.የኢሳት አማርኛ ዜና

በኢትዮጵያ ያለው አገዛዝ የኢኮኖሚ እድገት አስመዝግቤያለሁ በሚል በሕዝብ ላይ የሚያደርሰውን በደል ለመሸፋፈን እየሞከረ መሆኑ ተገለጸ

(ኢሳት ዜና–መስከረም 5/2010)በኢትዮጵያ ያለው አገዛዝ የኢኮኖሚ እድገት አስመዝግቤያለሁ በሚል በሀገሪቱ ሕዝብ ላይ በአንድ ፈላጭ ቆራጭ የፓርቲ መዋቅር የሚያደርሰውን በደል ለመሸፋፈን እየሞከረ መሆኑን በአለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቀው ጸሃፊ ግራህም ፒብልስ ገለጸ። ጸሀፊው ጉዳዩን አስመልክቶ ባቀረበው ሃተታ እንደገለጸው ዓለም ዓቀፍ መገናኛ ብዙሃንና ምእራባውያን ኢትዮጵያን የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት አስመዝግባለች በሚል የሚያቀርቡት ሪፖርት የአገዛዙን ግፍና በደል ለመሸፈን ምክንያት ሆኗል። በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያውያን በሀገራቸው ባለው ...

Read More »

አዴሃን በጠገዴ ግጨው አካባቢ ለትግራይ ክልል የተሰጠው ቦታ የማያባራ የሕዝብ ግጭት ሊፈጥር እንደሚችል አስጠነቀቀ

(ኢሳት ዜና–መስከረም 5/2010) የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ/አዴሃን/ በጠገዴ ግጨው አካባቢ ለትግራይ ክልል በብአዴን ተላልፎ የተሰጠው ቦታ የማያባራ የሕዝብ ግጭት ሊፈጥር እንደሚችል አስጠነቀቀ። የትግራይና የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድሮች በቅርቡ ያደረጉት ስምምነት የሕዝብን ይሁንታ ያላካተተ በመሆኑ አካባቢውን ወደ ግጭትና ትርምስ ሊወስደው ይችላል ብሏል። መላው ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ የአማራ ሕዝብ ወልቃይትን ለማስመለስ የጀመረውን ትግል አጠናክሮ እንዲቀጥል የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ/አዴሃን/ጥሪ አቅርቧል። በቅርቡ በግጨው ጉዳይ ...

Read More »

በሰሜን ጎንደር ሊደረግ የታቀደውን ህዝበ ውሳኔ በመቃወም በተለያዩ አካባቢዎች ህዝቡ እርምጃ እየወሰደ መሆኑ ተገለጸ

(ኢሳት ዜና–መስከረም 5/2010) በሰሜን ጎንደር በ12 ቀበሌዎች ሊደረግ የታቀደውን ህዝበ ውሳኔ በመቃወም በተለያዩ አካባቢዎች ህዝቡ እርምጃ እየወሰደ መሆኑ ተገለጸ። ዕሁድ ሊደረግ በታቀደው በዚሁ ህዝበ ውሳኔ ሁለቱም ወገኖች ባለመሳተፍ እቅዱን እንዲያከሽፉም ጥሪ ተደርጓል። በመተማና ሽንፋ አካባቢዎች ግጭት ተፈጥሯል። ለዕሁዱ ህዝበ ውሳኔ በህወሀት የተሰማሩ የምርጫ አስፈጻሚዎችም ከየጣቢያ በህዝብ እየተባረሩ መሆኑ ታውቋል። ከ12ቱ ቀበሌዎች በ4ቱ ምርጫው መራዘሙ የተገለጸ ሲሆን በየአካባቢው ያለው ውጥረት በህዝበ ...

Read More »

በሶማሌና በኦሮሚያ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ የተፈናቃዮች ቁጥር ጨመረ

(ኢሳት ዜና–መስከረም 5/2010) በሶማሌና በኦሮሚያ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር በመጨመር ላይ መሆኑ ተገለጸ። ዛሬ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከሶማሌ ክልል ተፈናቅለው ወደ ድሬዳዋና አዋሳኝ የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች መግባታቸው ተገልጿል። በጂጂጋ የ28 ሰዎች የቀብር ስነስርዓት ዛሬ መፈጸሙ የተገለጸ ሲሆን፡ ትላንት ምሽት በከተማዋ የተደራጀ ዘረፋ ሲካሄድ እንደነበረ ለማወቅ ተችሏል። ከግጭቱ ጋር በተያያዘ በጂጂጋ ከተማ የሸቀጦችና የምግብ ዋጋ መጨመሩን ...

Read More »

የአሜሪካ ብሔራዊ የደህንነት ኤጀንሲ የኢትዮጵያው አገዛዝ ዜጎቹን እንዲሰልል የቴክኖሎጂ እገዛና ስልጠና እየሰጠ መሆኑ ተጋለጠ

(ኢሳት ዜና–መስከረም 4/2010)የአሜሪካ ብሔራዊ የደህንነት ኤጀንሲ የኢትዮጵያው አገዛዝ ዜጎቹን እንዲሰልል የቴክኖሎጂ እገዛና ስልጠና እየሰጠ መሆኑን ኢንተርሴፕት የተባለ ተቋም አጋለጠ። ብሔራዊ የደህንነት ኤጀንሲው በኢትዮጵያ የስለላ መረብ እንዲዘረጋ ትልቅ እገዛ ማድረጉን መረጃዎቹን ያሰባሰበው ይሄው ተቋም ገልጿል። የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በየአመቱ የሀገራትን ሰብአዊ መብት አያያዝ በማስመልከት በሚያወጣው መግለጫ ኢትዮጵያ ዜጎቿን መሰለሏንና ማፈኗን ቢያወግዝም የዚሁ ድርጊት ተባባሪ መሆኑ ግን ትክክል አለመሆኑን ተቋሙ ተችቷል። ...

Read More »

የአማራና የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንቶች ጠገዴ ላይ ያሳለፉትን ውሳኔ ልሳነ ግፉአንና የጠለምት አማራ ማንነት ኮሚቴ በጋራ እንደሚቃወሙት አስታወቁ

(ኢሳት ዜና–መስከረም 4/2010)የአማራና የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንቶች ጠገዴ ወረዳ ላይ ያሳለፉትን ውሳኔ ልሳነ ግፉአንና የጠለምት አማራ ማንነት ኮሚቴ በጋራ እንደሚቃወሙት አስታወቁ።   ሕወሃትና ተላላኪው ብአዴን በአዲሱ አመት ዋዜማ ለመላው የጎንደር ህዝብ የሰጡት ስጦታ ቢኖር ሰላምና አንድነቱን ሳይሆን አካሉ የሆነውን የጠገዴ ማህበረሰብን ለሁለት እንደ ቅርጫ መቀራመትን ነው በማለት እርምጃውን በጽኑ አውግዘዋል። ሕዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ የወልቃይትን መሬት ከረገጠበት ጊዜ ጀምሮ ሕዝቡ እስራት፣ድብደባና ...

Read More »

በኢትዮጵያ በክልሎች መካከል የተፈጠረው የወሰን ችግር የከፋ የሰብአዊ መብት ቀውስ ሊያስከትል እንደሚችል ሰብአዊ መብት ጉባኤ አሳሰበ

(ኢሳት ዜና–መስከረም 4/2010) በኢትዮጵያ በክልሎች መካከል የተፈጠረውና እየቀጠለ ያለው የወሰን ችግር መዳረሻውን ለመተንበይ የሚያስቸግር የከፋ የሰብአዊ መብት ቀውስ ሊያስከትል እንደሚችል ሰብአዊ መብት ጉባኤ አሳሰበ። በአሁኑ ወቅት በአራት ክልሎችና አካባቢዎች ከወሰን ጋር በተያያዘ ችግር መከሰቱና ውጥረት መንገሱን ሰሞኑን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።   የሰብአዊ መብት ጉባኤ በክልሎች መካከል ለግጭት መንስኤ የሚሆኑ ጉዳዮች በአስቸኳይ እልባት ይሰጣቸው በሚል ርእስ ባወጣው መግለጫ በአራት ክልሎችና አካባቢዎች ...

Read More »

ኦህዴድና ሶህዴፓ እርስ በርስ እየተወነጃጀሉ ነው

(ኢሳት ዜና–መስከረም 4/2010)ኦህዴድና ሶህዴፓ እርስ በርስ እየተወነጃጀሉ ነው። በኦሮሚያና በኢትዮጵያ ሶማሌ አዋሳኝ አካባቢዎች ሰሞኑን ከተከሰተውና ተባብሶ ከቀጠለው እልቂት ጋር ተያይዞ የሁለቱ ክልላዊ መንግስታት ቃል አቀባይ ቢሮዎች አንዱ ሌላኛውን ተጠያቂ የሚያደርግበት መግለጫ አውጥተዋል።   በአቶ አብዲ መሀመድ ኦማር የሚመራው የሶማሌ ክልላዊ መንግስት ባወጣው መግለጫ ሰሞኑን በኦሮሚያና ሶማሌ ወሰን አካባቢ የተነሳው ግጭት በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የሚደገፍና በክልሉ የታጠቁ ሃይሎች፣በክልሉ ፖሊስ፣ሚሊሺያና የኦነግ ቄሮ ...

Read More »

በኦሮሞና ሶማሌ ወሰኖች ላይ የተጀመረው ግጭት ተባብሶ መቀጠሉ ተገለጸ

(ኢሳት ዜና–መስከረም 4/2010) በኦሮሞና ሶማሌ ወሰኖች ላይ የተጀመረው ግጭት ተባብሶ መቀጠሉ ተገለጸ። በሺዎች የሚቆጠሩ የኦሮሞ ተወላጆች ከሶማሌ ክልል የተለያዩ ከተሞች ተፈናቅለው ወደ ሀረር መግባታቸው ታውቋል። ሁለቱ ክልሎች እየተወዛገቡ ነው። ከሁለቱም ወገኖች በርካታ ሰዎች ተገድለዋል። ግጭቱ ወደ አጠቃልይ ቀውስ ሊያመራ እንደሚችል እየተነገረ ነው። የሃይማኖት አባቶች ጥሪ አስተላልፈዋል። ይህ ግጭት በአገዛዙና በህዝብ መካከል ብቻ መሆኑን በሶማሌ እና ኦሮሚያ አካባቢዎች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በኢሳት ...

Read More »

በሶማሌና ኦሮሚያ አዋሳኝ አካባቢዎች የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ በበርካታ ከተሞች ተቃውሞ እየተካሄደ ነው

(ኢሳት ዜና–መስከረም 3/2010)በምስራቅ ኢትዮጵያ በሶማሌና ኦሮሚያ አዋሳኝ አካባቢዎች የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ በበርካታ ከተሞች ተቃውሞ እየተካሄደ ነው። አጠቃላይ የተቃውሞ ሰልፍም እንዲደረግ በኦሮሞ ወጣቶች ጥሪ መተላለፉ ተሰምቷል። ዛሬ በሀረርና በድሬዳዋ ተቃውሞ ተጀምሯል። የስራ ማቆም አድማም ተመቷል። በድሬደዋ ወታደሮች በብዛት መግባታቸው እየተነገረ ነው።በአወዳይ ከ10 በላይ ሰዎች መገደላቸውንም የደረሰን መረጃ አመልክቷል። በሌላ በኩል መንግስት ግጭቱ ቆሟል ሲል መግለጫ ሰጥቷል። ግጭቱ ቀጥሏል። የቀውስ ቀጠናው አድማሱን ...

Read More »