(ኢሳት ዜና–መስከረም 25/2010) አለም አቀፉ የሽብር ቡድን አይሲስ ከላስቬጋሱ ነፍሰ ገዳይ ጋር ግንኙነት አለኝ በሚል ያወጣውን መግለጫ ውድቅ የሚያደርጉ ሪፖርቶች በመውጣት ላይ መሆናቸው ታወቀ። ይህ በእንዲህ እንዳለም የነፍስ ገዳዩ ጓደኛ ለእረፍት ሄዳለች ከተባለበት ከፊሊፒንስ ወደ አሜሪካ ተመልሳ ለአሜሪካ የምርመራ ቡድን አባላት ቃሏን መስጠቷ ታውቋል። በአሜሪካ ኔቫዳ ግዛት ላስቬጋስ ከተማ 59 ሰዎችን በመግደል ከ500 በላይ ሰዎችን ያቆሰለው የ64 አመቱ ሴቴፈን ፓዶክ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በኢየሩሳሌም የሚገኘው ዴር ሱልጣን ገዳም አደጋ ላይ መሆኑ ተገለጸ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 25/2010) በኢየሩሳሌም የሚገኘው ዴር ሱልጣን ገዳም አደጋ ላይ መሆኑ ተገለጸ። ከላይ በግሪክ ቤተክርስቲያን የተጀመረው ግንባታ ገዳሙን እያፈረሰው በመሆኑ አንደኛው ቤተክርስቲያን ሙሉ በሙሉ መዘጋቱን በእስራኤል የኢትዮጵያ ማህበረሰብ በተለይ ለኢሳት ገልጿል። የሚካኤል ቤተክርስቲያን በጣሪያው ላይ በደረሰበት መደርመስ የተዘጋ ሲሆን የመድሃኒዓለም ቤተክርስቲያንም የመናድ አደጋ አንዣቦበታል ተብሏል። ጉዳዩ ያሳሰባቸው ኢትዮጵያውያን በእስራኤል ከሚገኙ የቤተክርስቲያኒቱ አባቶች ጋር ትላንት ስብሰባ ማድረጋቸው ታውቋል። የኢትዮጵያ ኤምባሲም ሆነ ...
Read More »በቋንቋ ላይ የተመሰረተው የፌደራሊዝም ስርአት አደጋ ላይ ነው ተባለ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 25/2010) በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ያለውና በቋንቋ ላይ የተመሰረተው የፌደራሊዝም ስርአት አደጋ ላይ መሆኑን የሶማሌ ክልላዊ አስተዳደር አስጠነቀቀ። የክልሉ አስተዳደር ከሶማሌ የሀገር ሽማግሌዎች ጋር በጅጅጋ ምክክር ካደረገ በኋላ የኦሮሚያ አመራሮች ወረራ እየፈጸሙና የግፍ ግድያ እያካሄዱ ነው ሲል መግለጫ አውጥቷል። በሶማሌና በኦሮሚያ መካከል የተከሰተው ግጭት በፌደራሉ ጣልቃ ገብነት በርዷል ቢባልም ችግሩ ተባብሶ መቀጠሉ እየተነገረ ነው። የሶማሌ ክልላዊ መንግስትና የአካባቢው የሀገር ...
Read More »አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከእስር እንዲፈቱ የብሪታኒያ መንግስት ግፊት እንዲያደርግ ጥሪ ቀረበ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 25/2010)ሁለት የብሪታኒያ የጠበቆች ማህበራት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከእስር እንዲፈቱ የብሪታኒያ መንግስት ግፊት እንዲያደርግ ጥሪ አቀረቡ። ዘጋርዲያን ማክሰኞ ዕለት ለንደን ላይ ባቀረበው ዘገባ እንዳመለከተው ሁለቱ የብሪታኒያ የጠበቆች ማህበራት ጥሪያቸውን ያቀረቡት ለብሪታኒያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በጻፉት ደብዳቤ ነው። የሎው ሶሳይቲ ፕሬዝዳንት ጆ ኤጋንና የባር ካውንስል ሊቀመንበር አንድሪው ላንግዶን በጋራ ለብሪታኒያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን በጻፉት የጋራ ደብዳቤ የብሪታኒያ መንግስት ...
Read More »በስፔን የካታላን ግዛት ነዋሪዎች የመገንጠል ውሳኔ አጨቃጫቂ ሆኖ መቀጠሉ ተገለጸ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 24/2010)በስፔን የካታላን ግዛት ነዋሪዎች ባለፈው እሁድ መገንጠልን በመደገፍ ድምጽ ከሰጡ በኋላ ውሳኔው አጨቃጫቂ ሆኖ መቀጠሉ ተገለጸ። የስፔኑ ንጉስ ፊሊፔ በቴሌቪዥን መስኮት ቀርበው የመገንጠል አጀንዳን ያቀነቀኑት ሰዎች ለሀገሪቱ ሃያልነት ያላቸውን ንቀት አሳይተዋል ሲሉም ተናግረዋል። ተገንጣዮቹ የሕግ የበላይነትና የዲሞክራሲ መርህን ጥሰዋል ብለዋል የሀገሪቱ ንጉስ። ባለፈው እሁድ በስፔን የካታላን ግዛት ነዋሪዎች መገንጠልን በመደገፍ ድምጽ ሲሰጡ ውለዋል። 90 በመቶ የሚሆነው ህዝብ መገንጠልን ...
Read More »የወጋገን ባንክ የጥበቃ ሰራተኛ ሁለት ሰዎችን በመግደል ራሱን አጠፋ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 24/2010)በአዲስ አበባ ከተማ የወጋገን ባንክ የጥበቃ ሰራተኛ ሁለት ሰዎችን በመግደል ራሱን ማጥፋቱ ታወቀ። ከአይን ምስክሮችና ከሀገር ቤት ጋዜጦች ማረጋገጥ እንደተቻለው ድርጊቱ የተፈጸመው ዛሬ ከሰአት በኋላ ሲሆን ግለሰቡ ግድያውን ለምን እንደፈጸመና በመጨረሻም ራሱን ያጠፋበት ምክንያት አልታወቀም። ቦሌ ኦሎምፒያ አካባቢ በሚገኘው ደምበል ሕንጻ 10ኛ ፎቅ ላይ የተፈጸመውን ግድያ በተመለከተ ዝርዝር መረጃዎችን ለግዜው ማግኘት አልተቻለም። አንዳንድ ምንጮች እንደገለጹት ግድያውን የፈጸመው የወጋገን ...
Read More »ኢትዮጵያና ሱዳን በየሀገራቸው ገንዝብ የንግድ ልውውጥ ለማድረግ ተስማሙ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 24/2010) ኢትዮጵያና ሱዳን በየሀገራቸው ገንዝብ የንግድ ልውውጥ ለማድረግ ከስምምነት ደረሱ። ስምምነቱ ለሶስት አመት የሚቆይ መሆኑም ተገልጿል። በተለያዩ የአለም ሀገራት የየሀገራቸው ገንዘብ የመጠቀም የንግድ ልውውጥ የማድረግ ስምምነት ይደረሳል። እንዲህ አይነቱ ስምምነት በተለይ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ እጥረት ውስጥ የሚገኝ ሀገር ጎረቤት ካለና በፖለቲካ ከሚስማማው ጋር የሚፈጽመው ስምምነት ነው ይላሉ የዘርፉ ባለሙያዎች። የኢትዮጵያ መንግስትም በውጭ ምንዛሪ እጥረት የሚዋዥቅ በመሆኑ ችግሩን በዘላቂነት ...
Read More »የባህርዳር ዩኒቨርስቲ ወደቀደመው አሰራር ተመልሻለሁ ሲል ተማሪዎቹ ግን የተቀየረ ነገር የለም አሉ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 24/2010)የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ወደቀደመው አሰራር ተመልሻለሁ ቢልም ተማሪዎቹ ምንም የተቀየረ ነገር እንደሌለ ገለጹ። ከ1500 በላይ የ4ኛ ዓመት የምህንድስና ተማሪዎች በውጤት አሰጣጥ ላይ በዩነቨርሲቲው የተጀመረውን አዲስ አሰራር በመቃወም ፈተናውን አንወስድም በማለታቸው ባለፈው ሰኞ ግቢውን ለቀው እንዲወጡ ተደርገዋል። በባህርዳር በየአብያተክርስቲያናቱ የተጠለሉት ተማሪዎች በከፍተኛ ችግር ላይ መሆናቸውንም ምንጮች ካደረሱን መረጃ ለማወቅ ተችሏል። ዩነቨርሲቲው ወደቀድሞው የውጤት አሰራር መመለሱን ቢገልጽም ወደግቢው ያመሩት አንዳንድ ተማሪዎች ...
Read More »በኢትዮጵያና ኬንያ ድንበር ስኳር ጭነው የቆሙት ከባድ ተሽከርካሪዎች ባለንብረቶች ችግር ውስጥ መውደቃቸውን ገለጹ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 24/2010) በኢትዮጵያና ኬኒያ ድንበር ሞያሌ ላይ ከሁለት ወራት በላይ ስኳር ጭነው የቆሙት ከባድ ተሽከርካሪዎች ባለንብረቶች ከፍተኛ ችግር ውስጥ መግባታቸውን በተለይ ለኢሳት ገለጹ። ከ100 በላይ የሚሆኑትና እያንዳንዳቸው 400ኩንታል ስኳር የጫኑት እነዚህ ተሽከርካሪዎች ለከፍተኛ ብልሽት እየተዳረጉ ሲሆን የጫኑት ስኳርም በመቅለጥ ላይ መሆኑን አስታውቀዋል። በባንክ ብድር የገዟቸው ተሽከርካሪዎች ያለስራ ከሁለት ወራት በላይ በመቆየታቸው ለባንክ የሚከፍሉት ገንዘብ እንደሌላቸው የጠቀሱት ባለንብረቶቹ አቶ ሃይለማርያም ...
Read More »በላስቬጋስ የጅምላ ግድያን ከፈጸመው ግለሰብ የሆቴል ክፍልና ከቤቱ በአጠቃላይ 42 መሳሪያዎች ተገኙ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 23/2010)በኔቫዳ ግዛት ላስቬጋስ ከተማ የተፈጸመውና በአሜሪካ ታሪክ ከፍተኛ የተባለው የጅምላ ግድያን ከፈጸመው ግለሰብ የሆቴል ክፍልና ከቤቱ በአጠቃላይ 42 መሳሪያዎችን ማግኘቱን የግዛቲቱ ፖሊስ አስታወቀ። በአደጋው የሞቱት ሰዎች ቁጥር 59 ሲደርስ የቆሰሉት ደግሞ 527 ደርሰዋል። አለም አቀፉ አሸባሪ ቡድን አይ ሲስ ስቴፈን ፓዶክ እምነቱን የቀየረ አባላችን ነው ሲል መግለጫ ሰጥቷል። የአሜሪካ ባለስልጣናት ድርጊቱን ከሽብር ጋር የሚያገናኘው ምልክት አላየንም ሲሉ ፕሬዝዳንት ...
Read More »