርቡ የታሰሩት የአቶ አባይ ጸሀዬ የቅርብ ጊዜ ባለቤት ወይዘሮ ሳሌም ከበደ ነበሩ። አቶ ተክለብርሃን አምባዬ ለባንኩ ፕሬዝዳንት አቶ በቃሉ ዘለቀ በስጦታ መኖሪያ ቤት ...
Read More »በኦሮሚያ ክልል የተጀመረው አድማ በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ከፍተኛ የትራንስፖርት ችግር መፍጠሩ ተገለጸ
(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 19/2009) በኦሮሚያ ክልል የተጀመረው በቤት ውስጥ የመቀመጥና የስራ ማቆም አድማ በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ከፍተኛ የትራንስፖርት ችግር እየፈጠረ መሆኑ ተነገረ። በምዕራብ ኦሮሚያ በበርካታ አካባቢዎች የንግድ እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ ቆሟል። በአዲስ አበባ ዙሪያ ባሉ ከተሞች የንግድም ሆነ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ የለም። በምዕራብ አርሲ ከሻሸመኔ እስከ ባሌ ሮቤ ያለው መስመር ከእንቅስቃሴ ውጭ ሆኗል። የኦሮሚያው አድማ በአማራ ክልል የትራንፖርት አገልግሎት እንዲቋረጥ በማድረግ ለ3ኛ ...
Read More »ወደ ካናዳ ሲጓዙ በመኪና አደጋ ሕይወታቸው ያለፈው የሶስቱ የአንድ ቤተሰብ አባላት የቀብር ስነስርአት ነገ ቅዳሜ ይፈጸማል
(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 19/2009) ከአሜሪካ ወደ ካናዳ ሲጓዙ በአሰቃቂ አደጋ ሕይወታቸው ያለፈው ሶስት የአንድ ቤተሰብ አባላት የቀብር ስነስርአት በዋሽንግተን ግዛት ሲያትል ከተማ ነገ ቅዳሜ ይፈጸማል። ከሳምንት በፊት ነሐሴ 11 2009 በካናዳ አልበርት ግዛት ከመለስተኛ የጭነት መኪና ጋር በተፈጠር ግጭት አባትና እናት ተርፈው ሆስፒታል ሲወሰዱ ሶስቱም ልጆቻቸው በአደጋው ማለቃቸው ይታወሳል። ብሌን፣ክርስቲያንና እምነት የተባሉት የ16፣የ11 አመትና የ11 ወር ሕጻን ከወላጆቻቸው ጋር ለእረፍት ከአሜሪካ ...
Read More »የአማራና የቅማንት ህዝብ በማለት ለመከፋፈል እየተደረገ ያለው ሴራ መጨረሻ ጥፋት ሊሆን እንደሚችል ተገለጸ
(ኢሳት ዜና –ነሐሴ 19/2009)የአማራና የቅማንት ህዝብ በማለት በአንድ ላይ የሚኖርን ሕብረተሰብ ለመከፋፈል እየተደረገ ያለው ሴራ መጨረሻው ጥፋት ሊሆን እንደሚችል የአካባቢው ተወላጅ የሆኑ ሁለት ኢትዮጵያውያን አመለከቱ። የቅማንት ተወላጅና የጎንደር ሕብረት ስራ አስፈጻሚ አቶ አበበ ንጋቱና የአገው ምድር ተወላጅ የሆኑት አቶ አይሸሽም ሰለሞን እንደገለጹት በሕወሃት /ኢሃአዴግ የሚመራው አገዛዝ ሕዝብን በመከፋፈል ሐገሪቱን ይበልጥ ወደማያባራ ግጭት በመውሰድ የጥፋት እርምጃ እየፈጸመ ነው። የቅማንትና የአማራ ...
Read More »በኢትዮጵያ ከመንገድ ግንባታ ጋር ተያይዞ የሚጣሉ መርዛማ ቆሻሻዎች ለሕጻናት ሞት ምክንያት እየሆኑ ነው ተባለ
(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 19/2009)በኢትዮጵያ ከሚገነቡ አዳዲስ መንገዶች ጋር ተያያዞ የሚጣሉ መርዛማ ቆሻሻዎች ለሕጻናት ሞት ምክንያት እየሆኑ መምጣታቸውን አንድ ጥናት አመለከተ። ጥናቱን ያካሄዱት ከለንደንና ደብሊን ከሚገኙ ሁለት ዩኒቨርስቲዎች የመጡ ባለሙያዎች ናቸው። ከለንደንና ደብሊን እንደተውጣጡት ባለሙያዎቹ ገለጻ አዳዲስ መንገድ በሚገነባባቸው የኢትዮጵያ አካባቢዎች በሕገወጥ ሁኔታ የሚጣሉ መርዛማ ቆሻሻዎች ለሕጻናት ሞት ምክንያት ናቸው። በተለይ ደግሞ አዲስ በሚገነቡ መንገዶች በ5 ኪሎሜትሮች ዙሪያ የሚኖሩ እናቶች ሕጻናት ወልደው ...
Read More »ሳውዲአረቢያ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ከሀገሯ በሃይል እንዳታባርር ሒዩማን ራይትስ ዎች ተማጸነ
(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 19/2009) ከግማሽ ሚሊየን የሚበልጡ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ከሀገሯ በሃይል እንዳታባርር ሒዩማን ራይትስ ዎች ሳውዲአረቢያን ተማጸነ። የሳውዲአረቢያ መንግስት በሀገሪቱ የሚገኙና የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው ኢትዮጵያውያንን በሃይል እንደሚያስወጣ ትላንት ሀሙስ አስታውቋል። በኢትዮጵያ ያለው አገዛዝ ኢትዮጵያውያኑ ስደተኞች ከሳውዲአረቢያ እንዲወጡ ግፊት ቢያደርግም በተቀመጠው ጊዜ ገደብ ውስጥ የወጡት 45 ሺህ ብቻ ናቸው። ሌሎች ከ5 መቶ ሺ በላይ የሚሆኑት በሳውዲአረቢያ የሚኖሩና ህጋዊ ፈቃድ የሌላቸው ኢትዮጵያውያን ግን ...
Read More »